Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 5889
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ኢትዮጵያን ማዘመን እንደ ዘመናዊ ኮሪደር ልማቶቹ በዘመናዊ ፌደራሊዝም ነዉ

Post by Naga Tuma » 06 Dec 2024, 15:47

በዜና የምሰማዉ ዘመናዊ ልማት ለሃገር ኢኮኖሚ እድገት መልካም መሠረቶችን የሚገነባ ከሆነ ተመሳሳይ የሆኑ ዘመናዊ ፌደራሊዝም መሠረቶችን መገንባት ኣይቻልም?

ኣዲሶቹ የሃገር ዩኒቨርዚቲዎች የዘመናዊ ፌደራሊዝም መሠረቶች መሆን ኣይችሉም?

አዲስ አበባ በኮሪደር ልማቶች መሃል ሃገር ዉስጥ ስትገዝፍ ኣዲሶቹ ዩኒቨርዚቲዎች ከፌደራል መንግስት ጋር በመተባበር የአከባቢዎቻቸዉ ኮሪደር ልማት መሠረት መሆን ኣይችሉም? የፌደራሊዝም ጥያቄ ይህ ኣልነበረም?

ለምሳሌ ሰላሌ አምቦን ሳይጠብቅ የፌደራል መዋቅር ዉስጥ ገብቶ አከባቢዉን ቀልጠፍ ብሎ ያሳድጋል። ቦረና ወለጋን ሳይጠብቅ ከፌደራል መንግስት ጋር እየሰራ አከባቢዉን ያሳድጋል።

ሀረርጌ ምቹ ባይኤን ቀበ ዘፈኑን ከማዳመጥ ተነስቶ አርሲን ሳይጠብቅ ከፌደራል መንግስት ጋር እየሰራ አከባቢዉን ያሳድጋል። ጭሮም ድሬደዋን ሳይጠብቅ።

ወለጋ ዉስጥም ነቀምቴም ደምቢ ዶሎን ሳይጠብቅ። ሻምቡም ነቀምቴን ሳይጠብ። ከፈለገ ከነቀምቴም ሆነ ከደብረ ማርቆስ ጋር በመተባበር።

ጎጃም ጎንደርን ሳይጠብቅ። ደብረማርቆስ ባህር ዳርን ሳይጠብቅ።

ወሎ ትግራይን ሳይጠብቅ። አክሱም አደዋን ሳይጠብቅ።

ጅማ ኢሉ አባ ቦራን ሳይጠብቅ። ወልቅጤ ወላይታን ሳይጠብቅ።

አርሲ የቀጥታ ፌደራል አስተዳደር ምሳሌ የሆነዉን ስዳማን ሳይጠብቅ።

ይህ ለዘመናዊ የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ጽንሰ ሀሳብ ነዉ። ኣዲስ ኣይዴለም። ስራ ላይ መዋል የሚችል መሆኑን ለማጥናት በቂ ዩኒቨርዚቲዎች ኣሉ።

ሃገርን ለማፍረስ የተዋቀሩ አስተዳደሮች ዘላቂ ሃገርን የምያስተዳድር አወቃቀር ነዉ ብሎ ማሰብ የፖለትካ መቃወስ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።

ኢትዮጵያ የስዳማን የፌደራል አስተዳደርን ዌልካም ካለች ሰነበተች። የአወቃቀሯ ሂደት ጥሩ ምሳሌ ኣልነበረም?

ጥሩ ምሳሌ የነበረ ከሆነ ይህ ጽንሰ ሀሳብ የኢትዮጵያን ፌደራሊዝም ዘመናዊ ኣያደርግም?