Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abdisa
Member
Posts: 3313
Joined: 25 Apr 2010, 19:14

"ሕዝቤ ሆይ ፥ ስማ!" ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የአደራ መንግስት እንዲመሰረት ጥሪ አቀረቡ። ሊቀ ጳጳሱ "ትግረኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ይህ ጊዜ አያምልጣችሁ!" ይላሉ

Post by Abdisa » 29 Dec 2017, 04:15

በተለይም ለትግረኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ይህ ጊዜ አያምልጣችሁ ። የእናንተ ነን የሚሉ ጥቂት ባለሥልጣናት አያታሏችሁ ። እነርሱ የሚሄዱበት መንገድ መልካም አይደለም ፣ ዘላቂ መፍትሔም የለውም ። ይልቅስ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገናችሁ ጋር ሁናችሁ የመፍትሔው አካል ሁኑ እንላለን ።
Awash, this message is for you. Pay close attention.
ሕዝቤ ሆይ ፥ ስማ! (አባ ጴጥሮስ)

Image
አባ ጴጥሮስ (የአውስትራልያ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ)

 • “ሕዝቤ ሆይ ፥ ሕጌን አድምጡ ፤ ጆሮአችሁንም ወደ አፌ ቃል አዘንብሉ ። አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ ፤ ከቀድሞ ጀምሮ ያለውንም ተምሳሊት እናገራለሁ። መዝ 77፥1።


በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

 • በሀገር ውስጥና በመላውዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያን ለምትወዱ ወገኖቻችን!

  ይህ ዘመን ከምንጊዜውም በላይ በኢትዮጵያ ላይ የፈተና ደመና ያንዣበበበት ጊዜ መሆኑ ለማንም የተሰወረ አይደለም ። አብሮ የኖረው የሕዝባችን የመተዛዘን የመደጋገፍ ባህል በዘመኑ ፖለቲከኞች ምክንያት እየተመናመነ ሄዷል። አልፎ ተርፎም እርስ በርስ በመተላለቅ ላይ ይገኛል። በኢትዮጵያ ሱማሌና በኦሮምኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን መካከል ፥ ጥቅመኛ ፖለቲከኞች ያቀጣጠሉት የርስ በርስ መፋጀት በኢትዮጵያውያን እንኳን ሊደረግ ሊታሰብ እንኳ የማይችል ድርጊት እየተደረገ ይታያል።

  በዚህ ወቅት ሰዎች በራሳቸው ወገኖች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን መስማት የሕዝባችን የርስ በርስ ጥላቻ ሁኔታ በከፋ ጎዳና ላይ መሆኑን ዓለም እያየ የሚሰቀው እየሳቀብን ፥ የሚያዝነውም አብሮን እያዘነ ይገኛል ።

  በሌላ መልኩ አገርን እናስተዳድራለን የሚሉት ፖለቲከኞች የሚያሳስባቸው የሀገር አንድነትና የሕዝብ ደህንነት ሁኔታ ሳይሆን እናጣዋለን የሚሉት ሥልጣን ብቻ ነው ። የፖለቲካ ጥቅም ያስገኝልናል ብለው እስካመኑ ድረስ የወገኖች አሰቃቂ ሞት ለእነርሱ ምንም አይደለም፥ ከምንም አይቈጥሩትም። አጥፊ እንዲቀጣ ሳይሆን ፥ በሞቱትና በተንገላቱት ዜጎች ላይ የፖለቲካ ትርፍ ማግኘት ነው የሚፈልጉት። በእንደዚህ አካሄድ ደግሞ ሌላ ጥፋትም ሊደርስ ይችላል ። የሚቀጡት ያጠፉት ሳይሆኑ ያለ አበሳቸው የሚጨፈጨፉትና የሚሞቱት የእነርሱ ወገኖች የሆኑ ንጹሐን ወገኖች ናቸው ።

