Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Tintagu wolloye
Member
Posts: 1351
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

ያበጠው ይፈንዳ!!ኢትዮጵያ ውስጥ የጎሳ መደብ አለ!!ወርቅና ወርቅ ያልሆነ ብሄረሰብ አለ!!ኢትዮጵያ ውስጥ ለወርቁ ብሄረሰብ ማቀፊያ ያልሆነ ሁሉ ከሌላው ጋር እንዲጋጭ ተደርጎ ወርቁ ማን እንደሆነ እንዲያውቅ ይደረጋል።ኢትዮጵያውያን ህወሓትን ማኖር፣ኢትዮጵያም ለትግራይ መኖር ሲያቅታቸው በህወሓት ይሰዋሉ።(ትንታጉ ነኝ)

Post by Tintagu wolloye » 22 Dec 2017, 08:00

XXX
ኢትዮጵያ ውስጥ የጎሳ መደብ አለ!!ኢትዮጵያ ውስጥ ወርቅና ወርቅ ያልሆነ ብሄረሰብ አለ!!ኢትዮጵያ ውስጥ ለወርቁ ብሄረሰብ ማቀፊያ ያልሆነ ሁሉ ከሌላው ጋር እንዲጋጭ ተደርጎ ወርቁ ማን እንደሆነ እንዲያውቅ፣አምኖ እንዲቀበልና ተገዶ እንዲገዛ ይደረጋል።ወርቁ ወርቅ ሆኖ የማይቀጥል ከሆነ፣ወርቁ አቃፊ ደጋፊ የለኝም ብሎ ያመነ ቀን ሁሉም እንዲበታተን፣ኢትዮጵያም እንደ ሀገር የመኖር ሕልውናዋ እንዲያበቃለት ይደረጋል። ይህን ባጭሩ ላስረዳ።

ስለመደብ ሳነሳ ማለት የፈለግሁት ርእዮተ አለሙን፣ኢኮኖሚውን፣ፓለቲካውን፣ወታደራዊና የደህንነት ተቋሙን ወዘተ በመቆጣጠር ረገድ ላይ መሬት የያዘው ማን ነው የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ነው።

በአሁኒቷ ኢትዮጵያ በብሄረሰብ ስለመደራጀት፣ ስለጎሳ ክፍፍል በጎነት፣ በአጠቃላይ ስለአብዮታዊ ዲሞክራሲ ያልገባው ወይም በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ያልተጠመቀ ያላመነ ——ወታደር ሆነ ሲቪል ካምፕ ገብቶም ሆነ ታስሮ ዳግም እንዲማረው፣እንዲጠመቅ ይደረጋል። ያላመነ ደግሞ ትምክህተኛ ተሰኝቶ፣የድሮው ስርአት ናፋቂ ተብሎ ከመወገዝ እስከ እስርና ሞት የሚደርስ ቅጣት ይደርስበታል።ለግለሰባዊ ነፃነት ቦታ የለም። በሙያ መደራጀት፣በፆታ መደራጀት ብሎ ነገር የለም።ፆታም ሆነ ሞያ ጎሳን መነሻ ማድረግ ይገባዋል። ያማራ ሴት፣የኦሮሞ መምህር እንጂ ዝም ብሎ ሴት፣ዝም ብሎ መምህር መሆን አይቻልም።

