-
- Senior Member+
- Posts: 33975
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
[VOA UPDATE] መተማ ጎንደር ላይ በህዝብ የተያዘው ህገ ወጥ የመሳርያ ዝውውር [VIDEO]
Please wait, video is loading...
Last edited by Revelations on 19 Aug 2019, 22:20, edited 1 time in total.
-
- Senior Member+
- Posts: 33975
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Re: [VIDEO] መተማ ጎንደር ላይ በህዝብ የተያዘው ህገ ወጥ የመሳርያ ዝውውር
መከላከያ በጎንደር መተማ ዮሀንስ በኩል ሳይፈተሽ ወደ ሱዳን ካርቱም ማለፍ አለበት ያለው ጥይት እና መሰል ንብረት በአካባቢው ሕዝብ እና በፀጥታ መዋቅሩ ተቃውሞ ታግቶ እንደሚገኝ ተነገረ።
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ነሐሴ 12 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ
ለአማራ ሚዲያ ማዕከል ወደ አካባቢው የስራ ኃላፊዎች በመደወል ያገኘው መረጃ እንዳመለከተው ነሐሴ 12 ቀን 2011 ዓ.ም ከማለዳው 2 ስዓት ጀምሮ ቁጥራቸው አምስት የሚሆኑ የመከላከያ ሰራዊት አርማ ባለባቸው የቢሾፍቱ ስሪት ተሽከርካሪዎች የተጫነ ጥይት እና መሰል ንብረት ያለፍተሻ ለማሳለፍ ቢሞከርም የፀጥታ መዋቅሩ እና ሕዝቡ የተለየ ጥርጣሬ ስላደረበት ማስቆሙ ነው የተነገረው።
ስለነበረው ሁኔታ መረጃ እንዲሰጡን ያነጋገርናቸው የመተማ ዮሀንስ ከተማ የአስተዳደር እና ፀጥታ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር ይናገር አምስቱም ተሽከርካሪዎች ታርጋቸው በማጥቆሪያ/ግሪስ የተቀባ በመሆኑ ለጥርጣሬ የሚጋብዝ ስለነበር ሕዝቡ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመተባበር ሳይፈተሹ አያልፉም በሚል አስቁሟል ብለዋል።
አምስት ሾፌሮችን ጨምሮ ሶስት አጃቢዎች እንዲሁም አሻሻጮች በአማራ ክልል ልዩ ሀይል አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያወሱት ኢ/ር ይናገር ተሽከርካሪዎች ፍተሻ እስኪደረግላቸው ድረስ በኮማንድ ፖስቱ ጥምር ሀይል እየተጠበቁ መሆኑን ገልፀዋል።
በአንደኛው ላይ በተደረገ ፍተሻ ጥይት መጫኑ የተገለፀ ሲሆን አካሄዱ ህግ እና ስርዓቱን የተከተለ ነው ብለው እንደማያምኑ ኢ/ር ይናገር አክለዋል።
ምንም እንኳ በመከላከያ ዋና ዳይሬክተር አህመድ ሀምዛ የተፃፈ ደብዳቤ ንብረት በሽያጭ ማስተላለፍን ይመለከታል በሚል ሳይፈተሽ እንዲያልፍ ቢጠይቁም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትም ሆነ የዞን የመስተዳድር አካላት እውቅና እንደሌላቸው ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል።
ኢ/ር ይናገር ሲቀጥሉ እስከ ምሽት ድረስ አለመፈተሹን በማረጋገጥ ነገር ግን በየደረጃው ካለ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ሳይፈተሽ እንዲያልፍ የሚል ግፊት እየተደረገባቸው መሆኑን አስታውቀዋል።
የመተማ ዮሀንስ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀብታሙ በበኩላቸው ለመስክ ስራ ወጥተው ስለነበር በአካባቢው እንዳልነበሩ በማስታወስ ነገር ግን ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት አምስት የመከላከያ ናቸው የተባሉ ተሽከሪካሪዎች ለፍተሻ አለመተባበራቸውን ተከትሎ ሕዝብ እና የፀጥታ መዋቅሩ ኬላ በመዝጋት ማስቆሙን አረጋግጠዋል።
ከወራት በፊት በአካባቢው ከሰፈሩት መካከል አምስት የሚሆኑ የመከላከያ ሰራዊት አመራር እና አባላት በመተማ በኩል በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ከቦታ ቦታ ሲያንቀሳቅሱ በአካባቢው ፋኖዎች፣ የፀጥታ አካላት እና በሕዝብ ጥቆማ እና ትብብር በህግ ጥላ ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑ ይታወሳል።
ፎቶ_Atrnos media

- Member+
- Posts: 6322
- Joined: 28 Apr 2018, 00:31
Re: [VIDEO] መተማ ጎንደር ላይ በህዝብ የተያዘው ህገ ወጥ የመሳርያ ዝውውር
Revelations wrote: ↑18 Aug 2019, 19:38
[/quote
I found this picture to be really sad.
