Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 34058
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by Horus » 07 Oct 2024, 15:42


በእኔ እይታ በውጭ ጉዳዩ ላይ የተደረገው ሹም ሽር ነው። ይህ ስልጣን አልባ የፕሬዚዳንትነት ወንበር ሰዎችን ለጡረታ ማባረሪያ ፉዛን ነው። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ በህልቁ መሳፍርት ውጥረቶች በሚገኝበት በዚህ ወቅት የውጭ ጉዳዩን ማንሳት ማለት ሰውዬው ቦታውን አልቻለውም ማለት ወይም በአቢይ አህመድ አይታመንም ማለት ነው። ይህም ሆነ ያ ዛሬ ላይ የውጭ ጉዳት ሚንስትር ከመሆን የላቀ ስልጣን በኢትዮጵያ የለም። ስለዚህ አምባሳደር ታዬ ላይ ሹም ሸር ነው አቢይ የፈጸመው ። ለዚህ ደሞ ብዙ ምክንያቶችን መገመት ይቻላል። አምባሳደሩና አቢይ የእድሜና የፐርሶናሊቲ ሰፊ ልዩነት አላቸው ። እንደ የስራ ጓዶች አብረው የሚሰሩ አይነት አይደሉም፣ ይህ ብቻ ሳይሆን አቶ ታዬ አቢይ እንደ ሌሎቹ አሽከሮቹ አገላብጦ የሚቆጣቸው አይነት ሰው አይደሉም፤ ስለዚህ ግዙፍ የባህሪ ኬሚስትሪ ልዩነት አላቸው። ሌላው ሊሆን የሚችለው ምክኛት ሱማሌ በጣም ተናዳፊ የሆነ የውጭ ሚኒስትር ነው ያላት። ያምባሳደር ለስላሳ ጸባይና የሱማሌው አቻቸው እስታይል ፍጹም የተለያዩ ናቸው ። አቢይ ተመሳሳይ ተርብ ባህሪ ያለው የውጭ ምኒስትር ፈልጎ ይሆናል ። ማን እንደ ሚሆን እናያለን። ታከለ ኡማ ቦታውን ለመለመን የሆነ ቴክስት ስለ ቀይ ባህር ግጥም ከለጠፈ በኋል መስሎ ደለዘው ። የውጭ ጉዳዩን ቦታ ለመያዝ ኦርሙማዎች ውስጥ መጋጋጥ አለ ማለት ነው።
Last edited by Horus on 07 Oct 2024, 16:27, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 34058
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by Horus » 07 Oct 2024, 16:06

WHO WILL BE THE NEXT FOREIGN MINISTER?
SAJIDS'S SPECULATION - 1 OF THE THESE 3 PEOPLE
Berhanu Nega
Redwan Hussien
Getachew Reda

we shall see.
Last edited by Horus on 07 Oct 2024, 16:19, edited 1 time in total.

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 11624
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by DefendTheTruth » 07 Oct 2024, 16:18