የጎሳ ሩጫ፣ የጎሳ እግር ኳስ ይፈቀዳል።ትግሬ አማራ በአስር ሺህ ረታ፣ኦሮሞ በማራቶን ሜዳልያ ወሰደ መባል የተለመደ ነው።በእግር ኳስ አማራና ትግሬ ገጥመው በቲፎዞ መካከል ግጭት ሲደርስ ግጭቱ ወደ ጎሳ አዘል ግጭት መሸጋገሩ ለህወሀት ምንም ማለት አይደለም።በእስፓርት ብቻ ሳይሆን በአየር ንብረት እወጃ ጎሳና ጎጥ አለ።አማራ ሲዘንብ ሶማሌ ፀሀያማ ይሆናል፤ትግሬ ሲጨግግ ኦሮሞ ያካፋል——የለመድነው ዜና ነው።በባህል ረገድ ህወሀት ከባንዲራ እስከቢራ የሚያስተዋውቅባቸው የአይዶል ዝግጅቶችና ፊልሞች፤ተፅዕኖ ለመፍጠር በአብዮታዊ ዲሞክራሲ የታነፁት እንደነ ፍርያት የማነ፣እንደ ሚስ ትግራይ ዳግማዊዋ ሰላም ተስፋየ፣የሬዲዮ ፋናው አንድ ሸረፍ ነፃነት ወርቅነህና ስርአት በተለወጠ ቁጥር ቆዳቸውን ሸልቅቀው አዲስ የሚመስሉት እንደነ ጌትነት እንየውና ሰራዊት ፍቅሬ ያሉ ሞልተዋል።በመቶ ሚሊዮን ብር በሚሰላ ወጭ የሚዘጋጀው የብሄረሰቦች ቀንም ግቡ ያው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ከፋፍለህ በትን ነው።በእየ ትምህርት ቤቱ፣ እየ መስሪያ ቤቱ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ይሰበካል። በእየመንግስት መስሪያቤቱ ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ በቀር ሌላ አይነት፣ሶሻል ይሁን ሊብራል ዲሞክራሲ ዝር፣አይልም።መንግስት እየከፈላችሁ የመንግስት ያልሆነ አመለካከትም ሆነ ፖሊሲ ሊኖራችሁ አይችልም ይሉናል፣ህወሀቶች።ደመወዝ መክፈላቸው እንደገዙን እንዲቆጥሩን አድርጓቸዋል። የተገዛ እቃ ደግሞ ገዥው እንዳረገው ከመሆን ምርጫ የለውም!!

ህወሓት አነሳሱ ከትግራይ ለትግራይ መሆኑን አስረግጨ ለመነሳት እፈልጋለሁ።ይህ ቡድን ከማገብት እስከ ተሀህት፣ከተሃህት እስከ ህወሓት ከዚያም ኢህአዴግ ብሎ በአሽከሮቹ ለመታጀብ እስከበቃብት ድረስ አላማው አልተለወጠም፣አይለወጥምም። ሲነሳ ለትግራይ ሀገርነትና ለኢትዮጵያ መበታተን አልሞ ነው።ይህ ልክ በኦነግ በኩል ሲገፋበት እንደምንሰማው ኢትዮጵያ ሳትበተን ትግራይ ነጻ ሀገር ስለማትሆን፣ሁለቱ በአንድ ላይ ስለማይቀጥሉ ከጥንቱ ከጧቱ ጀምሮ ለኢትዮጵያ ጥፋት፣ ለትግራይ አገርነት የኢኮኖሚ፣ወታደራዊ፣ፖለቲካና የመልከአምድር መሰረት እየተጣለ አሁን ካለበት ደርሷል።

ህወሓት አዲስ አበባ ሳይገባ ነው መሰረትና እቅዱ የተጣለው።የዚያ አርክቴክት ደግሞ መለስ ነው።ህወሓት በወታደራዊ ኃይል ስልጣን ላይ ከመውጣቱ በፊትና ማግስት ከሻዕቢያ ያጣላውን የሀገር ዘረፋ ተግባር ጀመረ።በአንድ በኩል ስልጣኑን እያደላደለ በሌላ በኩል የሀገሪቱን ኢኮኖሚ የሚቆጣጠርበትን የኢኮኖሚ ተቅዋማት አጠናከረ። በቁምጣ አዲስ አበባ የገባው የህወሓት አንጋች ሁሉ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ ባለ ፎቅ፣ ባለ መካናይዝድ እርሻ፣ ባለ ድርጅት የሆነው ዝም ብሎ አይደለም።ዛሬ ስለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማውራት አይቻልም፣ የሚቻለው ስለእኔ ኢፈርት፣ ስለኔ ማረት ነው።የህወሓት ባለስልጣናት ሚኒስትሮችም፣ የህወሓት የኢኮኖሚ ተቅዋማት ማናጀሮችም ናቸው።በሚንስትርነት ያወቁትን የሀገር ሚስጥርና መልከአ ምድራዊ የሀብት ስርጭት ለሚመሯቸው የህወሀት የኢኮኖሚ ተቅዋማት ያውሉታል።ከባንክ ብድር ያወጣሉ፣የወጣው ገንዘብ ለህወሓት ተቅዋሞችና በግለሰብ ስም ድርጅት ለተከፈተላቸው የትግራይ ተወላጆችና በሽፋን በድብቅ ለምያሰሯችውና በሌላ ብሄረሰብ ተወላጅ
"ይዞታ" ያሉ በሚመስሉ የንግድ ተቋሞች እንዲሰጥ ይወስናሉ።

