Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Tintagu wolloye
Member
Posts: 1433
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

ህወሀት ያስፈፀመውን ግድያና ማፈናቀል ለመሸፋፈን ለግድያውና ለማፈናቀሉ የተጠቀመበትን የሱማሌ ክልል አመራርና ልዩ ሀይል ለመሸፋፈን የሀሰት ወናፍ ጋዜጠኞቹንና መገናኛ ብዙሀን እየተጠቀመ ነው( ትንታጉ ዘወሎ)

Post by Tintagu wolloye » 27 Dec 2017, 18:43

የሀውዜኑ ተውኔት ደራሲና ዳይሬክተር እንደለመደው ሀረርም ላይ ካሜራ በቅድሚያ አዘጋጅቶ የእልቂት ድራማውን እንዳይቀርፅ ገዳዩ ራሱ ሆነ።እናም ሌላ አማራጭ መጠቀም ግድ ሆነበትና በህዝብ የተተፉ፣የህዝብ አመኔታን ማጣታቸውን ራሳቸው ሳይቀር የመሰከሩ ጋዜጠኞቹንና መገናኛ ብዙሀን ከመጠቀም በቀር አማራጭ አልነበረውም። ግን ውጤቱ ያው ውግዘት፣ያው ዳውን ዳውን ወያኔ ሆኗል።የናዝሬትና የአምቦ ውሎ ይህን ይመሰክራል።

አብዲሌም ሆነ በአሻንጉሊትነት የሚጠቀምበት ህወሀት ገለልተኛ መርማሪ አይምጣብን ቢሉ፣በይፋ ስለጉዳዩ እንዳይዘገብ የውጭ ጋዜጠኞችን አትምጡብን ቢሉ ይገባናል። ጨፍጨፊና አፈናቃዩ አብዲሌ ከህወሀት ጋር በመስራት የራሱን ወገን ጭምር ሲጨፈጭፍ አለም ያውቀዋል።የሚፈፅመውን ግፍ መታዘብ አንገሽግሾት የቀረፀውን የግርፋት፣አስገድዶ መድፈርና ጅምላ ጭፍጨፋ ቪዲዮ እንደያዘ በኬኒያ በኩል፣በስዊድን ኢምባሲ እርዳታ ጉዳዩን ለአለም ይፋ ያደረገው ኢትዮጵያዊ ወንድማችን የአብድሌን ሰብእና ብቻ ሳይሆን በረዥም ሰንሰለት አስረው የገዛ ወገኑን እንዲፈጅ ያደረጉትን የእነሳማራ ኢ ሰብአዊነት የት እንደሚደርስ አሳይቶናል።

የህወሀትመሪወች ወደ ስልጣን ለመውጣት የገዛ ህዝባቸውን ሀውዜን ላይ በእዚያ መጠን ማስጨፍጨፋቸውን ያወቀ ሰው በጥዋት በማታ አትዝረፉኝ፣አታፍኑኝ፣መብቴን አትርገጡ በማለት ለራሱም ለመላው ወገኑም ሲል ገድሎ ሳይሆን ሞቶ ሊያሸንፋቸው የተነሳውን የኦሮሞ ማህበረሰብ ለመበቀልም፣ለማስፈራረትና ፀጥ እንዲል ለማድረግም በሚል አንዴ ብቻ ሳይሆን ተከታታይነት ባለው፣በታቀደና በተጠና መልኩ ይህን ያክል ግድያና ጭፍጨፋ ቢፈፅም አይገርምም።

ብሄርን ከብሄር የማጋጨት ናፋጀቱ ጉዳይ በአናሳው ህወሀት ዘንድ የመኖር ዋስትና ተደርጎ ከተወሰደ ቆየ። አማራውንና ኦሮሞውን ለማፋጀት አማራውን በጅምላ "የሚኒሊክ ሀጢአት ወራሽ" አድርጎ ከማቅረብ ባሻገር በደኖና አርሲ ላይ የግፍ ጭፍጨፋ በመፈፀም " ጨከኙ ኦሮሞ አማራን አርዶ ተበቀለ" ለማለት ደፍሯል።አፈ ሰፊ ህወሀቶች የሁለቱን ብሔረሰቦች ቅርርብና መተጋገዝ እነደ አስጊ ጉዳይ በመቁጠር "እሳትና ጭድ" ያሉበት ሁኔታ ይታወሳል።