  ከዚህም ጋር ለሀገር አንድነትና ለሕዝብ ደኅንነት ተብሎ የተቋቋመው የደኅንነት ፥ የፖሊስና የመከላካያ ሠራዊት ፖለቲካ ማስፈጸሚያ ሁኖ ሰላማዊ ዜጎችን በማሰቃየት ላይ መሆኑን እየሰማን ነው። በጠቅላላ የሚታዩት ነገሮች ሁሉ ከቀጠሉ የኢትዮጵያ ጉዳይ ወዴት እንደሚሄድ ሁላችንም አናውቅም ከእግዚአብሔር በቀር ።

  በዚህ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ምን ማድረግ አለባት ? ቤተ ክርስቲያን አሁንም ለተከበረውና ጨዋ ለሆነው ሕዝባችን መልእክት አላት፦ “ሕዝቤ ሆይ ! ስማ” ትላለች ። መሪዎች ጥበብ አጥተው ኃላፊነታውንም ዘንግተው ለሥልጣን በሚሻኮቱበት በዚህ ጊዜ ። ለዜጎች የሚያስብ ጠፍቶ ዜጎች እርስ በርሳቸው ሊባሉ በቀረቡበት ጊዜ፣ ሀገሪቱን እንመራለን የሚሉት ተንኮለኛ ፖለቲከኞች ኃላፊነታቸውን መወጣት ባቃታቸው በዚህ ጊዜ፤ የሀገሪቱ ባለቤት የኢትዮጵያ ሕዝብ የራሱን ኃላፊነት መወጣት ይጠበቅበታል። ስለዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ እስከ አሁን በታሪክ ተባብሮ ለኖረው ሕዝባችን የሚለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ !! በዚህ ወቅት የሚጠቅምህ ከአባቶችህ የወረስከው ጨዋነትህ ነው።ያ የተለመደው አብሮነትህና ተከባብሮ መኖርህ ነው። ለዚህ ነው በእግዚአብሔር ቃል «ሕዝቤ ሆይ ! ስማ» የምንለው ።

  በሀገራችንም በዓለም ታሪክም እንደሚታወቀው ፥ የመሪዎች መለዋወጥ የተለመደ ነው ፣ አንዱ ሲወድቅ ሌላ እየተተካ ነው የተኖረው ። በሽህ በሚቈጠሩት ዘመናት በአንድ አገዛዝ የተመራ ዓለም የለም ። እንዲያ ቢሆን ኑሮ የባቢሎናውያን ሥልጣኔ ከስሞ ከነስም አጠራራቸው እንኳ እንዳይታወቁ አይሆኑም ነበር ። ግን አሁን እነርሱ በታሪክ ካልሆነ በቀር የሉም ፥ ግን የነዚያ ሕዝቦች ዘር ዛሬም አለ። የፈርዖን አገዛዝ አይኑር እንጂ የጥንት ግብጻውያን ዛሬም አሉ ። የአክሱም ሥርወ መንግሥት አይኑር እንጂ ኢትዮጵያውያን አሁንም አሉ ። ይህም የሆነው በመሪዎች ጥንካሬ ሳይሆን ፥ ጨዋው ሕዝባችን ተከባብሮ በመኖሩ ምክንያት ነው ።

  ዛሬ በሠለጠነ ዘመን ላይ ሆነን ከነበረው የበለጠ መሆን እንጂ አንሰን መገኝት የለብንም ፣ ስለሆነም እናንተ ሁላችሁ የአንዲት ኢትዮጵያ ልጆች ኢትዮጵያውያን ናችሁ ። እስከ አሁን እንዳደረጋችሁት ሁሉ አሁንም በነበረው መከባበራችሁ እንድትቀጥሉ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች ።

