Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Tintagu wolloye
Member
Posts: 1433
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

የህወሀትን ግብአተ መሬት የሚያፋጥኑ ሁለት ብቸኛ መንገዶችና ህወሀት ህዝብን ለማፋጀት የሚወስዳቸው ሁለት ብቸኛ አማራጮች ( ትንታጉ ዘወሎ)

Post by Tintagu wolloye » 21 Dec 2017, 19:19

የአውሮፖ ህብረት ተባለ አሜሪካ ገፍተው የማደራደር ስራ፣ቢሰሩ ኖሮ ከተጋበዙ 26 አመት ባልሞላቸው ነበር።ኮህን ሌሎችን ጨምር ሲባል ያገለለበትን ጊዜ ረስቶ እናደራድራችሁ ማለቱ በግሌ አበሳጭቶኛል። የአውሮፖ ህብረት ከአሚሪካ ቢሻልም የብዙወች ጥርቅም በመሆኑ ለውሳኔ የሚደርሰው በስንት ችግር ነው።እናም አይደርስልንም።ቢሆን ኖሮ የወከላት የወይዘሮ አና ጎሜዝ ሪፖርት በበቃውና ህወሀትን አንቅሮ በተፋው ነበር።

ህወሀት ግብአተ መሬቱን የሚያፋጥኑ ሁለቱ አንኳር መንገዶች የሚከተሉት ናቸው።
1) በዋናነት ህወሀት ሲገለገልባቸው የነበሩት ሁለት ድርጅቶች ( ኦህዲድና ብአዴን) ኢህአዲግ የተሰኘውን ጉረኖ ሰብረው ራሳቸው ከእስር በመፍታት በጋራ ሲቆሙና በዙሪያቸው ሌሎችን ማሰለፍ ሲችሉ ህወሀት ባህሩ የደረቀበት አሳ ይሆናል። እነዚህ ድርጅቶች አንድም በህዝብ ትግል ተገፍተው አለዚያም በአይናቸው ሲያዪት የኖሩትና እስከዛሬ ከግንዛቤ ያልጣፉት ህወሀት የሚፈፅመው ግፍ፣ዝርፊያና ዘረኝነት ገብቷቸው፣ወይም ሁለቱንም ባዘለ ምክንያት ህወሀትን ፊት ነስተውታል። ይሁንና የያዙት የሰራውን በአደባባይ ማመን የማይፈቅደውን ህወሀትን እመን፣ተለወጥ ማለት ነው። ይህ እሽም ተባለ እምቢ ቀጥለው ስለሚወስዱት እርምጃ ያሰቡበት አይመስልም። ህወሀት ቢሸነግል ቢለማመጣቸው " ጅብ እስኪነክስ፣ያነክሳል" እንዲሉ ጊዜ ቢጠብቅላቸው እንጅ በእነሱ ላይ ዘምቶ ድራሻቸውን ከማጥፋት አይቦዝንም።እንደ አቻ፣እንደ እኩያ፣እንደማይቆጥራቸው ከዚህ በፊት ያሳያቸው ሀቅ ሆኖ ለእነሱ ብሎ ስልጣን ሊያካፍል፣ዝርፊያ፣ሊያቆም፣ግደሉ ያላቸውን ለፍርድ ሊያቀርብ፣ከመሬት ተነስቶ ዲሞክራሲያዊ ሊሆንና በዚህም ጦስ ራሱን ፈልጎ ወደማያገኝበት ኢንቁፍጡ መወርወር አይፈልግም።ለእዚህ መፍትሄው ህወሀትን አሽቀንጥሮ ከህዝብ መወገን፣ከህወሀት ጋር ከመወቀጥ በህዝብ አምኖ የህዝብን ጥበቃ ማግኘት ያስፈልጋል።መሳሪያ የያዘው በአመዛኙ ኦሮሞውና አማራው ነው። ህወሀት በትጥቅ ቢሞክር የሚገጥመውን ያውቃልና ይህን አይሞክረውም።

ከአሁን በኋላ ትኩረቱ በሞተው ህወሀት ላይ ሳይሆን እሱን እንደ እባብ ግልፋፊ ጥለው ራሳቸውን እንደገና መፍጠር ስለቻሉና ወይም ስላልቻሉ ሁለት ትልቅ ድርጅቶች መሆን ይገባዋል።ህወሀት ሁሉንም ተቃዋሚ ድርጅት አዳክሞና መዋቅሩን በጣጥሶ ባለበት በዚህ ወቅት ለይቶላቸው ህወሀትን እንደሽቀን አራግፈው በእግራቸው መቆም እስከፈለጉና ለእዚህም ቁርጠኝነት እስካሳዩ ድረስ አገርቤትም ሆነ በውጭ ያሉ ድርጅቶች ሊያግዙአቸው ይገባል።

