Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Tintagu wolloye
Member
Posts: 1467
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

ህወሓት ላይ አመጽ በተነሳ ቁጥር ከአጋዚ ጦር ባልተናነሰ ፍጥነት ህወሃትን ሊታደጉ የሚሯሯጡት “የሀገር ሽማግሌና የሃይማኖት አባት” ተብየወች ሰልፋቸው ከማን ጋር ነው?የሀገራችንን የሽምገላ እሴት ለፀረ ሀገርና ፀረ ህዝብ ቡድን ጥቅም ማዋልስ ተገቢ ነወይ? (ትንታጉ ዘወሎ)

Post by Tintagu wolloye » 22 Dec 2017, 06:59

ፓለቲካው በሀይማኖት ተቅዋማትና መሪወች በኩል ወደ ሕዝብ ደርሶ የተፈለገውን ነገር ለህወሓት እንዲያስገኙ ሲደረግ አመታት ተቆጥረዋል።የሃይማኖት ነጻነት እንደሌሎቹ ነጻነቶች ሁሉ የተነፈገ በመሆኑ የሃይማኖት አባቶች የእግዚአብሔር መንግስት ሳይሆን አራት ኪሎ ቤተመንግስት በመሳሪያ ኃይል የገቡ ሹማምንት ተሽዋሚወች ከሆኑ ወዲህ ተጠሪነታቸው ለፈታርና ለምመናኑ/ሙእሚኑ መሆኑ ቀርቶ ለህወሓት ሆኗል።እነዚህ ነጭም ጥቁርም የጠመጠሙና አስረዝመው የለበሱ የህወሓት ካድሬወች ከቁርአኑና መጸሐፍ ቅዱሱ ቃል ይልቅ የወያኔ ዘረኛ ፖለቲካ አጥንታቸውን ዘልቆ የገባ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩሎች ናቸው። ህወሓትን የጠላ ጠላታቸው፣ለሃይማኖቱ በጽናት የቆመ ደመናቸው ነው።

እነዚህ ካባ ደራቢ ካድሬወች ህወሓት ችግር ሲገጥመው ዝጉርጉር ከለበሰው አጋዚ ጦር እኩል በቦታው ይገኛሉ። “መስቀል ይውጣ፣የሀገር ሽማግሌ ይሰብሰብ” ይሉና ደህንነቱና የአጋዚ ጦር የተቃውሞውን መሪወች፣የተቃውሞውን ወርድና ስፋት እንዲያጠና ፋታ ይሰጣሉ።ወዲያው እርቁ ሳይወርድ ቄሱና መስቀሉ ይመለስና የህዝብ ልጆች ለሞትና ለእስር ይዳረጋሉ። እረቻ ላይ ሰው ሲያልቅ፣ሕዝብ ስፈናቀልና ህወሓት በጫረው የጎሳ ግጭት ሲተላለቅ አንድም ጊዜ በመንግስት ላይ የሰላ ሂስ ሲሰነዝሩ የማናውቃቸው ጳጳሳትና ሙፍቲወች ህወሓት ጭንቅ ላይ ሲሆን ጉባዔ መቀመጥ፣ህወሓት ገማሁ ብሎ “ግምገማ” ሲቀመጥ እነሱም እንደ ካድሬ መጠን ባይገማገሙም ህወሃትን የሚያስጥል ነገር ለመዘየድ ለስብሰባ መሰየማቸው ልማድ ሆኗል።

