Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9509
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ የነፃነት ያለህ እያሉ ነው። .... አብይ አሕመድ መግቢያ መውጫ አሳጣኝ ብለዋል

Post by MINILIK SALSAWI » 05 Oct 2024, 13:18

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ የነፃነት ያለህ እያሉ ነው። ............ የአብይ አሕመድ አገዛዝ በዜጎች ላይ የሚያደርሰው እንግልት እና አፈና ፕሬዝዳንቷ በቂ ማሳያ ናቸው። ........ ፕሬዝዳንቷ ነፃነታቸውን ከማጣታቸው የተነሳ በሚደርስባቸው አፈና መማረራቸውን ተናግረዋል። ...... ከሚኖሩበት ቤተመንግስት አውጥቶ በራሱ መኖሪያ ፊት ለፊት በመውሰድ ነጻነታቸውን ከማጣታቸው በተጨማሪ ከውጪ የሚያሳይ ከውስጥ የማያሳይ መስታወት በመኖሪያቸው ላይ በመግጠም ግለሰባዊ ነፃነታቸውን እየተጋፋ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሰምተናል። ...... ፕሬዝዳንቷም የነፃነት ያለህ ሲሉ በተዳጋጋሚ ተንፍሰዋል። ..... መውጫና መግቢያ እንዳጡም ተናግረዋል። ..... ይህ ሁሉ የመጣባቸው ስለ ሰላም እና ስለ ሰው ልጅ መብቶች በመናገራቸው ነው። ፕሬዝዳንቷ ነፃነታቸውና መብታቸው ተመልሶ ዝም ያሉበትን እንዲናገሩ ይሁን። #MinilikSalsawi
Please wait, video is loading...
ለአንድ ዓመት ሞከርኩት ”

ዛሬ በይፋዊ የፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የX ገጽ ላይ የወጣው ፅሁፍ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።

ፅሁፉ ” እነ ጥላሁን ገሠሠ : ቴዲ አፍሮ : አሊ ቢራ : ማህሙድ አህመድ … ድንቅ ድምጻውያን መካከል ናቸው ” ይላል።

ቀጥል አድርጎ ፥ ” ‘ የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው : መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው ‘ ማህሙድ ‘ ዝምታ ነው መልሴ’ ን ሲያዜም ” ሲል ይገልጻል።

መጨረሻ ላይ ” ለአንድ ዓመት ሞከርኩት ” የሚል ያልተቋጨ ፅሁፍ ታክሎበታል።

ፕሬዜዳንቷ ገጽ ላይ ፅሁፉ ስለምን ጉዳይ እንደሆነ በግልጽ የተብራራ ነገር አልሰፈረም።

በተረጋገጠው አካውንታቸው የወጣውን ፅሁፍ ግን በርካቶች እየተቀባበሉት ይገኛሉ።

Odie
Member
Posts: 2174
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ የነፃነት ያለህ እያሉ ነው። .... አብይ አሕመድ መግቢያ መውጫ አሳጣኝ ብለዋል

Post by Odie » 05 Oct 2024, 13:43

እንደቁራአትጬሂ መልቀቅ ትችያለሽ በላት ያችን ቁርንባጥ!
ዘረኞችን መሽከም ልምዱዋ ስለሆነ ወይ ዝም በይ በላት!
ከስሞኑ ልትለቅ ነው ከሳምንት በሁዋል ሲባል አልነበረም?

MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9509
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ የነፃነት ያለህ እያሉ ነው። .... አብይ አሕመድ መግቢያ መውጫ አሳጣኝ ብለዋል

Post by MINILIK SALSAWI » 05 Oct 2024, 23:18

Odie wrote:
05 Oct 2024, 13:43
እንደቁራአትጬሂ መልቀቅ ትችያለሽ በላት ያችን ቁርንባጥ!
ዘረኞችን መሽከም ልምዱዋ ስለሆነ ወይ ዝም በይ በላት!
ከስሞኑ ልትለቅ ነው ከሳምንት በሁዋል ሲባል አልነበረም?
https://mereja.com/amharic/v2/1015418

Post Reply