Look at the number of young people not involvred, yet two hands atamiro yemimeleket.
So many people with nothing to do, in such a small place.
As for the weapons, this whole area from Quara to Axum is always awash with weapons from the days of 7000 French weapons of Ras Wube.
-
- Member
- Posts: 4307
- Joined: 27 Sep 2017, 21:56
Re: [VIDEO] መተማ ጎንደር ላይ በህዝብ የተያዘው ህገ ወጥ የመሳርያ ዝውውር
I don't get it. I am looking someone is surrendering, Who is that? The army?
-
- Member
- Posts: 4919
- Joined: 23 Dec 2017, 07:23
-
- Senior Member+
- Posts: 33975
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Re: [VIDEO] መተማ ጎንደር ላይ በህዝብ የተያዘው ህገ ወጥ የመሳርያ ዝውውር
መተማ ላይ የተያዘው ጥይትና መሳሪያ መዳረሻው ትግራይ ሲሆን በብርሃኑ ጁላ ፊርማ የወጣ ነው ተብሏል።
=>4595 ሳጥን ጥይት ተይዟል።
=> በፍሬ 5 ነጥብ 5 ሚሊዬን ይሆናል።
=>ባለ 10 ባለ 24 ባለ 30 ዶላር ነው ዋጋቸው
የሚሄደው ወደ ትግራይ ነው።
ጥይቱን ለምን በሱዳን በኩል ማጓጋዝ እንዳስፈለገ፣ 5.5 ሚሊዮን ጥይት ወደ ተግራይ ለምን እንደሚላክ፣ ለአማራ ክልል ጥይትም መሳሪያም የለኝም ያለው መከላከይል ይህንን ሁሉ ለምን ወደ ትግራይ መላክ ፈለገ?ብዙ ጥያቄ ያጭራል።
ለማንኛውም ዛሬ ጀግናው የጎንደር አማራ ያስቆመው አምስት ተሳቢ ጥይትን ከገላባት (ሱዳን) ተቀብሎ ወደ ትግራይ የሚወስድ ሃይልም ተዘጋጅቶ ነበር ተብሏል።
=>4595 ሳጥን ጥይት ተይዟል።
=> በፍሬ 5 ነጥብ 5 ሚሊዬን ይሆናል።
=>ባለ 10 ባለ 24 ባለ 30 ዶላር ነው ዋጋቸው
የሚሄደው ወደ ትግራይ ነው።
=>የብርሃኑ ጁላ ማህተምና ፊርማ አለበት።
=> የክልሉ መንግስት ዕውቅና የለውም።
=>ፊርማውና ሰነዱ ላይ ያሉት ሰዎች በሙሉ #የትግራይ መኮንኖች ናቸው።
(Ayalew Menber)

አማራ ክልል፡ መተማ ዮሐንስ በተያዙት ተሽከርካሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው
የመከላከያ ሠራዊት ንብረት ናቸው የተባሉና በመተማ ዮሐንስ በኩል ጭነት ይዘው ወደ ሱዳን ሊሻገሩ ሲሉ እንዲቆሙ በተደረጉ አምስት ከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የአካባቢው ፖሊስ ለቢቢሲ ገለጸ።
ትናንት ከሰዓት ከዘጠኝ ሰዓት በኋላ አምስት የመከላከያ ሠራዊት ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ሱዳን ለመሻገር ሲሞክሩ መተማ ዮሐንስ ላይ በአካባቢው ማኅበረሰብ ታግደው እንዳያልፉ መደረጋቸውን በስፋት እያነጋገረ ይገኛል።
ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎችና ፎቶግራፎች እንደሚጠቁሙት ጭነት የያዙት ከባድ ተሽከርካሪዎች ጥቂት በማይባሉ ሰዎች ተከበው መንገድ ዳር እንደቆሙና የአካባቢው ባለስልጣናትም ስለጭነቱ ህጋዊነት ለማወቅ የማጣራት ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ያመለክታሉ።
ቢቢሲ ስለክስተቱ ለማወቅ ባደረገው ጥረት የመተማ ዮሃንስ ሁሉን አቀፍ የወንጀል ምርመራ ኦፊሰር የሆኑትን ሳጅን እንዳልካቸው ተሰማን በማናገር እንደተረዳው አምስቱ ከባድ ተሽከርካሪዎች እሁድ ከሰዓት በኋላ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ወደ ሱዳን ለመሻገር ሲሞክሩ የኢሚግሬሽን ሰራተኞች አሽከርካሪዎቹን ፓስፖርት እንዲያሳዩ መጠየቃቸውንና ማሳየት እንዳልቻሉ ተገልጿል።