ፖለቲካና ሃይማኖት የሽዋሚና ተሽዋሚ፣የተገልጋይና አገልጋይ ባህርይ ባይኖራቸው ኖሮ አንዱ ሌላውን ሃየ ቢል የሚያስከፋ ባልሆነ ነበር ።በመሰረቱ ሀይማኖትና ፓለቲካን የሚያስተሳስሩ ሁለት ዋነኛ ገመዶች አሉ። እነዚህም ሀይማኖትም ፓለቲካም ሁለቱም ሰውን የሚመለከቱ መሆናቸውና ሁለቱም ሀገር ህልው ሆና ስትኖር፣ ሰለምና መረጋጋት በአለበት ሁኔታ ብቻ ሕልው የሚሆኑ መሆናቸው ነው።ፓለቲካ"አማኝ ስለሆንኩ ፖለቲካ አይመለከተኝም" ስለተባለ የሚያስወግዱት ነገር አይደለም። በገቢና ወጪ፣በሰላም ወጥቶ በመግባትና የግለሰባዊ መብቶችን ( የሀይማኖት ነፃነትን ጭምር) መከበር ወዘተ የሚወሰነው የሀገሪቱን የፓለቲካ መዘውር እንደያዙት ሰወች ባህርይ ነው። የተመረጡ፣ሕዝብ የሰየማቸው ሲሆኑ የሃይማኖት ነጻነትን ጨምሮ ሌሎች ነጻነቶች ይከበራሉ። እንደ ህወሓት ያለ ጠበንጃ ነካሽ በኃይል ስልጣን ሲይዝ ሁሉንም መብቶች ማጣት ይመጣል።አፈናና ረገጣው ለሁሉም በመሆኑ ያን መቃወም እንሰሳዊ ባህርይ (instinct) ግድ የሚለው እንጅ ሌላ አይደለም።በእዚያ ላይ ሃይማኖታዊ አስተምህሮት በስነምግባር ውስጥ ሰርጾ ሰላምና አንድነት፣ፍቅርና ቸርነትን፣መረዳዳትና አንዱ ለሁሉም፣ሁሉም ላንዱ የሚሆንበትን ሁኔታ እንዲፈጥር የማድረግ ተልዕኮን በፍላጎትና በፈቃደኝነት የወሰዱ፣ለዚህም ብቁ የሚያደርጋቸው እውቀት የገበዩ እነዚህ በተግዋደሉበት ሁሉ ያግዋደለውን፣የፋለሰውን የመገሰጽ ሞራላውም፣ ሃይማኖታውም ግዴታ እንዳለባቸው መገንዘብ ካልቻሉ ማስመሰላቸው በምድርም በሰማይም እንደሚያስተይቃቸው ማወቅ አለባቸው።

ወደ ፖለቲካና ሀይማኖታዊ አስተምህሮቶች ጋርዮሽ ስመለስ ሁለቱም በሰው ልጅ እኩልነት፣በሰብአዊ መብቶች መከበር፣ በፍትህና ርትእ ወዘተ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ በመሆኑ በእርስ በእርስ ግንኙነቶቻችን፣በፍትህ ተቅዋማት፣በማህነራዊ ህይወታችን ወዘተ ከፍተኛ ተፅእኖ አላቸው። ለህዝብ የቆሙ ፓለቲከኞችም የሀይማኖት አባቶችም ስለ ሰው ልጅ ክቡርነት፣ስለፍትሀዊነት ወዘተ ይሰብካሉ።

ሀይማኖትና ፓለቲካ የመያያዛቸው የመተሳሰራቸውን ያህል አንዱ አንዱን በአወንታዊነት የሚያግዝና የሚረዳ ሆኖ የታየበት ሁኔታ ከእዚህ በፊትም አልታየም፣አሁንም እየታየ አይደለም። የሩቁን ትተን የቅርቦቹን የደርግንና የህወሀትን መንግስታት ብናይ ሀይማኖት የፓለቲካ መሳሪያ፣የሀይማኖት መሪወች የሀይማኖት ነፃነትን ጨምሮ ሌሎች ግለሰባዊና የወል መብቶች ሲረገጡ ከተባባሪነት እስከ አግድሞ ተመልካችነት፣ ሌዜጎችን ሰለባ ከማድረግ ጀምሮ እራሳቸውን ማዳን የማይችሉ ሰለባወች እስከመሆን ደርሰዋል።