Horus wrote:
07 Oct 2024, 15:42

በእኔ እይታ በውጭ ጉዳዩ ላይ የተደረገው ሹም ሽር ነው። ይህ ስልጣን አልባ የፕሬዚዳንትነት ወንበር ሰዎችን ለጡረታ ማባረሪያ ፉዛን ነው። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ በህልቁ መሳፍርት ውጥረቶች በሚገኝበት በዚህ ወቅት የውጭ ጉዳዩን ማንሳት ማለት ሰውዬው ቦታውን አልቻለውም ማለት ወይም በአቢይ አህመድ አይታመንም ማለት ነው። ይህም ሆነ ዛሬ ላይ የውጭ ጉዳት ሚንስትር ከመሆን የላቀ ስልጣን በኢትዮጵያ የለም። ስለዚህ አምባሳደር ታዬ ላይ ሹም ሸር ነው አቢይ የፈጸመው ። ለዚህ ደሞ ብዙ ምክንያቶችን መገመት ይቻላል። አምባሳደሩና አቢይ የእድሜና የፐርሶናሊቲ ሰፊ ልዩነት አላቸው ። እንደ የስራ ጓዶች አብረው የሚሰሩ አይነት አይደሉም፣ ይህ ብቻ ሳይሆን አቶ ታዬ አቢይ እንደ ሌሎቹ አሽከሮቹ አገላብጦ የሚቆጣቸው አይነት ሰው አይደሉም፤ ስለዚህ ግዙፍ የባህሪ ኬሚስትሪ ልዩነት አላቸው። ሌላው ሊሆን የሚችለው ምክኛት ሱማሌ በጣም ተናዳፊ የሆነ የውጭ ሚኒስትር ነው ያላት። ያምባሳደር ለስላሳ ጸባይና የሱማሌው አቻቸው እስታይል ፍጹም የተለያዩ ናቸው ። አቢይ ተመሳሳይ ተርብ ባህሪ ያለው የውጭ ምኒስትር ፈልጎ ይሆናል ። ማን እንደ ሚሆን እናያለን። ታከለ ኡማ ቦታውን ለመለመን የሆነ ቴክስት ስለ ቀይ ባህር ግጥም ከለጠፈ በኋል መስሎ ደለዘው ። የውጭ ጉዳዩን ቦታ ለመያዝ ኦርሙማዎች ውስጥ መጋጋጥ አለ ማለት ነው።
አናላይዝ አርገህ ሞተሃል፣ አምባሳደሩ የአንተን አይነቶች ቆዩ እኮ ቦኋልተኞች ብሎ የሰየሙአችዉ። የታላቅቷ ኢትዮጵያ ፕረዝዳንት መሆን ስሙ ብቻ ከበቂ በላይ ነዉ፣ የሳቸዉ ብቃት ነ ብስለት ስጨመርበት ደግሞ ትልቅ እድል ነዉ፣ ቁጭ ሞነጫጭር፣ የመጠልህን ሁሉ፣ እንደ ድኩማን!

እስኪ የአዲሱን ፕረዝዳንት ንግግር እንሰማና የአንተን መሞነጫጫር ተመልሰን እናንብብ፣ ምኑን ከምኑ እናገናኝ ታዲያ?



even your source of information is beyond my comprehension, you are so good as your source, nothing more.

Horus
Senior Member+
Posts: 34058
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by Horus » 07 Oct 2024, 16:24

DDT,
You are a PP cadre. The president simply reads the numbers and figures given to him. The president is a powerless ceremonial position good for those retired and values of symbolism. You are incapable grasping such concept because you are new to politics and a blind cadre.

Abere
Senior Member
Posts: 12696
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by Abere » 07 Oct 2024, 16:34

ሆረስ
በእውነቱ ለአብይ አህመድ ታዬ አጽቀስላሴን ከ large intestine ደንዳኔ አንጀት (ቆሻሻተካሚነት) ወደ በሆድዕቃ የተቀመጠ ትርፍ አንጄትነት ነው የተቀየረው። He will have no role at all. የሳሎን ሴት ወይዘሮ ሁኖት አረፈ እንጅ፡ :lol: የአብይ ስርዐት ሲሞት አብሮ የሚሞት። እንደ እኔ ታዬ አብይ አህመድ በጠበቀው ደረጃ የውጭ ጉዳይ ስራውም መላላክ እና በብቃት መወጣት አልችል ብሎ ይመስለኛል።

Horus
Senior Member+
Posts: 34058
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by Horus » 07 Oct 2024, 16:54

