The first evaluation report on Ethiopia’s macroeconomic reform will be released in the next few days, the International Monetary Fund (IMF) reveals. It said that authorities need to keep dealing with any issues that come up in the foreign exchange markets. "We visit periodically in the context of our program; we have just completed the first review, so that report will be published in the next few days,” according to the mission chief, who just traveled to Ethiopia.
“There is a lot of work to be done, but I think the agenda is well laid out already, so it’s a question of sticking to the course,” he says. “So these are two key areas in the program, but certainly they need to keep dealing with any issues that come up in the exchange rates, in the foreign exchange markets, and also the state-owned enterprises reforms in the program are also important.”
https://capitalethiopia.com/2024/10/29/ ... ic-reform/
-
- Member
- Posts: 4207
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
-
- Member
- Posts: 4207
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Re: IMF to release first evaluation report on Ethiopia’s Macroeconomic Reform
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይ ከዚህ ቀደም የነበረውን ጣልቃ ገብነት የመቀነስ ዕርምጃ በማጠናከር፣ ለገበያው ዕድገት የሚያግዙ የፖሊሲ ዕርምጃዎች መውሰዱን እንዲቀጥል የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) አሳሰበ፡፡
የአይኤምኤፍ ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የቦርዱ ሰብሳቢ ቦ ሊ እንዳስታወቁት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በብሔራዊ ባንክ አማካይነት ሲደረጉ የቆዩ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይ የሚደረጉ ጣልቃ ገብነትን የመቀነስ ተግባራት አጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡
አይኤምኤፍ በአራት ዓመታት የ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ የብድር አቅርቦት በተመለከተ ባለፈው ወር ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነት ላይ መድረሱ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህንንም ተከትሎ የተቋሙ ቦርድ 340.7 ሚሊዮን ዶላር ፈቅዷል፡፡
ሌላው በሪፖርቱ የተገለጸው የኢትዮጵያ መንግሥት በንግድ ባንኮች ላይ የተጣለውን አስገዳጅ የ20 በመቶ የግምጃ ቤት ቦንድ ግዥ በሰኔ 2017 ዓ.ም. ሙሉ በሙሉ እንደሚያነሳ ማረጋገጡ ነው፡፡ በተያዘው ዓመት ግን ሁሉም ባንኮች ከሚፈጽሙት አስገዳጅ የቦንድ ግዥ 55 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን፣ መንግሥት ለአይኤምኤፍ መግለጹ ተጠቁሟል፡፡
ገበያ መር የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ከተከፈተ 3.1 ቢሊዮን ዶላር ሌተር ኦፍ ክሬዲት (LC) ውስጥ እስካሁን ያልተከፈለውን ቀሪ 2.5 ቢሊዮን ዶላር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ለሎች የግል ባንኮች በጋራ እንደሚከፍሉት፣ የተቀረውን ደግሞ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ በማቅረብ እንደሚወጣው ታውቋል፡፡
https://www.ethiopianreporter.com/135167/
የአይኤምኤፍ ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የቦርዱ ሰብሳቢ ቦ ሊ እንዳስታወቁት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በብሔራዊ ባንክ አማካይነት ሲደረጉ የቆዩ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይ የሚደረጉ ጣልቃ ገብነትን የመቀነስ ተግባራት አጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡
አይኤምኤፍ በአራት ዓመታት የ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ የብድር አቅርቦት በተመለከተ ባለፈው ወር ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነት ላይ መድረሱ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህንንም ተከትሎ የተቋሙ ቦርድ 340.7 ሚሊዮን ዶላር ፈቅዷል፡፡
ሌላው በሪፖርቱ የተገለጸው የኢትዮጵያ መንግሥት በንግድ ባንኮች ላይ የተጣለውን አስገዳጅ የ20 በመቶ የግምጃ ቤት ቦንድ ግዥ በሰኔ 2017 ዓ.ም. ሙሉ በሙሉ እንደሚያነሳ ማረጋገጡ ነው፡፡ በተያዘው ዓመት ግን ሁሉም ባንኮች ከሚፈጽሙት አስገዳጅ የቦንድ ግዥ 55 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን፣ መንግሥት ለአይኤምኤፍ መግለጹ ተጠቁሟል፡፡
ገበያ መር የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ከተከፈተ 3.1 ቢሊዮን ዶላር ሌተር ኦፍ ክሬዲት (LC) ውስጥ እስካሁን ያልተከፈለውን ቀሪ 2.5 ቢሊዮን ዶላር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ለሎች የግል ባንኮች በጋራ እንደሚከፍሉት፣ የተቀረውን ደግሞ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ በማቅረብ እንደሚወጣው ታውቋል፡፡
https://www.ethiopianreporter.com/135167/
-
- Member
- Posts: 4207
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Re: IMF to release first evaluation report on Ethiopia’s Macroeconomic Reform
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዓመታት እያበደረ ሳይመለስለት የቀረና ከእነ ወለዱ የተጠራቀመ ከ845 ቢሊዮን ብር በላይ ለመክፈል፣ መንግሥት የቦንድ ሽያጭ እንዲፈጽም የሚፈቅድለት አዋጅ በፓርላማው ፀደቀ፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች አበድሮ ካልተመለሰለት አጠቃላይ ዕዳው ውስጥ በመጀመሪያ ዙር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ብድር 3.25 ቢሊዮን ብር፣ እንዲሁም ወለድ ብር 120 ሚሊዮን በአጠቃላይ 3.369 ቢሊዮን ብር፣ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ብድር 92.3 ቢሊዮን ብር፣ እንዲሁም ወለዱ 9.3 ቢሊዮን ብር፣ በድምሩ 101.7 ቢሊዮን ብር፣ የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ብድር 11.478 ቢሊዮን ብር፣ እንዲሁም ወለዱ 4.9 ቢሊዮን ብር በድምሩ 16.4 ቢሊዮን ብር መሆኑ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም በሁለተኛው ዙር አበድሮ ካልተመለሰለት ውስጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ብድር ብር 179.2 ቢሊዮን፣ እንዲሁም ወለድ 12.5 ቢሊዮን ብር በድምሩ 191.7 ቢሊዮን ብር፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ብድር 68.6 ቢሊዮን ብር፣ እንዲሁም ወለድ 4.205 ቢሊዮን ብር፣ በድምሩ 72.8 ቢሊዮን ብር በአጠቃላይ ስድስት የልማት ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደሩትን ዋና ብድር 365.2 ቢሊዮን ብር፣ እንዲሁም የተጠራቀመ ወለድ ብር 33.4 ቢሊዮን በድምሩ ብር 398.6 ቢሊዮን ብር ዕዳ ይገኝበታል፡፡
በተጨማሪም በተፈረሙ የዕዳ ማስተላለፊያ ስምምነቶች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ያበደራቸውና ተመልሰው ያልተከፈሉ ዕዳዎች ውስጥ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ብድር 3 ቢሊዮን ብር ወለዱ 5.9 ቢሊዮን ብር፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ብድር 3 ቢሊዮን ብር ወለዱ 4.3 ቢሊዮን ብር፣ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ብድር 5.2 ቢሊዮን ብር ወለዱ 1 ቢሊዮን ብር፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ዋና ብድር 1.4 ቢሊዮን ብር ወለዱ 4 ቢሊዮን ብር ናቸው፡፡
https://www.ethiopianreporter.com/135161/