Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 12724
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Start Monday with እማማ ኢትዮጵያ የጀግኖች አገር - ባል ወለድብሽ ይቆጨኝ ነበር። እሸቱ ከጓሮ -ወተቱ ከማጄት እማማ ኢትዮጵያ -ምድራዊ ገነት።

Post by Abere » 18 Nov 2024, 12:56

Start Monday with እማማ ኢትዮጵያ የጀግኖች አገር - ባል ወለድብሽ ይቆጨኝ ነበር።

እሸቱ ከጓሮ -ወተቱ ከማጄት
እማማ ኢትዮጵያ -ምድራዊ ገነት



Fed_Up
Senior Member+
Posts: 22034
Joined: 15 Apr 2009, 10:50

Re: Start Monday with እማማ ኢትዮጵያ የጀግኖች አገር - ባል ወለድብሽ ይቆጨኝ ነበር። እሸቱ ከጓሮ -ወተቱ ከማጄት እማማ ኢትዮጵያ -ምድራዊ ገነት።

Post by Fed_Up » 18 Nov 2024, 13:07

Abere wrote:
18 Nov 2024, 12:56
Start Monday with እማማ ኢትዮጵያ የጀግኖች አገር - ባል ወለድብሽ ይቆጨኝ ነበር።

እሸቱ ከጓሮ -ወተቱ ከማጄት
እማማ ኢትዮጵያ -ምድራዊ ገነት




ግጥሙ ስስተካከል


እሸቱ ከጎሮ-ወተቱ ከማጄት
እማማ ኢትዮጵያ-ምድራዊ ገነት
ተብሎ ተገጠመ ምንም በሌለበት
ህዝቡ እየኖረ በተመጽዋችነት
ህሉም ነገር አለ - እነ ተረት ተረት::
ወተቱም ማሩም አለ በምናቡ አለም
እውነት እና ምግብ ኢትዬጵያ ውስጥ የለም::

Abere
Senior Member
Posts: 12724
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: Start Monday with እማማ ኢትዮጵያ የጀግኖች አገር - ባል ወለድብሽ ይቆጨኝ ነበር። እሸቱ ከጓሮ -ወተቱ ከማጄት እማማ ኢትዮጵያ -ምድራዊ ገነት።

Post by Abere » 18 Nov 2024, 15:26



የአፍሪካ ውሃ ማማ፤ የዳቦ ቅርጫት፥
እምቅ ተሰጥዖሽን ጠላሽ አውቆት፤
ተባይ ሽፋታ አስታጥቀው ወገብሽን ይዘውት፤
ቁንጫ ሽዕብያ፤ ትኋን ኦነግ እንድሁም ወያኔ የመዥገር እናት፤
ድሃነሽ ይሉሻል ተብትበው አስረውሽ በሴራ እግር ብረት።
አንችማ ሃብታም እማምይ ኢትዮጵያ - መቀነትሽን አስረሽ፤
ውጭ አገር ያለውን ሽሮ በርበሬው ትኩስ እንጀራ ትመግቢዋለሽ።

ከኤርትራ እስከ ባሌ ጠብቆ ወረፋ፤
እንጀራ ለመግዛት ወረፋ ሲጋፋ፤
አንችማ ሃብታም ነሽ ውጭ ታጠግቢያለሽ ሁሉ እንዳይ ከፋ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 5889
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: Start Monday with እማማ ኢትዮጵያ የጀግኖች አገር - ባል ወለድብሽ ይቆጨኝ ነበር። እሸቱ ከጓሮ -ወተቱ ከማጄት እማማ ኢትዮጵያ -ምድራዊ ገነት።

Post by Naga Tuma » 18 Nov 2024, 18:35

ግጠም ኣለኝ ብሎ አበረ ከአዲመሪኖ
በ ኤ ረታዉ ኣሉ ገጣሚዉ ኣሳምኖ

ይህ ስለክርክሩ ሳይሆን የማን ግጥም የበለጠ ግጥም ሆነ ለማለት ነዉ።

ኣንድ ግዜ የኢትዮጵያ ማትሪክ ፈተና ይባል የነበረዉ ዉስጥ አማርኛን ማን ነዉ ኤ የምያገኘዉ ብዬ ብጠይቅ ትግርኛ ተናጋሪዎች፣ በተለይም የኤርትራ፣ ናቸዉ ተባልኩኝ። ምክያቱም የአማርኛ መሠረት ትግርኛ ዉስጥ ኣለ ተባልኩኝ።

አዲመሪኖ ያልኩኝ የድሮ አዲስ ኣበቤዎችን፣ የዘንድሮ አስመሪኖዎችን ነዉ። የተሻለ ስም ከወጣላቸዉ እስቲ ሞክሩት። እኔ ለመከፋፈል ሳይሆን ደርግን በካልቾ፣ በጥፊ፣ በቴስታ ብሎ ያባረሩትን ያባብሉ ከሆነ ለማለት ነዉ።
Last edited by Naga Tuma on 20 Nov 2024, 13:29, edited 1 time in total.