መሬት የመቀማቱ፣ሌላውን የማፈናቀሉ ተግባርም የዚሁ አካል ነው።ትግራይ የሰፋች ጊዜ መሬቱ የተቀማው ወሎዬ፣ጎንደሬና አፋር ቁጭቱ ገና አልበረደም። ኮረም ላይ ልጆቹ አማርኛ ለምን ተናገራችሁ ተብለው ሲከሰሱ፣ወልቃይቴው አገሩን ለቆ እንዲሰደድና ልጆቹ "ክብ ሰርታችሁ ትግርኛ ጨፈራ ተማሩ " ሲባሉ፣ አፋሩ ጨው አታውጣ ሲባል የበደሉ ቅጥያ እንጂ ሌላ አልነበረም። መለስ ለቢቢሲ ጋዜጠኛ በኩራት የተናገረው የአዷና የአክሱም ሰው በገፍ ተጋግዞ ወልቃይት መስፈሩም ሆነ የሁመራና የማይካድራ ለም መሬት ለህወሓት የቀድሞ ታጋዮች ካሳ ጭምር መሰጠቱ ከህወሓት አላማ አንጻር የሚጠበቅ ነበር። በቅርቡ በቤንሻንጉል በሽወች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ከትግራይ ተጋግዘው መስፈራችውን ከዚያው ክልል በግፍ ከተፈናቀሉት አማራ ገበሬወች ጋር አነጻጽሮ ማየት አይቻልም።ወቅና ወርቅ ያልሆነ አይወዳደርማ!በጋምቤላ የሚደረገው የመሬት ወረራም ሆነ በአዲስ አበባ ዙርያ የሚደረገው የመሬት ነጠቃ አያስገርምም።የህወሓት ሕልም ኢትዮጵያ ለትግራይ መኖር እስክያቅታት ድረስ፣ሌላው ብሄረሰብ በህወሓት አልገዛም ብሎ ይምያምፅበት ሁኔታ እስኪደርስ ድረስ ይቀጥላል።

ወታደራዊና የደህንነት ተቋሙ የህወሀት ነው።የህወሀት አገር አፍራሽ ጀግኖች፣ የሞቱም ሆነ ያሉ ባአዛዥ ብቻ፣ሳይሆኑ ባለሀውልት ናቸው። ጃታኒ አሊንና አፈወርቅ አለምሰገድን ናይሮቢ/ ቲካ ያስገደኘው ሀየሎም ባለ ሀውልት፣ሀረርጌ ከቶ የሶማሌን ክልል በቅኝ አዙር የገዛውና ሰው በላውን የክልሉ መሪ የሰራው ሳሞራ ባለ ሀውልት——ናቸው።

ዛሬ ስለትግራይ ኢትዮጵያነት ማውራት ቀልድ ነው። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሆና የምትኖረው ለትግራይ መኖር የምትችል ከሆነ ነው።ኢትዮጵያ ይህን የማትችል ከሆነ ፣ሌላው ብሄረሰብም ወርቁን የትግራይ ብሔረሰአብ በጫንቃዬ መሸከም በቃኝ የማለት አዝማሚያ ካሳየ አንድም ተነጥሎ በደል ይደርስበታል፣ጌታው፣ጋዢው ህወሓት መሆኑን አምኖ እስኪቀበል ድረስ ይታሻል። አለያም ከሌላው ጋር ደም እንዲቃባ ተደርጎ ሕልውናው በህወሓት መኖር ላይ የተመሰረተ እንድመስለው፣ህወሓት የኑሮው ዋስትና፣ የመኖሩ ኢንሹራንስ እንድመስለው ይደረጋል።