  የአገር እንድነትን ለመጠበቅ የሠለጠነው መለዮ ለባሽ ወታደር ሥራው አገርን መከላከል ሁኖ ሳለ፥ በዚህ ዘመን ግን ባለ ሥልጣኖች ሕዝቡን ለማስፈራራት ከተልእኮው ውጭ እየተጠቀሙበት ይገኛል። የፖሊስ ሠራዊቱም እንደዚሁ የሕዝብን ጸጥታ በማስከበር ፈንታ ሕዝቡን በማሸበር ግዳጅ ላይ መሰማራቱ የዕለት ከዕለት ወሬ ሁኗል። ሁኖም ግን መለዮ ለባሹ የሕዝብ ወገን መሆኑን ተገንዝቦ ፥ ሕዝቡን ከማሰር ከማሰቃየት ከመግደል ተቆጥቦ ፥ ለተጠቂው ወገን መቆም ያለበት ጊዜው አሁን መሆኑን በዓለም ያለ ሕዝብ ሁሉ ያውቃል። ቅዱስ ሲኖዶስም በዚህ ይስማማል። መለዮ ለባሹ የታጠቀው የጦር መሳሪያው የሀገር ድንበር ለማስጠበቅ መሆኑን ተገንዝቦ አፈሙዙን ከሰላማዊው ሕዝብ ላይ ዞር እንዲያደርግ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያቀርባል። በተጨማሪም የወቅቱ የሀገራችን ሁኔታ የሚዋጀው በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያገባቸውን መላው አካላት ያካተተ የአደራ መንግስት እንጂ ገዢውን መንግስት በወታደራዊ መንግስት በመቀየር ወደ ሌላ ማብቂያ ወደሌለው የጦርነት አዙሪት ከማስገባት እንዲቆጠብ ቅዱስ ሲኖዶሱ እጅግ በጣም አጥብቆ ያሳስባል።

  ከዚህ ጋር አማራጭ አለን ብላችሁ በተቃዋሚነት የቆማችሁ ወገኖቻችን ምሁራን ፥ የሃይማኖት ሰዎች! ዛሬ በምድራችን በተጨባጭ እየተካሄደ ያለው የፖለቲካ ጉዳይ የማይሰማችሁ ከሆነ፥ ኢትዮጵያውያን ነን ብላችሁ ራሳችሁን የማትጠሩበት ጊዜ እየመጣ ነው። ለዚህ ትንቢት ተናጋሪ መሆን አስፈላጊያችን አይደለም። ትናንት አብረው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ዛሬ እንደ ጠላት ከመተያየት አልፈው ሲገዳደሉ ማየት በዘመናችን ይሆናል ብለን የማናስበው አሳዛኝ ጉዳይ ነው። በዚህ ጊዜ ችግሩን በዝምታ ማለፍ ወይም ይዋል ይደር እያሉ ቸል ማለት ፣ ለሥልጣን ሲሉ ሰው ከሚገድሉትና ከሚያስሩት የሕወአት ባለ ሥልጣናት ያነሰ በደል ሊሆን አይችልም ። ይህ እኮ የአማራጭ ጉዳይ አይደለም ። ይህ የመኖርና ያለ መኖር ጉዳይ ነው። ስለዚህም ይዋል ይደር ሳትሉ ለዚህ ችግር የመፍትሔ አካል እንድትሆኑ አደራ እንላለን ።

  ትናንት ለዓለም የሚበቃ ሀብት አለን ብለው ሲኩራሩ የነበሩ፥ ዛሬ ከተማቸው ወድሞ ፥ መንግሥታቸው ፈርሶ ፥ ሥርዓት አልበኝነት ነግሦባችው ይገኛል ። እሚያሳዝነው አሁንም ጦርነቱ አላበቃላቸውም ። ታዲያ ወደነዚሁ መንግሥት አልባ ወደ ሆኑት አገሮች የእኛ ወገኖች ሂደው በባርነት ሲሸጡ መታየታቸው የፊት እፍረት አይደለምን ? ልብንስ አያደማምን ? የዋልድባ አባቶች የኃማይኖት ነጻነታቸው ተገፎ ሲታሰሩ እና ሲሰቃዩ ማየትስ?የከፍተኛ ትምህርት ተቋሟት ተማሪዎች ላይ የተፈጠረውን ችግርስ? ይህን እየተመለክትንስ ዝምታና ሰላማዊ ሰልፍ ብቻ ይበቃልን ? በዚህ ጊዜ የእኔ የፖለቲካ ፕሮግራም ከዚያኛው ጋር አይስማማም ብለን የፖለቲካ ማኒፊስቶ የምናወዳድርበት ሰዓት ላይ እይደለንም ፣ ይህ ለተረጋጋና ተስፋ ላለው አገር ነው ። ኢትዮጵያ ዛሬ ከዚህ ያለፈ ፈጣንና ቅን አመለካከት ያላቸውን ዜጓቿንና ረዳት ወዳጆቿን የምትፈግልበት ወቅት ላይ ናት ። ይህ ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ የድረሱልኝ ጥሪ ነው። «ሕዝቤ ሆይ ! ስማ» ያልነውም ለዚህ ነው ። ወገኔ ሆይ ፥ ዛሬ ስማ ! ለነገ ቀጠሮ የምንደርስበት ሰዓት ላይ አይደለንም ያለነው ።