ሳጅን እንዳልካቸው አክለውም "ይህንን ተከትሎ አለመግባባት መፈጠሩንና በዙሪያው የነበሩት የአካባቢው ነዋሪዎች የተሽከርካሪዎቹ ጭነት በሕገ ወጥ መልኩ ሊሻገር ነው በሚል ጥርጣሬ እንዳይንቀሳቀሱ አድርገው በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርገዋቸዋል" ብለዋል።
ምንም እንኳ ፖሊስ ተሽከርካሪዎቹን ባገኘበት ጊዜ እንደተባለው ሆኖ ባያገኘውም "ሌላኛው የጥርጣሬ መነሻ ደግሞ የተሽከርካሪዎቹ የሰሌዳ ቁጥር በግሪስ ተቀብቶ እንዳይታይ ተደርጓል" የሚል እንደነበርም ሳጅን እንዳልካቸው ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት አምስቱም ተሽከርካሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆነው የአካባቢው የመስተዳድር አካላት ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን ማጣራት እየተደረገ መሆኑን የገለጹት የወንጀል ምርመራ ኦፊሰሩ ተሽከርካሪዎቹ የጦር መሳሪያ የጫኑ መሆናቸውን ማረጋገጣቸውን ተናገረዋል።
ከባድ ተሽከርካሪዎቹ የተወሰነ ቁጥር ባላቸውና የመከላከያ ሠራዊት የደንብ ልብስና መለዮን የለበሱ ጠባቂዎች አጅበዋቸው እንደነበር ቢነገርም እስካሁን ግን ሙሉ መረጃ የሌላቸው መሆኑን ሳጅን እንዳልካቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ክስተቱን ተከትሎ መተማ ላይ ተይዘው እንዳያልፉ የተደረጉት ከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ ዘረፋ እንደተፈጸመ እየተነገረ መሆኑን ጠቅሰን የጠየቅናቸው የፖሊስ ኃላፊው በሰጡን ምላሽ "በተፈጠረው ግርግር የጸጥታ ችግርም ሆነ ዘረፋ አላጋጠመም" ሲሉ አረጋግጠዋል።
ፖሊስ ስለተያዙት ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ምንነትና ወደየት እያመሩ እንደሆነ ለማወቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የገለጹት ሳጅን እንዳልካቸው እስካሁን ከከፍተኛ የመከላከያ ሠራዊት ባለስልጣናት የተባሉት ነገር እንደሌለ ጠቅሰው "በዚሁ አካባቢ የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊትም ስለጉዳዩ የሚያውቀው ነገር እንደሌለው ነግሮናል" ብለዋል።
ስለጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የመተማ ዮሐንስ ከተማ የአስተዳደርና ጸጥታ ኃላፊ ኢንስፔክተር ይናገርን ብንደውልላቸውም ለጊዜው ያላቸው መረጃ ከዚህ የተለየ አለመሆኑን ገልጸው በአሁኑ ወቅት ሁሉም ተሽከርካሪዎች በአንድ ቦታ ሆነው ጥበቃ እየተደረገላቸው ሲሆን ጉዳዩን ለማጣራት የዞንና የክልል የሥራ ኃላፊዎች ወደ ስፍራው መጓዛቸውን ገልጸዋል።
አክለውም የተያዙት ከባድ መኪኖች አሽከርካሪዎች ሕጋዊ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ደብዳቤ እንዳላቸው መናገራቸውንና እስካሁን ግን የደብዳቤውን ሕጋዊነት ማረጋገጥ አለመቻሉን የአስተዳደርና ጸጥታ ኃላፊው ለቢቢሲ ገልጸዋል።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሁለቱም የአካባቢው የፀጥታ ኃላፊዎች እንዳሉት ክስተቱን ተከትሎ በአካባቢው ምንም አይነት የፀጥታም ሆነ የትራንስፖርት መስተጓጎል እንደሌለና ከሱዳን ወደ መተማ ዮሐንስና ከመተማ ዮሐንስ ወደ ሱዳን ገላባት የሚደረገው እንቅስቀሴም እንደቀጠለ ነው ሲሉ አረጋግጠዋል።
ስለተሽከርካሪዎቹ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከመከላከያ ሠራዊት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ስልክ ባለመነሳቱ ለጊዜው አልተሳካልንም።
https://www.bbc.com/amharic/news-49394919