ይህ በመጀመሪያ በአማራና ጉራጌ ብሔረሰቦች ላይ ተፈጽሟል።ግፉ ባይቅዋረጥም የግፉ ተካፋይ ቁጥር ግን ጨምሯል።በጭቁን ብሔረሰብነት ፈርጆ የተስፋ ዳቦ ሲያስገምጣቸው የነበሩት ዛሬ የደም አበል እየከፈሉ ነው።ጉራጌውና አማራው በየስፍራው ሲፈናቀል ተባባሪ አፈናቃይ ጭምር የነበረው ሁሉ ተራ ደርሶታል።

ህወሓት የኢትዮጵያን መበተን እርሾ ሲበጠብጥ "ኢትዮጵያዊ ብሔር ብሔረሰቦች አይዋደዱም" ሲል ለካድረወቹ አስተምሯል።"ዘይምዋደድውን " ሲል የጻፈውና ያስተማረው መለስ ያኔ አደለም ሁሉንም ብሄረሰብ 15 ያህሉን በስም ትራ ቢባል እንክዋ አያውቅም ነበር።ሌላው ቀርቶ ቆምቁላት በሚለው ትግራይ ያሉትን የተለያዩ ብሔረሰቦች ቅዋንቅዋና ባህል፣የግንኙነት መስተጋብር ሊያውቅ የሚችልበት ሁኔታ አልነበረም።"አክሱም ለትግሬው እንጅ ለወላይታው ምኑ ነው" ባዩ መለስ የአክሱም ሃውልት ሲቆም በቦታው ትግርኛ ተናጋሪ ያልነበረ መሆኑን ያውቃል ማለት አይቻልም።ሁሉን አውቃለሁ ባይነቱ ግን ሚኒስትር ተሁኖ እንክዋ መሳት የሌለበትን አስቶታል።

ዛሬ ሶማሌና ኦሮሞ እንዲፋጅ የህወሓት ፈቃዱ ቢሆን አንድም ኦሮሞ መሬቴን ፣መብቴን በማለቱ ለመቅጣት፣ህወሓት ካልኖረ ሶማሌ እንደሚፈጀው እንዲያውቅ ለማድረግ የታለም እኩይ ተግባር ነው።ለዚህ ነው እኔ አባይ ጸሃየ ሩዋንዳን እየጠቀሱ የምያስፈራሩት። ግጭቱን ፈጣሪም ጨፍጫፍ አስጨፍጫፊም እነሱ ናቸው።ምክንያቱም ግቡም ያው ነው።

አማራን መጨፍጨፍና ማሳደድ ብቻ ሳይሆን ማሳጣትም የሚያውቅበት ህወሓት የወርቁ ጎሳ አባላት ጎንደርና ጎጃም "ጥቃት እንዳይደርስባቸው " አማራ በከፈለው ግብር ደመወዝ የምቆረትላቸው ያማራ ወታደሮች ለትግሬዎቹ ዋርድያ እንዲቆሙ፣ አማራ ፖሊሶች ትግሬወችን ከአማራ ጥቃት እንዲያድኑ፣ እንዲጠብቅዋቸው ተደርገዋል።በሕዋሃት ትእዛዝ አገር ለቀው ሱዳን እንዲገቡ የተደረጉ ትግሬወች በአውሮፕላን ትግዋጉዘው መቀሌ መግባት ብቻ ሳይሆን ከሶማሌ ክልል ያዕርዳታ ልገሳ ተደረገላቸው የሚል አስቂኝ ግን እኩይ ዜናም ሰምተናል።ዛሬ የሱማለው ምንሻ መሪ ከትግራይ በቀር ሌላው ካጠገቤ አልቆመም ቢል ምናልባት ድሮ የሰጠው ገንዘብ ተመላሽ እንዲሆን ፈልጎ ባይመለስለትም በሱና በህወሓት መካከል ያለውን ትስስር ያሳያል።