የሀይማኖት አባቶች "ከሀጢአት ራቁ" ሰበካ፣ " አትግደል፣በሀሰት አትወንጅል" አስተምህሮት በዋናነት የሚሰጠው ኑሮ አስመርሮት ኑሮው እንዲቃና ፈጣሪውን ለመለመን ወደ አምልኮ ስፍራ ለሚሄደው ምእመን፣መከራና ውጣ ውረድ ያልተለየው ምድራዊ ህይወቱ በሰማይ እንዳይደገም ፈጣሪውን ለመለመን ለታደመው ነው። ይህ ባልከፋ ነበር። ነገሩ ኑሯቸው የድሎት ሆኖ ሌላው ቀርቶ የቀፈት ፎቅ የሰሩና የመስጊድም ይሁን የቤተ ክርስቲያን በር የማይረግጡ፣ ግና ደግሞ ውሎ አዳራቸው መግደልና ማስገደል፣ ማሰርና ማሳሰር፣ ፍትህን ማዛባትና በጎሳና ዝምድና ላይ የተመሰረተ መድልው የሚፈፅሙትስ? እነሱን " አትግደል" አይመለከታቸውም? ተገዳዩ፣ታሳሪው፣ተበዳዩ ላይ በማይክሮፎን የሚጠው የ" አትግደል፣ሌላውን እንደራስህ ውደድ! ወዘተ " ለምን ገዳይ አፋኞችን አይመለከትም? እንዲያውም የሀይማኖት መሪ ወጉ በሀጢአት ነትባ ዘላለማዊ ሞቷን ለመሞት የተዘጋጀችን ነፍስ ከጥፋቷ መልሶ ከዘላለማዊ ጥፋት ማዳን ነው።

በዘመነ ደርግ ወጣቶች የቀይ ሽብር ሰለባ ሲሆኑ፣ እናት ልጇ ተገድሎ "እልል" በይ ስትባል፣ወንድም በወንድሙ፣አባት በልጁ ላይ ሲነሳ የሀይማኖት አባቶች " ተው! ይህ ተግባር ከፈጣሪ መንገድ የወጣ ነው" ሲሉ አልተደመጡም። እንዲያውም እሬሳ ዘለው አዛን ሲያደርጉ፣ ቅዳሴ ሲገቡ ነው ያየነው። ሲወጡም እንደዚሁ እሬሳ እየዘለሉ እቤታቸው ይገባሉ።ከሙፍቲ እስከ ጳጳስ፣ከቄስ እስከሸህ፣ከደረሳ እስከዲያቆን "አፈ ልጓም የተባሉ" ይመስል ፀጠደ እረጭ ብለው ጊዜውን አለፉት። ለወትሮው ለተሰጣቸው ሰማያዊ አደራ ቆመው "አትግደል፣በአንተ እንዲፈፀምብህ የማትሻውን በሌላው አትፈፅም" ባሉ፣ በዚህም የሚመጣባቸውን መከራ ተቀብለው የምንኮራበት ታሪካቸውን እንደነ አቡነ ጴጥሮስ በዘከርነው ነበር።

ደርግ ወድቆ ህወሀት ስልጣን ሲይዝ ልክ እንደባህርይ አባቱ እንደፋሽስት አ በሀይማኖትና ውስጥ እጁን አስገብቶ በማተራመስ ሀ አለ።በአድዋው መለስና በእሱ በተሾመው አባ ጳውሎስ መካከል የደምና የቋንቋ ብቻ ሳይሆን የአላማ ትስስር ተፈጠረ። ሀገር መከፋፈል መገነጣጠሏ፣ ህዝቧ እርስ በርስ ተራረድ፣ተለያይ መባሉን፣ መለስና ህወሀት የሚፈፅሙትን "ይኩን" ብለው ባረከ። ኢትዮጵያና ህዝቧ የሀዘን ማቅ ለብሰው ሳለ ጳውሎስ የምንኩስና ልብሱን አሽቀንጥሮ የሙሽራ ልብስ፣ ነጭ ሀር አስቀደዶ ለበሰ። በህወሀት አነሳሽነት በገዳማት በግፍ የሚታረዱ አባቶችን ጉዳይ "ቅቡል" ብለው አለፋት። ግራዝያኒ አያሌ ዜጎችን በፈጀበት የስድስት ኪሎ አደባባይ በበሀሪ ልጁ በመለስ ትእዛዝ ተማሪወች ሲጨፈጨፉ ሸሁና ጳጳሱ አይተው እንዳላዩ ሆኑ። ከዚያም በኋላ ተማሪወች ከዩኒቨርሰቲ ግቢ ተባረው በተጠለሉበት በቅድስት ስላሴ ቅፅር ግቢ የህወሀት አንጋች ያን ያክል ድብደባና አፈና ሲፈፅሙባቸው ጽህፈት ቤቱ እዚያው አጠገብ የነበረው ጳውሎስ በጣእርና ሰቆቃ ጩኸታቸው አልተረበሸም።