Abere wrote:
07 Oct 2024, 16:34
ሆረስ
በእውነቱ ለአብይ አህመድ ታዬ አጽቀስላሴን ከ large intestine ደንዳኔ አንጀት (ቆሻሻተካሚነት) ወደ በሆድዕቃ የተቀመጠ ትርፍ አንጄትነት ነው የተቀየረው። He will have no role at all. የሳሎን ሴት ወይዘሮ ሁኖት አረፈ እንጅ፡ :lol: የአብይ ስርዐት ሲሞት አብሮ የሚሞት። እንደ እኔ ታዬ አብይ አህመድ በጠበቀው ደረጃ የውጭ ጉዳይ ስራውም መላላክ እና በብቃት መወጣት አልችል ብሎ ይመስለኛል።
በትክክል፤ በእኔ ግምት ነገሩ ከወደቡ ስምምነት የተያያዘ ይመስለኛል። አምብሳደር ታዬ የድሮ አይነት ዲፕሎማት ስለሆነ የአቢይን መንቀዥቀዝና በደመነፍስ የሚወስዳቸው የውጭ ጉዳይ ነገሮች፣ ከኢሚራትም ጋር ያለው መርህ አልባ የግል ዝምድና መሰል ፖሊሲዎች ሁሉ አቶ ታዬን የሚያበሳጨው ይመስለኛል። ስምምነት እንደ ሌላቸው ግልጽ ነው ።

Selam/
Senior Member
Posts: 13888
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by Selam/ » 07 Oct 2024, 18:17

ገና በ68 ዓመቱ እንግዳ አስተናጋጅና ለቅሶ ደራሽ ተደርጎ መሰየሙ ሹመት ሳይሆን ዝርጠጣ ነው።

ጌታቸው ረዳ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ይሆናል ብሎ መጠበቅ ቅዠት ነው። አቶ አብዮት ወያኔዎችን ፍፁም ስለማያምናቸው፣ ይኸንን ቁልፍ ቦታ አሳልፎ አይሰጣቸውም።

Horus
Senior Member+
Posts: 34058
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by Horus » 07 Oct 2024, 20:05

በእኔ ግምት አቢይ የሚሾመው አንድም ሙስሊም ሆኖ አረብኛ የሚችል (ያቢይ ገንዘብ ሁሉ የሚመጣው ከአረቦች ስለሆነ) አለያም ካውሮፓና አሜሪካ ሊያስጠጋው የሚችል ሰው ይመስለኛል። ዛሬ አቢይ ችግር ያለው ካውሮፓ/አሜሪካና ግብጽ ጋር ስለሆነ ። ኦሮሞቹ ካፍሪካ ሕብረት ጋርም ችልግ አላቸው።

sun
Member+
Posts: 9582
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by sun » 07 Oct 2024, 21:46

Horus wrote:
07 Oct 2024, 16:06
WHO WILL BE THE NEXT FOREIGN MINISTER?
SAJIDS'S SPECULATION - 1 OF THE THESE 3 PEOPLE
Berhanu Nega
Redwan Hussien
Getachew Reda

we shall see.

Under the current circumstance the foreign minister needs to be young, energetic, loyal, verbal, analytical, oratorical, diplomatic and bright sunshine even during seasons of darkness so as to instill hope and all the goodies in the world. I like Dr. Behanu but as an old academic he may be too old and not a spontaneous oratorical bright sunshine so as to put up tough verbal dwellings and bring light and hope to the table. Foreign ministers and diplomats may in the future need to take some courses in theatrical performances and drama staging so that they may be able to attract and capture public attention and lead to their logical arguments and its conclusion.

One good example is the former Iraqi foreign minister named Mohammed Saeed al-Sahhaf, Iraqi former diplomat and politician. He served as Minister of Foreign Affairs from 1992 to 2001. He came to worldwide prominence around the 2003 invasion of Iraq, during which he was the Minister of Information under Iraqi President Saddam Hussein, acting as spokesman for the Arab Socialist Ba'ath Party and Saddam's government. He is the type of orator who can make even the Pigs fly, so to say.
:lol:

Last edited by sun on 07 Oct 2024, 22:47, edited 6 times in total.