ኦሮምኛና ሶማልኛ ከ አርባ በመቶ ያህል የሚመሳሰሉ ቋንቋወች ናቸው።ቆለኛው ሙስሊም ኦሮሞ ሶማልኛ አቀላጥፎ ይናገራል።ሶማሌውም እንዲሁ።ሀረርጌ የኢትዮጵያዊ አብሮነት ነፀብራቅ ነበረች።ሙስሊሙ ከክርስቲያኑ፣አደሬው ከሶማሌውና፣ኦሮሞው፣ዘማራውና ጉራጌው ወዘተ ማን ምንነቱ በማይለይበት ሁኔታ፣ይኖርባት ነበር።ጅጅጋ የሌለ አዲስ አበባም የለም።

አብዲሌ የጭፍጨፋው አበጋዝ መሆኑ "ለኦሮሞ ከተቆረቆራችሁ እናንተን አማሮችንም አባራለሁ" ብሎ በይፋ መናገሩን ረስቶ፣ግጭቱ በህወሀት የታቀደና በእሱ አጋፋሪነት የተፈፀመ መሆኑ እየታወቀ አጋጩ ህወሀትም ሆነ የጭፍጨፋ እቅዱን መሬት ላይ ተግባራዊ ያደረገው እሱ የዘላበዱትን ቢዘላብዱ ማንንም አያታሉ። ሶማሌም ይፈናቀል ኦሮሞ ይህ በማን ታቀደ፣በማን ተጫረ ለሚለው መልስ ፍለጋ አንዋትትም።መልሱን ይጣራ የሚለውን ጥሪ ጆሮ ዳባ ብሎ የሚያከላክለው ህወሀት እንደሆነ እናውቀዋለንና።

ህወሀት ግደል ያለውን ሲከላከል የመጀመሪያው አይደለም።ለዚህም ነው የሚታዘዝ ገዳይ፣ጨፍጫፊ እንደ አብዲሌ ያለ፣እንደ ጌዴኦ ዞን መሪወች ያለ ወዘተ ያላጣው።

የሀሰት ዘገባ በማቅረብ ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት የተሸጋገረ ከመሰለው ህወሀት አሁንም ቀብሩን አርቆ መቆፈሩ መሆኑን ይወቀው።

ህወሀት የሚደራደሩት፣የሚመካከሩት የፖለቲካ ድርጅት ሳይሆን ሀገርን ይዞ ሳይጠፋ መወገድ ያለበት የህዝብ ጠላት ነው።ህወሀት የችግሮች ሁሉ እናት ብቻ፣ሳይሆን ራሱ ችግር ነው።የሽግግር ወቅት ተሳታፊ አካል፣መፍትሄ ለማምጣት አብረውት የሚሰሩ፣ተደራዳሪ፣ታዳሽ ወዘተ ሊሆን የማይታሰብ፣ችግርና ችግር ብቻ ነው።ህወሀት የሚባለው ችግራችን መፍትሄው የዚሁ ችግር መወገድ ነው። በቃ!!

Tintagu wolloye
Member
Posts: 1433
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

Re: ህወሀት ያስፈፀመውን ግድያና ማፈናቀል ለመሸፋፈን ለግድያውና ለማፈናቀሉ የተጠቀመበትን የሱማሌ ክልል አመራርና ልዩ ሀይል ለመሸፋፈን የሀሰት ወናፍ ጋዜጠኞቹንና መገናኛ ብዙሀን እየተጠቀመ ነው( ትንታጉ ዘወሎ)

Post by Tintagu wolloye » 28 Dec 2017, 05:18

አብዲሌም ሆነ በአሻንጉሊትነት የሚጠቀምበት ህወሀት ገለልተኛ መርማሪ አይምጣብን ቢሉ፣በይፋ ስለጉዳዩ እንዳይዘገብ የውጭ ጋዜጠኞችን አትምጡብን ቢሉ ይገባናል። ጨፍጨፊና አፈናቃዩ አብዲሌ ከህወሀት ጋር በመስራት የራሱን ወገን ጭምር ሲጨፈጭፍ አለም ያውቀዋል።


Post Reply