Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 33538
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

Video Of: BeQele Gerba In Cursed-Land-Tigray:-- Is Abiy Slowly Showing Us That He Is A Tplf Puppet???!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 27 Jul 2019, 16:41

ኢትዮጵያ
አቶ በቀለ ገርባ በመቐለ

አቶ በቀለ ገርባ በመቐለ በቋንቋዎች ህልውናና ዕድገት ላይ ባተኮረ ውይይት ተሳትፈዋል። ከዚህ ቀደም በኦሮሞ ፖለቲካ ከፍ ያለ ቦታ ያላቸው ልሒቃንም ወደ መቐለ ተጉዘው ውይይት አድርገዋል። የመቐለ ዩኒቨርሲቲው መምህርት አቶ ማቲዎስ ገብረሕይወት ፖለቲከኞቹ ደጋግመው ወደ ሰሜን መጓዛቸው የፌድራሊስት ኃይሎች መሰባሰብ ምልክት ሊሆን ይችላል ይላሉ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:32
አቶ በቀለ ገርባ በመቐለ

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ቋንቋዎች መምህር አቶ በቀለ ገርባ ባሳለፍነው ዕለተ ሐሙስ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው በቋንቋዎች ህልውናና ዕድገት ትኩረት ያደረገ ፅሑፍ አቅርበዋል፡፡ አቶ በቀለ አሁን ስራ ላይ ያለው ሕገ መንግስት ለሁሉም ቋንቋዎች እኩል እውቅና መስጠቱ ለኢትዮጵያ ቋንቋዎች ዕድገት መልካም አጋጣሚ ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ አቶ በቀለ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ ጥያቄ ተነስቶላቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ቋንቋዎች መምህር አቶ በቀለ ሐሙስ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ዓዲ-ሓቂ ግቢ ባቀረቡት በቋንቋዎች ህልውናና ዕድገት ዙርያ በሚያጠነጥን ፅሑፋቸው በኢትዮጵያ የሚነገሩ ቋንቋዎች ለዘመናት እኩል እውቅናና ዕድገት ሳይኖራቸው መቆየቱ ገልፀዋል፡፡ አቶ በቀለ ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ሌሎች ታዳሚዎች ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት በቋንቋና የህዝቦች ማንነት ላይ የተመሰረተው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ስርዓት ለሀገሪቱ አዋጪ መሆኑ ጠቁመዋል፡፡

አቶ በቀለ ገረባ ካቀረቡት በቋንቋዎች ህልዕናና ዕድገት ላይ ትኩረት ካደረገው ፅሑፋቸው በተጨማሪ በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ የፖለቲካ ሀይሎች ፍላጎታቸው ለመፈፀም የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በተያየ መንገድ ግጭት እንዲከሰትና መረጋጋት እንዲጠፋ ምክንያት እየሆነ ነው ያሉት የኦፌኮ ምክትል ሊቀ መንበሩ አቶ በቀለ ገረባ ፍትሓዊ፣ ታማኝና ግዜው የጠበቀ ምርጫ በማድረግ ወደ ሌላ ምዕራፍ መሸጋገር እንደሚገባ በመጥቀስ መፍትሔ ያሉት ሐሳብ አቅርበዋል፡፡

ስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ሕገ መንግስትና የፌደራል ስርዓት ለግጭት መነሻ አድርጎ ማቅረብ ተገቢ አለመሆኑ የጠቀሱት አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ በቀለ የፌደራል ስርዓቱ ለግጭት መነሻ ሊሆን እንደማይችል፣ ሕገ መንግስቱም እርሳቸው ጨምሮ ህዝብ ተወያይቶበት የፀደቀ ሰነድ መሆኑ ተናግረዋል፡፡

ከቅርብ ግዜ ወዲህ በተለይም የኦሮሚያ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች በመቐለ እየተገኙ ከምሁራንና አክቲቪስቶች ጋር በፌደራሊዝምና ሌሎች ጉዳዮች ዙርያ እየተወያዩ ይገኛሉ፡፡ ይህ የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት ከሌሎች ፌደራሊስት ያላቸው የፖለቲካ ሐይሎች ጋር በጋራ እንደሚሰራ ከጠቆመው ጋር ግንኙነት ይኑረው አይኑረው የጠየቅናቸው የውይይቱ አዘጋጆች፡ የፓለቲከኞቹና ምሁራኑ ውይይት ከአንድ ፖርቲ ዕቅድና ፍላጎት ጋር ግንኙነት የለውም ብለዋል፡፡

ሌሎች ምሁራን ግን የውይይቱ ምናልባትም አዲስ የፖለቲካ ጥምረት ለመመስረት ያለመ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አላቸው፡፡

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

እሸቴ በቀለ