መለስ ከምድር ቢጠፉም የጀመረው ሰፊ የጥፋት አላማ አልጠፋም። ጳውሎስ ቢሸኝም በምትኩ የተተካው "ጳውሎስ ዘዳግም" ግፍን መባረክ መቀደሱን ወጥሏል። እሱም ሆነ አቻውና በህወሀታዊው የእስልምና ጉባኤ መሪ ተብየ በቅርቡ ህወሀት የሚወስደውን የጭፍጨፋ እርምጃ ደግፈው ለነፃነቱ የሚታገለውን ህዝብ "አርፈህ ብትቀመጥ ይሻልሀል" በማለት ለግፍ እነድሰግድ፣ ግፍን አሜን ብሎ እንዲገዛ አሳሰቡ።

በጳውሎስ ዘመን ህወሀት ለአፉ እንኳ ቢሆን " ገምቻለሁ፣ በስብሻለሁ" ሲል ጳውሎስ ለአፋ " በሀጢአት መርከስህን፣ በሙስና ተዘፍቀህ መልካም አስተዳደር አለማስፈንህን፣ ፍትህ ማዛባትህን ካመንክ ዳግም የማትደግምበትን ሁኔተታ ፍጠር፣ንስሀ ግባ" አላለም። ህወሀት ዳግም ገምቶና በስብሶ አሁንም ለአፋ እንዲህ ሆንኩ ሲል የክርስትናም ሆነ የእስልምና መሪወች " በሀጢአት ስትገማ አትኖርምና ለእዚህ የመግማት የመበስበስ አባዜህ ለከት አብጅለት" አላሉም።

ድሮ እናት በልጇ እሬሳ ዙሪያ እየዞረች እልል እንድትል ስትገደድ የሀይመሰኖት አባቶች ያሉት ነገር አልነበረም። የዛሬወቹ ደግሞ በተራቸው እናት በልጇ አስከሬን ላይ እንድትቀመጥ ታዝዛ በህፃን ልጇ ፊት ስትደበደብ ሰምተው ጆሮ ዳባ ልበስ አሉ። አተግደል የሚለው ለተገዳይ የሚሰበክበት ምድር!! ግፈኛ ሳይሆን ግፉአን የሚገዘቱበት አገር ሆናለች ኢትዮጵያ። ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት በሀይማኖት ውስጥ መግባት ብቻ ሳይሆን ራሱ አዛዥ ሲሆን፣የሀይማኖት አባቶች እነደፓለቲካ ሹመኞቹና የጦር ጀነራሎቹ ከአንድ ጎሳ ይምጡ ሲባል ከዚህ የተለየ ሌላ አይፈጠርም። እላይ ያሉትስ የላይኞቹ ሆነው ነው። ምነው ሌላው በደረሰው መከራ ወርድና ስፋት ጋር የሚመጣጠን ጩኸት አያሰማ?

Last edited by Tintagu wolloye on 22 Dec 2017, 15:19, edited 1 time in total.

Tintagu wolloye
Member
Posts: 1467
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

Re: ህወሓት ላይ አመጽ በተነሳ ቁጥር ከአጋዚ ጦር ባልተናነሰ ፍጥነት ህወሃትን ሊታደጉ የሚሯሯጡት “የሀገር ሽማግሌና የሃይማኖት አባት” ተብየወች ሰልፋቸው ከማን ጋር ነው?የሀገራችንን የሽምገላ እሴት ለፀረ ሀገርና ፀረ ህዝብ ቡድን ጥቅም ማዋልስ ተገቢ ነወይ? (ትንታጉ ዘወሎ)

Post by Tintagu wolloye » 22 Dec 2017, 15:15

ህወሀትን ለማዳን የሚፍጨረጨሩ ጢማምና በአንጅ እጃቸው መስቀል በሌላው ፈንጅ የያዙ ካድሬወችን ከህዝብ መነጠል ያስፈልጋል።

ማትያስ እንደ ጳውሎስ ጫማ ሊወረወርበት፣የገማ እንቁላል መፍቀሬ ሰብዕ ሳይሆን መፍቀሬ ህወሀት በአናወዘው ጭንቄው ላይ ሊፈጠፈጥበት ይገባል።

Post Reply