2) የህወሀትን ግብአተ መሬት የሚያፋጥነውና ለህዝባችን አለኝታ፣የሚሆነው ሁሉም ተቀምጦ የሚመክርበት አስቸኳይ ጉባኤ ውጭ ሀገር በአለ በአንዱ መዲና በማድረግ ህዝብን አንድ አድርጎ በጀመረው ትግል እንዲገፋ የመሚያደርግና አካል ማቋቋም ነው። ህዝብ የተቋተ ውሀ ነው ጎርፍ እንዲሆን ቦይ የሚቀድ ያስፈልገዋል።አገር ቤት ያለውን የለውጥ ሀይል ለመደገፍና ለመምራት ሳይቻል ቀርቶ ህወሀት ዳግም ቢያንሰራራ የተናጠል ትግል አበቅቴ፣የድርጅት ህልውና ተረት ተረት ማሳረጊያ መሆኑ እውን ነው።ትግል በጋለበት ጊዜ ህዝብን አለሁ የሚል መታጣቱ በህወሀት ሊመካኝ አይችልም። አንዲ ከሌላው የኮረጀ እስከሚመስል ድረስ ተመሳሳይነት ያለው የፖለቲካ፣ፕሮግራም ያላቸው ድርጅቶች በአንድ ሆነው ለመታገልና ለማታገል ካልቻሉ አለመኖራቸው ይመረጣል።"ህብረት ያልፈጠርነው በእዚህ ምክንያት ነው" የሚሉ ካሉ ሰበባቸው ይነገርና ያስቸገረው ይሸምገል፣ይገለል፣ድጋፍ ይነፈገው።

ሰላማዊ የሽግግር ሰነድ መዘጋጀቱና ያም ለአውሮፖ ህብረት መቅረቡን ከኢሳት ስሰማ አታጋይ ሰነድ ሆኖ ለህዝብ ይፋ አለመደረጉ ግራ፣አጋብቶኛል። "ይሸጋገር " ተባዩ ህዝብ እንዲት እንደሚሸጋገር ማስተማር ሲገባ ሰነዱ ብራስልስ ላይ መታየቱ ብቻ በቂ ሆኖ መቅረቱ አስቀይሞኛል። ህብረት አስፍቶ አመለካከትን አቻችሎና አጣጥሞ ማታገል ባህል የመሆኑ ወቅታዊነት ሊታይ ይገባል።መሪና ጀግናን ጭንቅ ይወልደዋል። የሚያምጠው ህዝብ ያፈራው ጭንጋፍ ብቻ እንዳልሆነ እርግጠኛ ብሆንም ያን ወይም እነዚያን ጀግኖች አይቸ ሞቴ አሁኑኑ ቢሆን አልቆጭም።

ከላይ የተጠቀሱትን የሚያያይዘው ህብረት፣መተጋገዝ፣መናበብና መተማመን የሚለው ነው። ኦህዲድና ብአዴን ውስጥ ያሉት ፀረ ህወሀት፣ፀረ— የትግሬ መደብ ጭቆና ሀይሎች በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ካሉት ጋር መስራት፣በመረጃና ዲፕሎማሲ፣በፋይናንስና በመሳሰሉት ሊደጋገፉ ግድ ነው።

ህወሀት ክፉኛ ቢቆስልም በሚያጣጥርበት መከዳ ላይ ሆኖ "ማን አባቱ!!" እያለ ይገኛል። የከሰረ መሆኑ ስለተሰማው ሁለት አገርና ህዝብን አፋጅ መንገዶችን ይከተላል።
1) ህወሀት እጁ በደም የጨቀየ፣የዘረፈና በግፍ ሚሊዮኖችን ያሰቃየ መሆኑን አያጣውም። "እንደራደር፣ አጣሪ ኮሚቴ እንኮምት" ምናምን የሚሉ ቀልዶች አይመቹትም። ዞሮ ዞሮ ቢያንስ ግፍና ሀጥያትህ ፀሀየደ ይሙቀው የሚል አንድምታ የያዙ ስለሆኑ " ሙቆትሳ!!" ብሎ ለመጠየቅ ቅንጣት ፍላጎት የለውም።ስልጣን ሲያጣ ተፅእኖና ጥቅም ያጣል ብቻ ሳይሆን ተርፎ ህልው ቢሆን እስከ ዳግሚያ ምፅአት እድሜ ቢኖረው ዳግመኛ ወደ ስልጣን እንደማይመጣ፣ያውቀዋል።ለፍርድ ላለመቅረብ ያለው አማራጭ ወትሮውንም ለእዚህ እንዲመቸው ያዘጋጀውን አንቀፅ 39 ጠቅሶ የዘረፈውን ዘርፎ የገደለውን ገድሎ ትግራይ ይገባል። በእየብሄሩ ያደራጀውና ለዚህ ጊዜ ያዘጋጀው ሀይል እንዳለ የሚናገሩም አሉ። የሶማሌ ልዩ ሀይል ብቸኛ አይደለም ባዮች እነዚህ የተደራጁና፣የታጠቁ ወምበዴወች ከህወሀት ጋር በረዥም ገመድ ተቆራኝተው ብሄር ተኮር ጥቃቶችን በመፈፀም ለህወሀት መደላደያ፣ጊዜ፣የእፎይታ አጋጣሚ ይፈጥራሉ። ይህን የህወሀት እኩይ ተግባር አፈፃፀም በያዘው የውጭ ምንዛሬ ማሸሽ፣የእህል ሸመታ ስምሪትና መሸጥ የሚችሉ ጥቃቅን ንብረቶችን በሀራጅ የመሸጥ እርምጃ ጠቅሰው የሚሞግቱ ተበራክተዋል። ህወሀትን በሚቃወሙ መካከል ይህን የህወሀት እርምጃ የሚናፍቁ አነጋዉያን መኖራቸው የአንድነት ሀይሉ ልብ ሊለው ይገባል። ህወሀት የጋራ፣ጠላት ቢሆንም የኦነግ አላማ የሁላችን ሆኖ አያውቅምና "የገበያ ግርግር—— " ብለን ነቅተን መጠበቅ ይገባናል።

