እዚህ ፎረም ላይ ልማታዊ ዘጋቢዎች ስለ ኮሪደር ብርቅርቅታ ሳንወድ ሊያሳምኑን ከልማታዊ የመንግስት ሜድያዎች የተስቀለ ቪድዮ ሁሉ አምጥተው የሚለጥፉብን የዲያስፖራ ካድሬዎች ግን ሄደው አይተው ነው ወይስ ሳያዩ የሚያምኑ ፃድቃን ናቸው ተብለው ነው?
መቸም ገንዘብ ከስይጣን ይልቅ ያስለፈልፋልና::
ስንዴ አናስገባም ኤክስፖርት እናረጋለን ሲሏቸው አምነው አሜን ይላሉ
የኢትዮዽያ ኢኮኖሚ በ 2030? እድገቱ በአለም አንደኛ ይሆናል-አሜን
ወደብ አገኘን ሲሏቸውማ.....እልልልልልል
ስው ሲያልቅ በለውጥ እየተሻገር ነው ሲባሉ---አሜን
ዛሬ የማደርገውን እናንተ አይገባችሁም ነገ ሳርግ ታመስግኑኛላችሁ ሲባል......ሃሌሉያ
ጢያራ ስርተናል ድሮን አምርተናል (ሲበሩ ግን አልታየም...አይ መርዳሳ ነብስህን አይማረው)....ሞቅ ያለ ጭብጨባ
...................
እኛ እያየናቸው እውርን እውር እየመራው ሁለት እውሮች ሳያዩ የሚያምኑ ፃድቃን ናቸው እየተባባሉ ወዴት እየገስገሱ እንደሆነ መሪውም ተመሪውም አጨናባሪውም የሚያውቁት አይመስልም!