Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Tintagu wolloye
Member
Posts: 1467
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

ለሄርማን ኮህን፣ ባለህበት!! ህወሀት አሜሪካንን ሸምግይኝ ቢል ኢትዮጵያውያን በደማቸው የጨቀየ እጁን በእርቅ የሚጨብጡት ይመስልሀል??( ትንታጉ ነኝ።)

Post by Tintagu wolloye » 25 Dec 2017, 10:16

ወደ ነገሬ ከመግባቴ በፊት ለኮህን የትዊተር መልእክት ይህን ያህል ትኩረት መሰጠቱ የተፈጠረው አንድምታ ላንሳ።አንድምታው ህወሀት ያሻውን አድርጎ በአሻው ጊዜ ነፍስ አባቱን አሜሪካን ተተግኖ ለእርቅ ሲጣራ ኢትዮጵያውያን ለእዚያ እርቅ እየተጋፉና እየተተራመሱ ይታደማሉ የሚል ነው።ህወሀት የሚባለውን ፀረ ህዝብ ድርጅት ከመሰሎቹ ጋር ብቻ እንዲሰበሰብና ሀገሪቱን እዚህ ደረጃ ያደረሰበትን ቡራኬ ፣የምንጨፈጨፍበትን ትጥቅና፣ሎጅስቲክ የሰጠ ኮህንና አሜሪካው ናቸው። ያኔውኑ የሽግግር መንግስቱ ሁሉን አቀፍ ይሁን ሲባል ያልተዋጠላቸው የህወሀት መሪወች ብቻ ሳይሆኑ ኮህንና አሜሪካው ነበሩ።

የዛሬው የከህን መዘባረቅ ህወሀትን ለማዳን ይሁን ኢትዮጵያን አልታወቀም። እኔ ካልኖርኩ ኢትዮጵያውያን በጎሳ ተከፍለው ይዋጋሉ የሚለውን የህወሀት ሟርት የሚያስታውስ ላለመሆኑ መረጃ የለም።

እያየነው ያለው እውነታ ህዝብ የህወሀት አቆራቁሶና አለያይቶ ለመግዛት ያለው ፍላጎት እንዲመክን እያደረገ፣ህወሀትን ነጥሎ አንጡራ ጠላቱ መሆኑን እየገለፀ መሆኑን ነው።ህወሀት ከህዝብ ተፃርሮ በመቆሙ፣ከራሱ ብሄረሰብና ከመሪወቹ ጥቅም በቀር ለማንም ያልቆመ መሆኑ ተጋልጧል። በስልጣን ለመቀጠል ሁሉንም መጨፍጨፍ፣ማፋጀትና ማፈናቀል ነበረበት።ይህ የተበላ ጉዳይ ሆኗል አብረውት የቆሙ ሳይቀሩ መሰሪነቱ፣ዝርፊያና ጭካኔው አቅለሽልሿቸው እየሸሹት ነው።

የተከላካይነቱ፣ህልው ሆኖ ለመቆየት መፍጨርጨሩ የህወሀት ተራ ሆኗል።ህዝብ አጥቂ፣ህወሀት ደግሞ ተከላካይ በሆነበት በዚህ ወቅት የሽምግልናው ጥሪ መዥጎድጎዱ ምንድን ነው?

የአፖርታይድ መሪወች፣ ፖልፖትና ቻወ ቸስኮ የህወሀት መሪወችን ኢምንት ወንጀል አልሰሩም። የሻርፕ ቪልም ሆነ የስዌቶ ጭፍጨፋ ከአሶሳው ጭፍጨፋ ጀምሮ እስከ እሬቻና የትናንትናው የሀረርጌ ንፁሀን ግድያ ጋር ሲነፃፀር ኢምንት ነው።የጎሳ፣ካንፖኒ ፈጥሮ ሀገርን የዘረፈ ከህወሀት ሌላ አንድም ድርጅት በአለም አይገኝም። ዝርዝሩ ረዥም ነው።

ኢትዮጵያውያን ህወሀትን ከምድረ ኢትዮጵያ ከማጥፋት በቀር ሌላ አማራጭ የላቸውም።ትግራይን ገንጥየ እዚያ እኖራለሁ የሚለው የጥንቱ ህልሙ ቅዥት ሆኗል። ይህን ቢሞክር ህወሀትን ድራሹን የሚጥፋው በእዚህ ተጎጅ የሚሆነው የትግራይ ህዝብ ነው።

እርቅ ያሉ፣ሰላም ያሉ እንደነ አበራ የማነአብ ያሉትን አስሮ ሲያንገላታ ህወሀትን እናውቀዋለን። ሁሌ የሚሞኝ ገልቱ ብቻ ነው።

ምእራቡ ፋሽስት ጣሊያን ዶጋሊ ላይ ሲመታ፣አድዋ ላይ ሲመከት " ተደራደሩ" ብቻ ሳይሆን ሊካስ ይገባዋል ሲሉ መፃፉን አልረሳነውም።ህወሀት ጋር ስለ ሰላም መነጋገር ወራሪው የጣሊያን ሀይል እስከመርዝ ጋዙ፣እስከጭፍጨፋው በገዥነት እንዲቆይ፣ስልጣን ተካፍሎ እንዲኖር የመመኘት ያህል ነው።

ለህወሀት የሚሆን ፍርፋሪ ይቅርታ የለንምና ኮህን ሆይ፣አትልፋ።በህወሀት መውደቅ ወይም በእሱ ጦስ የሚነሳ፣ቀጭ እግው ቢኖር መፈታቱ የጊዜ ጉዳይ ነው።

Tintagu wolloye
Member
Posts: 1467
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

Re: ለሄርማን ኮህን፣ ባለህበት!! ህወሀት አሜሪካንን ሸምግይኝ ቢል ኢትዮጵያውያን በደማቸው የጨቀየ እጁን በእርቅ የሚጨብጡት ይመስልሀል??( ትንታጉ ነኝ።)

Post by Tintagu wolloye » 26 Dec 2017, 04:29

All of the criminals that neither been identified and expossed to the public nor saw a court of justice shall experience that.Unless,killing in inpunity will continue.

The TPLF leaders are stained by the blood of inocent people to the bones.Their rightfull place is the International Criminal Court and not a round board of dialogue.

Post Reply