Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Digital Weyane
Member+
Posts: 9447
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

በ BBC ውስጥ ተሰግስገው የሚገኙ እሳት የላሱ የህወሓት ካድሬዎቻችን ለግብፅ ያላቸውን ፍቅርና ድጋፍ በተራቀቀ መንገድ አሳዩ

Post by Digital Weyane » 08 Sep 2024, 10:24

የኢትዮጵያ እና የግብጽ ወታደራዊ አቅም እንዴት ይነጻጸራል?



3 መስከረም 2024

አባይ ወንዝ ላይ ተገንብቶ እየተጠናቀቀ ባለው የሕዳሴ ግድብ ምክንያት ውዝግብ ውስጥ የቆዩት ግብጽ እና ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከየትኛውም ጊዜ የበለጠ ውጥረት ውስጥ ገብተዋል።

በተፈጥሯዊ ድንበር የማይገናኙት ሁለቱ አገራት፤ የግብጽ ጦር ሶማሊያ መግባቱን ተከትሎ አዲስ አበባ እና ካይሮ ፊት ለፊት ተፋጥጠዋል።

ከሰሞኑ በግብጽ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ውጥረት ያየለው ግብጽ እና ሶማሊያ የደረሱትን ወታደራዊ ስምምነት ተከትሎ ጦር መሳሪያ የያዙ የግብጽ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ሞቃዲሾ ካረፉ በኋላ ነው።

የአውሮፕላኖቹን መምጣት ተከትሎ ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የግብጽ ጦር በሶማሊያ እንዲሰማራ መደረጉ ለሶማሊያ እና ለአጠቃላዩ የአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት እና ደኅንነት አሳሳቢ ነው በማለት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የሶማሊያ መንግሥት “ቀጠናውን ለማተራመስ ከሚሹ የውጭ ኃይሎች ጋር እየሠራ ይገኛል” ማለቱ ይታወሳል።

ባለፉት ቀናት ግብጽ በበኩሏ የውሃ ድርሻዬን ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ከመውሰድ ወደ ኋላ አልልም ስትል ማሳሰቢያ አዘል ደብዳቤ ለፀጥታው ምክር ቤት ልካለች።

በአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለፀጥታው ምክር ቤት በተላከ ደብዳቤ ላይ “ግብጽ ሕልውናዋን ለመከላከል እና የሕዝቦቿን ጥቅም ለማስከበር በተባበሩት መንግሥታት ቻርተር መሠረት ሁሉንም እርምጃዎች ለመውሰድ ዝግጁ ናት” ተብሏል።



የግብጽ እና የኢትዮጵያ ወታደራዊ አቅም

የኢትዮጵያ ጦር ባለፉት አስርት ዓመታት በተለያዩ የአገር ውስጥ እና የውጭ ጦርነቶች ውስጥ አልፏል።

ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጦርነት እንዲሁም ከሁለት ዓመታት በፊት ያበቃው ደም አፋሳሹ የሰሜን ኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ዋነኞቹ ሲሆኑ፣ ከዚህ ባሻገርም የአገሪቱ ሠራዊት በተለያዩ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ውስጥ ተሳትፏል።

በቅርብ የተደረገው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በሰው እና በንብረት ላይ ካደረሰው ውድመት ባልተናነሰ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ ቀላል የማይባል ጉዳትን ማስከተሉ አይቀሬ ነው።

በአንጻሩ የግብጽ ጦር ባለፉት 40 ዓመታት ጉልህ በሆነ ጦርነት ላይ ሳይሳተፍ በምዕራባውያን አገራት ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ሲደራጅ ቆይቷል።

የግብጽ ጦር በጥቂት ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራዊቱን ያጣበት ወታደራዊ ዘመቻ ያካሄደው በሲናይ በረሃ ከኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) ሰርጎ ገቦች ጋር ባደረገው ግጭት ነው።

