በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች እና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት «በርካታ» ሕፃናት ከትምህርት ውጪ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዐሳውቋል ።
በተከሰቱ ግጭቶች እና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት «በርካታ» ሕፃናት ከትምህርት ውጪ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዐሳውቋል ። ኮሚሽኑ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብት ሁኔታዎችን በሚመለከት ባወጣው ዓመታዊ ዘገባ «ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል ።» ኮሚሽኑ ከሰኔ 2015 እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም ድረስ ባደረገው የመረጃ ማጣራት በስምንት ክልሎች ውስጥ 5,568 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን መመልከቱን ይፋ አድርጓል ።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በዝርዝር ባስቀመጠው መረጃ «በበርካታ አካባቢዎች ለመምህራንም ሆነ ለተማሪዎች አስተማማኝ የጸጥታ ሁኔታ ባለመኖሩ» የትምህርት መብት እጅግ ተጎድቷል ።
በኮሚሽኑ የሲቪል፣ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር አብዲ ጅብሪል የዚህ ሁሉ ችግር መነሻው ዋናው በመንግሥት እና በታጣቂዎች የሚደረግ ግጭት ሲሆን የተፈጥሮ አደጋዎችም ቀላል ግምት የሌለው ተጽእኖ አድርሰዋል። ኮሚሽኑ አንዳንድ ባላቸው አካባቢዎች መምህራን ትምህርት ቤት ውስጥ ለመገኘት በተለይም ሴት መምህራን "የመደፈር እና የመዘረፍ ሥጋት" ያለባቸው በመሆኑ ትምህርት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን አመልክቷል።
ሰሞኑን የአጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ባደረገው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሄው የመምህራን ጉዳይ ተነስቶ ነበር።
https://www.dw.com/am/%E1%8A%A2%E1%88%B ... a-70724708