ሁሉም ለትግራይ ተወላጆች ሲሆን፣ሁሉም ለትግራይ ተወላጆች ሲባል የገዢና ተገዥ ብሄር መኖር ፍንትው ብሎ ይታያል።ገዥው መደብ ብሄረተኛ መሆኑ ግልፅ ቢሆንም አልፎ ተርፎ የለየለት የመደብ አቋም ይኖረዋል ብሎ ያሰበ አልነበረም።ይህ፣ያለምክንያት አይደለም።ሁሌም የወያኔ ክስ"የአማራ፣የገዥ መደብ——ነበርና ራሱ የትግሬ የገዥ መደብ ያቋቁማል ያለ፣የጠረጠረ አልነበረም። አማራ እንደብሄር መግዛቱን ወይም አማራ የሆኑ ብቻ ተመርጠው በመንግስት ወጭ ባለመካናይዝድ እርሻ፣ ባለፋብሪካ፣ባለ ሪለደ ኢስቴት——የሆኑበትን ዘመን ባላስታውስም የዛሬውን አይነደ ሀያወጣ፣የትግሬ ብሄር የመደብ የበላይነት መኖር ግን በማስረጃ እመሰክራለሁ።የመለስ 5 ሚሊየን ዶላር በባንክ ኦፍ አሜሪካ ለስምሀል በስሟ ቢያስገባ ምናልባት ንጉሱ ከአሸሹትና ኋላ ለዘር ማንዘራቸው ከሆነው የኢትዮጵያ፣ህዝብ ሀብት ጋር ሊነፃፀር ይችላል። ግን አንድ ሙሉ ብሄር ይህን ያህል ሲገዛና ሲነዳ " ምርጥ ምርጡን ለትግሬወች" አይነት ይሆንና የብሄር የመደብ አለ ለማሰኘት ያስደፍራል።

ዛሬ ግማሽ ሚልዮን ኦሮሞ ወገኖቻችን ሲፈናቀሉ ህወሓት ጉዳዩ ባይሆን የችግሩ እንጂ የመፍትሄው ባለቤት ስላልሆነ አያስገርምም።ይህ የሆነው በትግራይ ተወላጆች ላይ ቢሆን አውሮፕላን ማሰለፍ ሳይሆን ጥቃት አደረሱ በተባሉት ላይ የነርቭ ጋዝ በነሰነሰ ነበር። ወርቅና ወርቅ ያልሆነ ማለት ይሄ ነው። እንዲፈናቀሉ ማድረግ የተፈናቀሉት እርዳታ እንዳያገኙ ከማድረጉ ጋራ የተያያዘ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ገዢ መደብ መኖሩ ብቻ ሳይሆን ገዢው መደብ ከአንድ ብሄረሰብ የመጣ ነው።ይህ ማለት ብሄረሰቡ እንዳለ ገዢ ሆኗል ሳይሆን ከእዚያ ብሄረሰብ የመጡ ተለይተው የፖለቲካ፣ የወታደራዊ፣የኢኮኖሚ፣የባህል ወዘተ ተጽዕኖ ባለበት ሆነዋል ማለት ነው።ከመሬት ተነስቶ ሚሊዮነር አይኮንም።ከጎጆ ወጥቶ ባለሰባት ፎቅ ባለቤት መሆን ተዓምር ካልሆነ አይቻልም።በህወሓት ሁሉም ተአምር ይሆናልና ሆኖላቸዋል።ነገሩ ይህ ሁሉ የሆነው ሌላው ተጨፍጭፎ ፣ተዘርፎ፣ተፈናቅሎ፣ተሰዶና ተሳድዶ መሆኑ ነው ክፋቱ።ምላሹን ታሪክ ያሳየናል።

ምኞት አይከለከልም።ተቃዋሚው ልቦና ስጥቶት በአንድ ተሰልፎ ብታገል ብዙ ጥፋት ያስቀራል።አለበለዚያ ህወሓት በሕዝብ አመጽ ተገፍቶ መግዛት ተስኖኛል ባለ ማግስት፣ኢትዮጵያ ለትግራይ መኖር አቅቷጣል ብሎ በደመደመ ጊዜ እንደ ሶማሌ ክልል መሪ አይነት ሰው በላወችን በአንድ በኩል አሰማርቶ ህዝብን እያባላ በሌላ በኩል የዘረፈውን ዘርፎ፣ትግራይን ወደውጭ ጭምር እየላከ ባሰለተነው፣እስካፍንጫው ባስታተቀውና ሌላውን አጋፍጦ እያስገደለና እያጋደለ በቆጠበው "ተጋዳላይ" መንጋ ትግራይን ያጥራል።


Post Reply