ኢስላሚክ ስቴት በሲናይ በረሃ በግብጽ የፀጥታ አካላት ላይ የከፈተውን ወታደራዊ ዘመቻ ተከትሎ ከእኤአ 2013 አንስቶ 3200 የሚሆኑ የግብጽ ጦር እና የፖሊስ አባላት መገደላቸውን በአንድ ወቅት ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ተናግረው ነበር።

የግብጽ ጦር በሲናይ በረሃ ከእስላማዊ ቡድኖች ጋር ከሚያደርገው ውጊያ ውጪ ይህ ነው ሊባል በሚችል በቅርብ ጊዜ በሙሉ ወታደራዊ ውጊያ ውስጥ አልተሳተፈም።

የአገራትን አጠቃላይ ወታደራዊ አቅም በመመዘን ደረጃን የሚሰጠው ግሎባል ፋየር ፓዎር፤ በ2024 ዕትሙ የአገራትን ከሠራዊት ብዛት እስከ ትጥቃቸው ድረስ በመፈተሽ የወታደራዊ አቅም ደረጃን ይሰጣል።

የ145 አገራትን ወታደራዊ አቋም በመመዘን በየዓመቱ ደረጃ የሚያወጣው ግሎባል ፋየር ፓወር፣ ለምዘናው 60 ያህል የመገምገሚያ ነጥቦችን ይጠቀማል።

እነዚህ መመዘኛዎችም አገራት ያሏቸው ወታደራዊ ክፍሎች ብዛት፣ ሠራዊቱ የታጠቃቸው ወታደራዊ ትጥቆች፣ ለሠራዊታቸው የሚመድቡት ዓመታዊ በጀት፣ ለሠራዊታቸው የሚያስፈልጉትን አቅርቦቶች በተገቢው እና በአስፈላጊው ጊዜ የማቅረብ አቅም፣ ተፈጥሯዊ ሃብት እንዲሁም አገራቱ ካላቸው መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ አንጻር በዝርዝር ይገመግማል።

እንደ ግሎባል ፋየር ፓወር አሃዝ ከሆነ ግብጽ ወታደራዊ አቅሟ በብዙ ርቀት ከኢትዮጵያ ከፍ ያለ ነው።

በግሎባል ፋየር ፓወር አሃዝ ኢትዮጵያን ከ145 አገራት 49ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ግብጽን ደግሞ 15ኛ ላይ ትገኛለች።

ኢትዮጵያ በወታደራዊ አቅም በአህጉሪቱ ካሉ 54 አገራት የአምስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ ቀዳሚዋ ደግሞ ግብጽ ናት።

የግብጽ ጦር በሠራዊት ብዛት በአየር፣ በምድር እና በባሕር ኃይል ከኢትዮጵያ ጦር ያለው ልዩነት ሰፊ ነው።



የጦር ሠራዊት ብዛት

ምንም እንኳ ግብጽ እና ኢትዮጵያ ተቀራራቢ የሆነ የሕዝብ ቁጥር ቢኖራቸውም፤ በሠራዊት ብዛት ላይ ግን ልዩነታቸው ሰፋ ያለ ነው።

ኢትዮጵያ 162 ሺህ የሚሆን አጠቃላይ የሠራዊት ብዛት ያላት ሲሆን ግብጽ በአንጻሩ 440ሺህ ሠራዊት አላት። ከዚህ በተጨማሪ ግብጽ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ተጠባባቂ ኃይል እና 300ሺህ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ሲኖራት፤ ግሎባል ፋየር ፓወር ኢትዮጵያ ተጠባባቂ እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እንደሌላት ያመለክታል።

አየር ኃይል፣ የምድር ኃይል እና የባሕር ኃይል

ግብጽ አጠቃላይ 1080 ወታደራዊ አውሮፕላኖች ሲኖሯት ኢትዮጵያ ያሏት 91 ናቸው።

ከ1080 የግብጽ ወታደራዊ አውሮፕላኖች 238 ተዋጊ ጄቶች ናቸው። ኢትዮጵያ ያላት ተዋጊ ጄቶች ደግሞ 23 ናቸው። የሄሊኮፕተር ቁጥርን ስንመለከት ግብጽ 338 ሲኖሯት የኢትዮጵያ አየር ኃይል ያለው የሄሊኮፕተር ብዛት 31 ነው።