Selam/
Senior Member
Posts: 13888
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by Selam/ » 07 Oct 2024, 22:19

ጭልፊቱ - አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ አረብ፥ ታዲያ ከአማራጮቹ ውስጥ ምን አስተረፍክ? :lol:

ልክ እኮ “ወይ ይነጋል ያ ካልሆነ ደግሞ ይመሻል” የሚል የሚመስል ዓይነት አማራጭ ነው ያቀረብከው።

Horus wrote:
07 Oct 2024, 20:05
በእኔ ግምት አቢይ የሚሾመው አንድም ሙስሊም ሆኖ አረብኛ የሚችል (ያቢይ ገንዘብ ሁሉ የሚመጣው ከአረቦች ስለሆነ) አለያም ካውሮፓና አሜሪካ ሊያስጠጋው የሚችል ሰው ይመስለኛል። ዛሬ አቢይ ችግር ያለው ካውሮፓ/አሜሪካና ግብጽ ጋር ስለሆነ ። ኦሮሞቹ ካፍሪካ ሕብረት ጋርም ችልግ አላቸው።

Selam/
Senior Member
Posts: 13888
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by Selam/ » 07 Oct 2024, 22:22

ወሮ ጠሃይቱ - ስንት ላሞች እንዲኖረው ትፈልጊያለሽ?
sun wrote:
07 Oct 2024, 21:46

sun
Member+
Posts: 9582
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by sun » 07 Oct 2024, 22:50

Selam/ wrote:
07 Oct 2024, 22:22
ወሮ ጠሃይቱ - ስንት ላሞች እንዲኖረው ትፈልጊያለሽ?
sun wrote:
07 Oct 2024, 21:46
[/color]698]
666 ላሞች. Your nightmare!

Horus
Senior Member+
Posts: 34058
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by Horus » 07 Oct 2024, 22:55

Selam/ wrote:
07 Oct 2024, 22:22
ወሮ ጠሃይቱ - ስንት ላሞች እንዲኖረው ትፈልጊያለሽ?
sun wrote:
07 Oct 2024, 21:46
sun,
ካንተ ጋር ብዙ የመስማማት ፍላጎት ባይኖረኝ 50% ትክክል ነህ ፣ እኔም አቢይና አምባሳደር ታዬ የማያስማማ ያልኩት በጥቂቱ ያልካቸው ነገሮች ናቸው ። የድርጅት መሪዎች አንድ ቲም ስለሆኑ ኬሚስትሪ ያልኩት ያንን ነው። ሲጂድ ባለ ዩቱበሩ ብርሃኑ ነጋን የጠቀሰበት የሚመስለኝ ፣ የአንድ አገር ውጭ ሚኒስትር ጉልበትና ፍጥነት ብቻ ሳይሆን ኮምፕሌክስ የሆነን ሁኔታና ችግርን በጥልቀትና ሲስተማቲክ በሆነ መንገድ የሚገባው ፣ 180 አገሮች ኢክኖሚና ፖለቲካን በምርምርና ዳታ ላይ የተመሰረተ ግንዛቤን መያዝ የሚችል ጥብቅ ኢነተለክቿል ችሎታ ያለው ሰው መሆን አለበት ።

ሌላው እጅግ ግዙፍ ቢሮክራሲን የማስተዳደርና የሲስተም ቲንኪንግ ልምድና ችሎታ ያለው ሰው መሆን አለበት ። የቋንቋ ችሎታ እንዳለ ሆኖ ። ሌላው ያ ሰው በአለም ደረጃ ያለው ቁመና እስታቹር በጣም አስፈላጊ ነው። ብርሃኑ ነጋ አሜሪካንን ሆነ አውሮፓን በጣም ያውቁታል። ይህ ማለት ግን አቢይ ይህን ቦታ ከብልጽኛ ውጭ ይሰጣል ማለት አይደለም ። ብርሃኑ በቅርብ ለምናውቀው ባመነበት ነገር ግትርና ኩሩ ሰው ነው። ሰው እንደ ሚለው አይደለም፣ ብርሃኑ ታዛዥ ቢሮክራት አይደለም፣ ትሁት ሰው ነው ግን ተራ ታዛዥ አይደለም ። በዚህ ብቻ አቢይ ላያስጠጋው ይፈልግ ይሆናል።

ከዚያ በተረፈ አንተ ዲስክራብ ያደረከው ሰው አስቤው የለም። ጮሌና ካድሬ ብዙ ብዙ አሉ። ግዙፍ እውቀትና ወጣትነት ያካተተ ለአለም አገሮች ተቀባይነት ያለው እውቅ ወጣት ዲፕሎማት ቢኖር እናውቀው ነበር።

ለማንኛውም የሚታይ ይሆናል! እንደ ታከለ ኡማ ያለ ገመድ አፍን ሊሾም ይችላል! የጎሳ ድራማ ሰልሆነ!