  በተለይም ለትግረኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ይህ ጊዜ አያምልጣችሁ ። የእናንተ ነን የሚሉ ጥቂት ባለሥልጣናት አያታሏችሁ ። እነርሱ የሚሄዱበት መንገድ መልካም አይደለም ፣ ዘላቂ መፍትሔም የለውም ። ይልቅስ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገናችሁ ጋር ሁናችሁ የመፍትሔው አካል ሁኑ እንላለን ።

  የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን ሆይ፥ አሁንም ወደ እውነተኛው አምላክ መጸለይ የዘወትር ሥራችን ሊሆን ይገባል ። ስለዚህም በጸሎትና በምህላ ሁናችሁ፥ እርስ በርሳችሁ እየተረዳዳችሁ ፥ በአንድነት በመቆም ፥በመተባበርና በመደማመጥ ይህን ክፉ ቀን እንድታሳልፉት በእግዚአብሔር ስም ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያቀርባል ።

  እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ከፈተና ይጠብቅልን ።

  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

  አባ ጴጥሮስ የአውስትራሊያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

Dedessa
Member
Posts: 693
Joined: 12 Sep 2016, 22:56

Re: "ሕዝቤ ሆይ ፥ ስማ!" ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የአደራ መንግስት እንዲመሰረት ጥሪ አቀረቡ። ሊቀ ጳጳሱ "ትግረኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ይህ ጊዜ አያምልጣችሁ!" ይላሉ

Post by Dedessa » 29 Dec 2017, 13:44

ትግሬን መለማመጫ ጊዜ አልፏል።

ትግሬዎች የኢትዮዽያ ጠላቶች መሆናቸውን በተግባር እየፈፀሙ ነው።

በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው በደል ደንታ የማይሰጣቸው በጥላቻ የተመረዙ ፍጥረቶች ናቸው።

Degnet
Senior Member
Posts: 19845
Joined: 16 Feb 2013, 11:48

Post by Degnet » 29 Dec 2017, 13:57

The Ethiopians will win in the end,mejemeria madreg yelebn hezbu nekat/awareness endinorew new,this is the only way,think of the Europeans of the past,especially Germany before the reformation.For the rest the rasat singer said,just survive,stay alive,kezih yebelete yenor yehon?

tolaylemo
Member
Posts: 4184
Joined: 01 Apr 2016, 19:22

Re: "ሕዝቤ ሆይ ፥ ስማ!" ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የአደራ መንግስት እንዲመሰረት ጥሪ አቀረቡ። ሊቀ ጳጳሱ "ትግረኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ይህ ጊዜ አያምልጣችሁ!" ይላሉ

Post by tolaylemo » 29 Dec 2017, 14:17

Dedessa wrote:ትግሬን መለማመጫ ጊዜ አልፏል።

ትግሬዎች የኢትዮዽያ ጠላቶች መሆናቸውን በተግባር እየፈፀሙ ነው።

በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው በደል ደንታ የማይሰጣቸው በጥላቻ የተመረዙ ፍጥረቶች ናቸው።

Ament to that !! We should intensify our campaign to isolate and expose their crimes day in day out. As we speak they are looked on with suspicion and resentment in most part of city.

Post Reply