በዕቃ ጫኝ የጦር አውሮፕላኖች፣ ለሥልጠና በሚውሉ እንዲሁም ልዩ ተልዕኮ በሚወጡ አውሮፕላኖች ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ የበላይነት አላት።

የምድር ኃይልን ስንመለከት ግብጽ ከ5300 በላይ ታንኮች ሲኖሯት የኢትዮጵያ የታንክ ብዛት 680 ነው።

ኢትዮጵያ ከ10ሺህ የማያንሱ ብረት ለበስ ተሸከርካሪዎች ሲኖሯት፤ ግብጽ ደግሞ ከ77ሺህ በላይ ብረት ለበስ ተሸከርካሪዎች አሏት።

በዚህ እኤአ 2024 በተሻሻለው የግሎባል ፋየር ፓወር ሪፖርት ላይ ባይጠቀስም ኢትዮጵያ ጥቂት የማይባል ቱርክ፣ ቻይና እና ኢራን ሰራሽ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮን) እንዳላት ይታመናል።

ግብጽ በበኩሏ ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ የተመረቱ ወታደራዊ ዘመቻዎችን መፈጸም የሚችሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ታጥቃለች።

በመካከለኛው ምሥራቅ እና በአፍሪካ ግዙፍ የባሕር ኃይል የገነባችው ግብጽ አብዛኛዎቹ የአሜሪካ፣ የፈረንሳይ፣ የጀርመን እና የጣሊያን ስሪት የሆኑ የተለያዩ መጠን እና አገልግሎት ያላቸው 140 መርከቦች አሏት።

የባሕር በር አልባዋ የሆነችው ኢትዮጵያ ባሕር ኃይሏን መልሳ እየገነባች እነደሆነ ቢነገርም፣ በአሁኑ ወቅት ወታደራዊ ዘመቻን የሚወጡ ምንም አይነት የባሕር ኃይል መርከቦች የሏትም።

የሠራተኛ ኃይል፣ ፋይንስ እና ሎጂስቲክ

ለረዥም ጊዜ ቀጥሎ በሚካሄድ ጦርነት ውጤት ላይ የአንድ አገር ንቁ ተሳታፊ የሆነ ሠራተኛ ኃይል፣ ፋይናንስ እና የሎጂስቲክ አቅርቦት ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።

ግሎባል ፋየር ፓወር በአገር ውስጥ ሊመረቱ የሚችሉ እና በጦር ሜዳ ውሎ ግብዓት የሚሆኑ እንደ ተተኳሽ፣ የደንብ ልብስ፣ መለዋወጫዎች፣ መድኃኒት፣ ምግብ. . . እና የመሳሰሉትን የሚያመርተው ሠራተኛ ኃይል ወሳኝ ነው ይላል።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ከግብጽ በ10 ሚሊዮን ሕዝብ በመብለጥ የተሻለ የሰው ኃይል አላት። በዚህ ሪፖርት ላይም ኢትዮጵያ በወታደራዊ አቅም ከግብጽ ተሽላ የተገኘችው ለግዳጅ ዝግጁ ሊሆን በሚችል የሰው ኃይል ብዛት ነው።

ግብጽ ለጦሯ የምታወጣው ወጪ በብዙ እጥፍ ከኢትዮጵያ ይበልጣል። የግብጽ ጦር ዓመታዊ በጀቱ 9.4 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ የኢትዮጵያ በ10 እጥፍ አንሶ 888 ሚሊዮን ዶላር ነው።

አሜሪካ በመካከለኛው ምሥራቅ ላላት ፍላጎቷ ትልቅ ሚና ያላት ካይሮ ከእኤአ 1980ዎቹ ወዲህ ለምጣኔ ሃብት እና ጦር መሳሪያ በሚል 50 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ድጋፍ አድርጋለች።