Wedi
Member+
Posts: 8365
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by Wedi » 07 Oct 2024, 23:00


አብይ አህመድ ይህን ተላላኪ ኩርንችች ከውጭ ጉዳይ ስልጣኑ ያነሳው የውጭ ጉዳይ ወንበሩን ለሌላ ተላላኪ ጌታቸው ረዳ ለመስጠት ስለፈለገ ነው። እውነታው ይኸው ነው::


Horus wrote:
07 Oct 2024, 15:42

በእኔ እይታ በውጭ ጉዳዩ ላይ የተደረገው ሹም ሽር ነው። ይህ ስልጣን አልባ የፕሬዚዳንትነት ወንበር ሰዎችን ለጡረታ ማባረሪያ ፉዛን ነው። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ በህልቁ መሳፍርት ውጥረቶች በሚገኝበት በዚህ ወቅት የውጭ ጉዳዩን ማንሳት ማለት ሰውዬው ቦታውን አልቻለውም ማለት ወይም በአቢይ አህመድ አይታመንም ማለት ነው። ይህም ሆነ ያ ዛሬ ላይ የውጭ ጉዳት ሚንስትር ከመሆን የላቀ ስልጣን በኢትዮጵያ የለም። ስለዚህ አምባሳደር ታዬ ላይ ሹም ሸር ነው አቢይ የፈጸመው ። ለዚህ ደሞ ብዙ ምክንያቶችን መገመት ይቻላል። አምባሳደሩና አቢይ የእድሜና የፐርሶናሊቲ ሰፊ ልዩነት አላቸው ። እንደ የስራ ጓዶች አብረው የሚሰሩ አይነት አይደሉም፣ ይህ ብቻ ሳይሆን አቶ ታዬ አቢይ እንደ ሌሎቹ አሽከሮቹ አገላብጦ የሚቆጣቸው አይነት ሰው አይደሉም፤ ስለዚህ ግዙፍ የባህሪ ኬሚስትሪ ልዩነት አላቸው። ሌላው ሊሆን የሚችለው ምክኛት ሱማሌ በጣም ተናዳፊ የሆነ የውጭ ሚኒስትር ነው ያላት። ያምባሳደር ለስላሳ ጸባይና የሱማሌው አቻቸው እስታይል ፍጹም የተለያዩ ናቸው ። አቢይ ተመሳሳይ ተርብ ባህሪ ያለው የውጭ ምኒስትር ፈልጎ ይሆናል ። ማን እንደ ሚሆን እናያለን። ታከለ ኡማ ቦታውን ለመለመን የሆነ ቴክስት ስለ ቀይ ባህር ግጥም ከለጠፈ በኋል መስሎ ደለዘው ። የውጭ ጉዳዩን ቦታ ለመያዝ ኦርሙማዎች ውስጥ መጋጋጥ አለ ማለት ነው።

Selam/
Senior Member
Posts: 13888
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by Selam/ » 07 Oct 2024, 23:02

ወሮ ጠሃይቱ - እኔ “እንቧ!” በይ እንጂ ያልኩት መቼ “የክርስትና ስምሽን” ንገሪኝ አልኩኝ።

sun wrote:
07 Oct 2024, 22:50
Last edited by Selam/ on 07 Oct 2024, 23:16, edited 1 time in total.

