Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Tintagu wolloye
Member
Posts: 1433
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

ሰሞነኛ ቀልድ.የኢህአዲግ መጨረሻ ግብ ( ትንታጉ ዘወሎ)

Post by Tintagu wolloye » 22 Dec 2017, 08:42

ጓደኛሞች እየጠጡ ይጫወታሉ።

" እ እኔ እምለው? ግን በቃ ተወው!!"

"ኧረ ረ ረ! በቃ እንደ መብራት ሀይል፣እንደ ቦኖ ውሸ— —ወሬ ብልጭ ድርግም፣ስልም ብልጭ እያደረግህ ልብ መስቀል ጀመርክ?"

"አንተኮ ነህ ’ኢትዮጵያና ፖለቲካ ትዝ የሚሉህ የቀመስክ ጊዜ ነው’ ትለኛለህ።አሸማቀቅከኛ!! "

" ኦኮ ፈታ በልና ወደጉዳዪ ግባ"

" ስብሀት "የኢህአዲግ የመጨረሻ ግብ መጥፋት ነው" ያለው ምን ለማለት ፈልጎ ነው?"

" እኔ በምን አባ አውቃለዋለሁና ታፋጥጠኛለህ። ታይቶት ይሆናላ!"

"ምኑ?"

" መጥፋቱ ነዋ! በእዚህ አያያዛቸው ማን ያኖራቸዋል! በጧት በማታ ዳውን ዳውን ወያኔ!!ወያኔ አይገዛንም!!!——ነው መፈክሩ"

"ኖኖኖኖ! ያለውኮ "ያጠፉናል" አይደለም "አላማችን መጥፋት ነው" ነው። አይገባህም?"

" ያው ነው! ዋናው አላማቸው የሚያጠፋ መሆኑ፣የሚያጠፋቸው መሆኑ ነው።"

"እኔ ግን አልመሰለኝም።"

" ታዲያ ምን ማለት ሊሆን ይችላል?"

"ወደየውጭ ሀገር ባንክ ያስኮበለሉትን ሀብት ፍለጋ የመኮብለላቸው ነገርስ? ህወሀት ከኤስ ኤስና አንጡራ ናዚወች ተግባር ለመማር የማይችል ደንቆሮ ይመስልሀል?"

" እንዴ እዚህ ያለውስ ሀብታቸው? ሜቴክ! ኤፈርት! ፎቁና ፋብሪካው?"

" ከነፍስ ይበልጣል? ህወሀት ከደርግ ስህተት ተምሯል መባሉ ስልጣን ሱያጡ ከርቸሌ መከተም ወይም ባዶ እጅ መቅረት መኖሩን አያካትትም?"

" እሱስ——። "

" ፓርቲ ስልጣን ሲለቅ ዳግም ለመያዝ ይጥራል እንጅ ራሱን አያጠፋም።ህወሀት ያጣውን ሰልጣን ዳግመኛ አያገኘውም።የተተፋ፣ራሱና እንጥሉ ላይ ከገማ አመታት ያለፉት ድርጅት ነው። የስብሀት እንጠፋለን ትንቢት በቁምጣ መጥቶ ከዘረፈውና ከሀገር ካሸሸው ሀብት ጋር ይያያዛል።ገባህ?"

" እ?"

" ተመልከቱት!! አይንና ህሊናውን ዳሌ ላይ ሲተክል! ቁም ነገሩን ትቶ!!!"

" እናቴ! ይሄ ዳሌ በኢንቨስመንት የዳበረ ነው።የተረፈን እንደሉካንዳ ስጋ አሻግረን ማየት ነው።አታይም? ሂዳኮ ከባለማደያው ሽሜ፣ወዲ ማነው የሚሉት፣ሂዳ ስትታዘለው!! በሞቀ ብር የበደነ ገላ እንዲህ ይሞቃል!!ምነው መጥፋታቸው ካልቀረ ባፈጠኑትና......!!

" ዶሮ ብታልም ጥሬዋን! አለ?"

"ማለምም ተከለከለ እንዴ? ህልሙ ሁሉ በመለስ ራእይ ተካቷልና ከህልም ነፃ ናችሁ ተባለ?"

" ከሀብት ነፃ ከወጣህ አይበቃም! ህልሙንማ ቤት አከራይህ፣የመስሪያቤት አለቃህ፣የኑሮ ውድነቱ በቅዠት መንዝረውታል።"

" ተወኝ እባክህ! ከዚህ ኑሮስ ምናለ እኔም ብን ብየ በጠፋሁ!!"

"ሳላውቅ ሰርቀህ ውጭ የላከው ዶላር አለህ እንዴ?ከመጥፋትህ በፊት ቢሉን ክፈል!! ሆ ሆ!