ይህም ሆኖ ግን ኢትዮጵያ እና ግብጽ በቀጥታ ወደ ወታደራዊ ግጭት የሚገቡበት ዕድል ጠባብ ነው። በእጅ አዙር የሚደረጉ ግጭቶች ደግሞ አገራቱ ያላቸውን ወታደራዊ አቅም በሙሉ ለመጠቀም የሚያስችላላቸው አይደለም።

ከዚህ ባሻገር ግን የጎረቤት አገራትን የአየር ክልልን በማለፍ የሚፈጸሙ ድንበር ዘለል የአየር ጥቃቶች ቢኖሩ እንኳን በግሎባል ፋየር ፓወር ሪፖርት ላይ ባይጠቀስም ሁለቱም አገራት ዘመናዊ እና ጠንካራ የአየር መከላከያ ሥርዓት እንዳላቸው ይነገራል።

https://www.bbc.com/amharic/articles/cn7lp6e4l03o

Digital Weyane
Member+
Posts: 9447
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: በ BBC ውስጥ ተሰግስገው የሚገኙ እሳት የላሱ የህወሓት ካድሬዎቻችን ለግብፅ ያላቸውን ፍቅርና ድጋፍ በተራቀቀ መንገድ አሳዩ

Post by Digital Weyane » 08 Sep 2024, 10:41

የቁርጥ ቀን ወዳጃችን ግብፅ በምስራቅ አፍሪካ አካባቢ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋትና የህዝቡን ሰላም ለመጠበቅ ህጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ እንድትወስድ የሚያስችላትን ወታደራዊ ቤዝ በትግራይ እንዲኖራት ግድ ይላል። :roll: :roll:

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 11780
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: በ BBC ውስጥ ተሰግስገው የሚገኙ እሳት የላሱ የህወሓት ካድሬዎቻችን ለግብፅ ያላቸውን ፍቅርና ድጋፍ በተራቀቀ መንገድ አሳዩ

Post by DefendTheTruth » 08 Sep 2024, 10:53

ይህ የምጠበቅ ነዉ፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ ዉስጥ በቀዳሚነት ባንዳዎች አጥታ አታዉቅም፣ ሆኖም ደግሞ፣ የመጡባትን ጠላቶች ድባቅ መትታ መልሳቸዋለች፣ ሾልኮ የለፈዉ ሻቢያ ብቻ ነዉ፣ በተፈጠረዉ የዉስጥ ስህተት። ሻቢያም ብሆን፣ አሁን ተቀዳጀሁ ብሎ የምፅናነበት ድል፣ ምነዉ በቀረብኝ አያለ የፀፀት ሕይዎቱን አየገፋ ነዉ፣ በስጋት ኑሮ ተጠምዶ ይገኛል፣ መጨረሸው መቼ እንደሆነ አሁንም አይታወቅም፣ "ድሉን" መልሶ በራሱ ሳይሰጥ አይቀርም!

Digital Weyane
Member+
Posts: 9447
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: በ BBC ውስጥ ተሰግስገው የሚገኙ እሳት የላሱ የህወሓት ካድሬዎቻችን ለግብፅ ያላቸውን ፍቅርና ድጋፍ በተራቀቀ መንገድ አሳዩ

Post by Digital Weyane » 08 Sep 2024, 11:00

ባለውለታችንና የቁርጥ ቀን ወዳጃችን ግብፅ በመዲናችን መቀሌ ውስጥ የገነባችልን የሞቶ ሚልዮን ዶላር ኢንዳስትሪያል ፓርክ። ኢትዮጵያ ምን ገነባችልን? :roll: :roll:


Abdisa
Member+
Posts: 6063
Joined: 25 Apr 2010, 19:14

Re: በ BBC ውስጥ ተሰግስገው የሚገኙ እሳት የላሱ የህወሓት ካድሬዎቻችን ለግብፅ ያላቸውን ፍቅርና ድጋፍ በተራቀቀ መንገድ አሳዩ

Post by Abdisa » 08 Sep 2024, 12:17

Why do TPLF cadres like Axumezana, Abere, DefendtheTruth..etc ... pretend to be anti Egypt when Egypt is bankrolling their online propaganda activities? :mrgreen: :mrgreen: :mrgreen:

Post Reply