Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Tintagu wolloye
Member
Posts: 1467
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

ኦህዲድና ብአዴን ከሌሎች ተቃዋሚወች ጋር ጠንካራ ግምባር መፍጠር አለባቸው።(ትንታጉ ዘወሎ)

Post by Tintagu wolloye » 23 Dec 2017, 01:38

ህወሀት የሀገሪቱን ፖለቲካ እግር ተወርች ጠፍሮ በማሰርና የለየለት የጎሳ ጦርነት በማስነሳት ሀገሪቱን ወደማትወጣበት አዘቅት እየከተታት መሆኑ እየታየ ነው።በአንድ በኩል ተቃዋሚው ጥሪና መግለጫ ከማንጋጋት በቀር ሀገሪቱ ከተደቀነባት አደጋ የሚመጣጠን የተጨበጠ ተግል በሁሉም መስክ ሲያደርግ አይታይም። ህዝቡ ይታገላል፣መስዋእትነት ይከፍላል ወዘተ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፈራ፣ተባ እያሉም ቢሆን ህወሀትን መሞገት የያዙት ኦህዲድና ብአዴን ህወሀት ጋር በአንድ አዳራሽ ተቀምጦ ጉንጭ አልፋ ውይይት ከማድረግ ያለፈ፣ይህ ወይም ያ ለምን ተደረገ/ አልተደረገ ከማለት የዘለለ እርምጃ ሲወስዱ አልታዩም።ህወሀት ወታደራዊ ሀይሉን ከመጠቀም የማይቦዝን፣ግደሉና አፈናቅሉ ብሎ ትእዛዝ የሰጣቸውን ነፍሰ ገዳዮቹን እስከመጨረሻው ለመከላከል የቆረጠና ከሀገር በፊት የፖለቲካ ስልጣኑን የሚያስቀድም መሆኑን የተረዱ አይመስሉም።የህወሀት መሪወች እጃቸው በደም የጨቀየ፣በሙስና የተጨማለቁ ወደፊት ሀገሪቱና ህዝቧ ለፍርድ የምትፈልጋቸው ወንጀለኞች መሆናቸውን የተረዱና ከእነዚህ እኩያን መራቂያው ጊዜ አሁን መሆኑን ያጤኑትም አይመስልም። ከእነዚህ የህወሀት ቁንጮወች ራስን ማራቅ ብቻ ሳይሆን በቅርብ ርቀት የሚያውቁትን ወነጀልና ግፍ ለህዝብ ይፋ አድርጎ የፍርድ ቀናቸውን ማፋጠንም እንደሚያሻ ሊገነዘቡ በተገባ ነበር።

ፖለቲካውን ቆልፎ ይዞ ሀገሪቱን ወደ ማጥ እየገፋት ያለው ህወሀት ሊመከር፣ ሊዘከር፣ሊስተካከልና ዳግም አጋር ሊሆን የሚችል ድርጅት አለመሆኑን ብቻ ሳይሆን ይዞ የሚሞት፣አብረውት ውለው ባደሩበት ሰአትና ቀን መጠን በህዝብ እንዲጠሉና በጠላትነት እንዲፈረጁ እንደሚያደርጋቸው ኦህዲድና ብአዴን መገንዘብ አለባቸው። ኦህዲድና ብአዴን ህወሀት እንደለመደው ሁሉንም እኔ ልወስን ሲል፣እንዳሻኝ ልግደል ላፈናቅል ሲል ይህን አሜን ብሎ ተቀብሎ ላለመቀጠል መወሰናቸው ገና ነጥሮ አልወጣም።ህብረትና መናበብ አለ ቢባልም ይህን መልክ የሚያስይዝ ግልፅ መዋቅር የለም። በፀረ ህወሀትነት ደረጃም ቢሆን ብአዴን ብዙ የሚቀረው መሆኑ አረየታየ ነው።ለምሳሌ ኦህዲድ የሰራዊቱ መኖሪያ ካምፕ እንጅ ካምፓስ ወይም መንደር አይደለም ሲል ብአዴን መርሳ፣ኡርጌሳና ውጫሌን በመሳሰሉት የህወሀት ጦር መፈንጫ ሲሆን አግድሞ እያየ ነው። ኦህዲድ ንፁሀንን ከአጋዚ እንዲከላከል ለፖሊስና ፈጥኖ ደራሹ ግልፅ ትእዛዝ ሰጥቷል።ብአዴን የክልሉ ፖሊስ ከአጋዚ መንጋ ጋር አብሮ ሲጨፈጭፍ አግድሞ ያያል።