2) ህወሀት የሁለቱ ታላላቅ ብሄረሰቦች ህብረት አስደንግጦታል።እናም ይህን መናድ መሞከሩ ከህወሀት የሚጠበቅ እንጅ ሌላ አይሆንም። ለዚህ ደግሞ የተለያዪ መነሻወችን ሊፈጥር ይችላል። መጀመሪያ ኦሮሞወችን ፈጅቶ "ሶማሌ ፈጃቸው"ን ከአሰረፀ በኋላ ፈጀ ለአለው ዋርድያ ሆኖ የቆመውን ጦር በማንሳት " በቁጭት የተነሳ ህዝብ" የፈጃቸው እንዳስመሰለው አይነት ድራማ ሊሰራ ይችላል።ይህን በበደኖ አድርጎታል። "አዲስ አበባ የእዚህ ብሄር ነው" የሚል በይዘቱ ምንም ማለት ያልሆነ ነገር ግን ስሜትን ጭሮ ወደ ንትርክና ግጭት የሚወስድ ነገር መጫሩም ሌላው ሊሆን ይችላል። ህብረት ባለበት ህወሀት ስጋት አለው።ሌሎች ድርጅቶችን ከፋፍሎ ሲያጠፋ፣እርስ በርስ ሲያባላ፣ሲያጋጭና ሲበትን የኖረ ነው። የሚወራውና የሚያወሩት እውነት ሆኖ ህወሀትን ከላያቸው ላይ አራግፈው የራሳቸው ህዝብ መሪ፣የራሳቸው ድርጅት አጋፋሪ የሚሆኑ ካሉ ጊዜ ያሳየናል።አለበለዚያ "ወጣ፣ወጣና ——" የሚለውን በእነ ብርቱካን፣በእነ ስየና መሰሎቻቸው ያየነው ነውና ስጋታችን ምክንያታዊ ነው። ህወሀት የራሴ የሚለውን ህዝብ ሀውዜን ላይ ያስጨፈጨፈ፣አመራሩ አብረው ለታገሉም ሆነ ለአታገሉ ቅንጣት ርህራሄ የሌለው መሆኑን ከተክሉ ሀዋዝ እሰከ ስየ አብረሀ፣ከክንፈና ሀየሎም " ሚስጥራዊ" አሟሟት አማራነቷ ተነቅሶ እስከተባረረችው አዜብ መስፍን ያየነው ነው። ለለማ መገርሳ ይመለሳል አይባልም። እንደነ አለምነው መኮንን ያሉ ህወሀታዊ አማሮች ባሉበት ህወሀት ከፍሎ ማጋጨትም ሆነ መበተን ቢከብደው እውነትም ግብአተ መሬቱ ደርሷል ማለት ነው።

Tintagu wolloye
Member
Posts: 1433
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

Re: የህወሀትን ግብአተ መሬት የሚያፋጥኑ ሁለት ብቸኛ መንገዶችና ህወሀት ህዝብን ለማፋጀት የሚወስዳቸው ሁለት ብቸኛ አማራጮች ( ትንታጉ ዘወሎ)

Post by Tintagu wolloye » 22 Dec 2017, 08:17

The stupid TPLF calculated that the dispute around the status of Addis Ababa could weaken the strong bond between the Oromo and Amhara ethnic groups.As ususal it misscalculated the reasoning abiltity of the non- TPLF guys. No energy shall be wested on trivial issues.

Full focus on the TPLF!!! VIVA OPDO!

Post Reply