Misraq
Senior Member
Posts: 14159
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by Misraq » 07 Oct 2024, 23:03

ትግሬዎች በኦሮም ሕዝብ ላይ ሲያላግጡ ኦሮሞዎቹን ነጋሶ ጊዳዳን ፤ ግርማ ወልደ ጊዬርጊስን በፕሬዘዳንትነት እየሾሙ ኦሮሞ ስልጣን ላይ ነው እያሉ ያላግጡ ነበር። ይህ ያተረፈላቸው friend ሳይሆን ጠላትን ነው።

ከትግሬ ስህተት ያልተማሩ ኦሮሞዎች ደግሞ አማራ ላይ ሲያላግጡ ይሃው በ6 አመት ውስጥ ሁለት ሆዳም አማራ ሾመው አማራም አብሮ እየመራ ነው እያሉ ነው። የሚያተርፍላቸው ጥላቻን ቁጭትን እና በቀልን እንጂ ምንም ትርፍ አያገኙበትም።

ኦሮሞ ብልፅግናን ካልታገለ አደገኛ ቅርቃር ውስጥ ይገባል

sun
Member+
Posts: 9582
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by sun » 07 Oct 2024, 23:04

Abere wrote:
07 Oct 2024, 16:34
ሆረስ
በእውነቱ ለአብይ አህመድ ታዬ አጽቀስላሴን ከ large intestine ደንዳኔ አንጀት (ቆሻሻተካሚነት) ወደ በሆድዕቃ የተቀመጠ ትርፍ አንጄትነት ነው የተቀየረው። He will have no role at all. የሳሎን ሴት ወይዘሮ ሁኖት አረፈ እንጅ፡ :lol: የአብይ ስርዐት ሲሞት አብሮ የሚሞት። እንደ እኔ ታዬ አብይ አህመድ በጠበቀው ደረጃ የውጭ ጉዳይ ስራውም መላላክ እና በብቃት መወጣት አልችል ብሎ ይመስለኛል።
You are just a low IQ savage bandit bum who is jealous and envious just like a street corner cheap twerking professional.

Congratulations to ato Taye for being chosen and becoming the head of state in this historical country of some 120 million people. A once in a life great chance.



Last edited by sun on 07 Oct 2024, 23:11, edited 1 time in total.

Wedi
Member+
Posts: 8365
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by Wedi » 07 Oct 2024, 23:08

Horus wrote:
07 Oct 2024, 16:06
WHO WILL BE THE NEXT FOREIGN MINISTER?
SAJIDS'S SPECULATION - 1 OF THE THESE 3 PEOPLE
Berhanu Nega
Redwan Hussien
Getachew Reda

we shall see.
በጣም ጥሩ ግምት ነው። አብይ አመድ ሬድዋን ሁሴንን ፈፅሞ አያምነውም። ሬድዋን ሁሴን is pro TPLF and diehard TPLF loyalist.

sun
Member+
Posts: 9582
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by sun » 07 Oct 2024, 23:20

Wedi wrote:
07 Oct 2024, 23:08
Horus wrote:
07 Oct 2024, 16:06
WHO WILL BE THE NEXT FOREIGN MINISTER?
SAJIDS'S SPECULATION - 1 OF THE THESE 3 PEOPLE
Berhanu Nega
Redwan Hussien
Getachew Reda

we shall see.
በጣም ጥሩ ግምት ነው። አብይ አመድ ሬድዋን ሁሴንን ፈፅሞ አያምነውም። ሬድዋን ሁሴን is pro TPLF and diehard TPLF loyalist.
Liar, liar, liar...
your old tattered pants are on hot fire,
Your pathological liar lips are rusty like the old barbed wire!

Dim witted baboon cheap bandit bum thinks that he can divide and attack the LIONS.
:mrgreen:

Selam/
Senior Member
Posts: 13888
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሹመት ወይስ ሽረት?

Post by Selam/ » 07 Oct 2024, 23:29

በሆዱና በደሙ እንጂ በአይሞሮው የሚያስብና ልቦና ያለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይሾማል ብለህ አትድከም።

የወደፊቱን ቅራቅንቦ ለማየት የኋላውን ቅራቅንቦ ማየት ነው፥

Seyoum Mesfin
Hailemariam Desalegn
Berhane Gebre-Christos
Tedros Adhanom
Workneh Gebeyehu
Gedu Andargachew
Demeke Mekonnen
Taye Atskeselassie

Post Reply