ህዝብ እቅጩን ተናግሯል።ህወሀት የሚባል ነፍሰ ገዳይ ድርጅት ከእንግዲህ ላይገዛው ወስኗል።የኦህዲድና ብአዴን ሚና እነሱን ሽፋን አድርጎ ህዝብን የሚፈጅ የሚያፈናቅለውን ህወሀትን ከእነሱ በመነጠልና ወንጀሉ የህወሀትና የህወሀት ብቻ መሆኑን በማጋለጥ መቋጨት የለበትም። 26 አመት የደፈነው ግፍና በደል እንዳይቀጥል ግፈኛው መወገድ አለበትና ሰልፋቸው ከህዝብ ጋር መሆኑን የህዝብን ጥሪ በማስተጋባት ( የስርአት ለውጥ አሁኑኑ የሚለውን) ብቻ ሳይወሰን የስርአት ለውጥ ለሚያመጣ የሽግግር መድረክ እንዲኖር ተጨባጭ እርምጃ በመውሰድ ከህወሀት አገዛዝ በኋላ ለምትመሰረተው ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ግንባታ ከሌሎች ዲሞክራሲያዊ ሀይሎች ጋር መስራት ይጠበቅባቸዋል። የሀገሪቱ ችግር ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ መፍትሄ የመስጫው ጊዜ አሁን ነው

ህወሀት መወገድ ያለበት የሀገርና የህዝብ ጠላት እንጅ አብረውት የሚወያዩት ድርጅት አለመሆኑ ግልፅ መሆን አለበት። ግምገማ በሚለው ጉንጭ አልፋ ንትርክ በመጠመድ ለህዝብ ጠብ የሚል መፍትሄ አይመጣም።

ከኑግ ጋር የተገኘ ሰሊጥ ላለመሆን ከኑጉ መለየት ያስፈልጋል።ህውሀትን እስከ አጥንቱ በዘለቀ ምሬት የጠላውና ይህን እኩይ ድርጅት ሊያወድመው የተነሳው ህዝብ ከህወሀት ጋር ሆኖ የሚያጠቃውን አይታገስም። ስለዚህ ኦህዲድና ብአዴን ኢህአዲግ ከሚባለው እስር ቤት ወጥተው ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመነጋገር የሀገሪቱን የወደፊት እጣ፣ፋንታ ፈር በማስያዝ ረገድ ሚና እንዲኖራቸው፣ከህወሀት ቁጥጥርና ተፅእኖ ውጭ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ሆነው መቀጠል መቻላቸውን ማረጋገጥና ማሳየት ያሻቸዋል።ህወሀት ከእንግዲህ ለእነሱ ሸክም (burden) ነው።ይዟቸው ሳይጠፋ፣ ጦሱ እንዳይተርፋቸው ከእነጦሱ በህዝብ ተመትቶ የሚጠፋበትን ሂደት ማፋጠንና ራሳቸውን የአይቀሬው ለውጥ አካል ለማድረግ ተጨባጭ እርምጃ፣መውሰድ አለባቸው።
Last edited by Tintagu wolloye on 24 Dec 2017, 11:42, edited 2 times in total.

Tintagu wolloye
Member
Posts: 1467
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

Re: ኦህዲድና ብአዴን ከፀረ ህዝቡ ህወሀት ጋር ያቆራኛቸውን " ኢህአዲግ" የተሰኘ ድርጅት ማፍረስና ከሌሎች ተቃዋሚወች ጋር ጠንካራ ግምባር መፍጠር አለባቸው።(ትንታጉ ዘወሎ)

Post by Tintagu wolloye » 23 Dec 2017, 08:17

The risk of being irrelevat in the politics of the country is eminent. Time is runing out and the Ethiopian public has neither time nor reason to wait. Time to dump the TPLF and join the people.

Tintagu wolloye
Member
Posts: 1467
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

Re:

Post by Tintagu wolloye » 24 Dec 2017, 03:21

The risk of being irrelevat in the politics of the country is eminent. Time is runing out and the Ethiopian public has neither time nor reason to wait. Time to dump the TPLF and join the people.

Post Reply