Fed_Up
Senior Member+
Posts: 22034
Joined: 15 Apr 2009, 10:50

Re: Start Monday with እማማ ኢትዮጵያ የጀግኖች አገር - ባል ወለድብሽ ይቆጨኝ ነበር። እሸቱ ከጓሮ -ወተቱ ከማጄት እማማ ኢትዮጵያ -ምድራዊ ገነት።

Post by Fed_Up » 18 Nov 2024, 22:44

Abere wrote:
18 Nov 2024, 15:26


የአፍሪካ ውሃ ማማ፤ የዳቦ ቅርጫት፥
እምቅ ተሰጥዖሽን ጠላሽ አውቆት፤
ተባይ ሽፋታ አስታጥቀው ወገብሽን ይዘውት፤
ቁንጫ ሽዕብያ፤ ትኋን ኦነግ እንድሁም ወያኔ የመዥገር እናት፤
ድሃነሽ ይሉሻል ተብትበው አስረውሽ በሴራ እግር ብረት።
አንችማ ሃብታም እማምይ ኢትዮጵያ - መቀነትሽን አስረሽ፤
ውጭ አገር ያለውን ሽሮ በርበሬው ትኩስ እንጀራ ትመግቢዋለሽ።

ከኤርትራ እስከ ባሌ ጠብቆ ወረፋ፤
እንጀራ ለመግዛት ወረፋ ሲጋፋ፤
አንችማ ሃብታም ነሽ ውጭ ታጠግቢያለሽ ሁሉ እንዳይ ከፋ።
እባክህ አታጎምዠን ሰለዚች ኢትዮጵያ
ማር ሞልቶ የሚፈስ ባት ወተትም እንደዚያ
ምግብና ወይኑ ድግሱ የበዛ
ሞየሚንዠርዠርባት የማያልቅ እንደዋዛ
የት ይሆን ያለችው ይች የእህል ዋንዛ?

የኛይቱ ኢትዮጵያ እማ ችግር ያጎበጣት
ምላስ ብቻ ቀርታ ..ምንም የሌላት ናት
ልጆቿ የተራቡ ፊታቸው የገረጣ
ሆኖባቸው ኑሮ ድህነት ፋንታና እጣ
የዘር ውርስ ይመስል ልክ እንደራስ መላጣ
ኑሯቸው ይመስላል የደረቅ ዛፍ ጦጣ
እርዳቸው እንዲወጡ "ጉርሻ" ከሚሉት ጣጣ::

እባክህ ንገረን ኢትዮጵያ ያንተዋ
የትኛው አለም ትሆን ...ከየትኛው ህዋ?

almaze
Member+
Posts: 6886
Joined: 15 Dec 2013, 03:38

Re: Start Monday with እማማ ኢትዮጵያ የጀግኖች አገር - ባል ወለድብሽ ይቆጨኝ ነበር። እሸቱ ከጓሮ -ወተቱ ከማጄት እማማ ኢትዮጵያ -ምድራዊ ገነት።

Post by almaze » 19 Nov 2024, 01:14

Fed_Up wrote:
18 Nov 2024, 22:44


እባክህ አታጎምዠን ሰለዚች ኢትዮጵያ
ማር ሞልቶ የሚፈስ ባት ወተትም እንደዚያ
ምግብና ወይኑ ድግሱ የበዛ
ሞየሚንዠርዠርባት የማያልቅ እንደዋዛ
የት ይሆን ያለችው ይች የእህል ዋንዛ?

የኛይቱ ኢትዮጵያ እማ ችግር ያጎበጣት
ምላስ ብቻ ቀርታ ..ምንም የሌላት ናት
ልጆቿ የተራቡ ፊታቸው የገረጣ
ሆኖባቸው ኑሮ ድህነት ፋንታና እጣ
የዘር ውርስ ይመስል ልክ እንደራስ መላጣ
ኑሯቸው ይመስላል የደረቅ ዛፍ ጦጣ
እርዳቸው እንዲወጡ "ጉርሻ" ከሚሉት ጣጣ::

እባክህ ንገረን ኢትዮጵያ ያንተዋ
የትኛው አለም ትሆን ...ከየትኛው ህዋ?
I had no idea Fendadaw was related to Maya Angelou! He has inherited some serious poetic skills. :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

Post Reply