Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 5740
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ኢትዮጵያ ዉስጥ ስንት የሰዉ ጎሳዎች ኣሉ?

Post by Naga Tuma » 08 Mar 2024, 16:59

ቀላል ጥያቄ ነዉ። ኣይዴለም?

ቀላል ጥያቄ ከሆነ ቀላል መልስ የለዉም?

ኢትዮጵያ ዉስጥ ኣድጌ ባህሉን ኣዉቃለሁ ማለት የምችል ይመስለኛል። ከዳመራ/ደመራ እስከ አብዳሪ/ኣድባር። ከጥምቀት እስከ ታቦት ገብቶ የፈረስ ጉክስ/ጉክሲ ፈንጠዝያ።

አድዋን መርቶ ለድል ለማብቃት ባህል ትልቅ ሚና የነበረዉ ይመስለኛል። ተሳሳትኩ?

ዘመናዊ የሚባል ትምህርት ኢትዮጵያ ዉስጥ የተጀመረዉ ከአድዋ በኋላ ነዉ። ኣይዴለም?

አድዋ መቶ ዓመታት እንኳን ሳይሞላዉ ሃገር ቀይ ሽብር ዉስጥ ኣለፈች።

ከርቀት የምሰማዉ እና የማነበዉ ቀይ ሽብር ዉስጥ ያለፈች ሃገር የባህል ሽብር እና የቃላት ሽብር ዉስጥ የገባች ይመስላል።

ባህል ሰዉ ተሰዋ፣ የሰዉ ህይወት ኣለፈ፣ ሰዉ ተቀጣ ማለትን ያዉቃል።

የባህል ሽብር ዉስጥ ሰዉ እንደ እንስሳ ተቀጣ ተብሎ ድምጽ ተቀድቶ፣ ቪድዮ ተቀርጾ ለኣለም ይሰራጫል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ያልተፈጠሩ የቴክኖሎጂ ቁሳቁስን በመጠቀም።

በባህል ሰዉ በጉድፈቻ ስያድግ ያልተወለደ ነዉ ተብሎ የማይነገረዉ ኣለ። ሳይነገረዉ ኣድጎ እስከ አሜሪክ ድረስ መጥቶ ቤተሰብ መስርቶ ስለሚኖር ሰዉ የሰማሁኝ ኣለ።

የኢትዮጵያ የዳበረ ባህል የምለዉ በርካታ እሴቶቹን ሳላስተዉል ኣይዴለም።

ኣንድ ጥልቅ ባህሉ በኣብዛኛዉ ሰዉ ከራሱ ጎሳ ወጥቶ ከሌላ ጎሳ መጋባት ነዉ። ይህ በባህል እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ከአረት ወይም ከዛ በላይ የሰዉ ጎሳዎች የተወለደ ነዉ ማለት ነዉ።

ስለዚህ እስቲ ሁላችሁም እራሳችሁን ጠይቁ። ከአረት የሰዉ ጎሳዎች ያልተወለዳችሁ ኣላችሁ?

ዋናዉ ጥያቄ ከማንም ተወለድ፣ ይህን የሃገርህን ባህል እንዴት ትስታለህ ነዉ።

ይህ ባህል ኣይዴለም የህዝቡን ሀርሞኒ ጠብቆ ያኖረዉ? ኼረ፣ ኼር፣ ብኼር፣ እግዝኣብኼር ኣስብሎ?

ባህል ብርመዱ ማለትን ያዉቃል። ያስተምራል። ባህል ስብእና ማለትን ያዉቃል። ያስተምራል።

ኢትዮጵያዊ ይህን ባያዉቅ ነዉ ወይስ ባያስተዉል ነዉ ሌላ ኢትዮጵያዊ ላይ በእግሩ የሚቆመዉ?

ብርመዱን ወይም ስብእና ያለዉን በማንነቱ ሳይሆን በድርጊቱ ማወደስም ሆነ መቅጣት ኣዲስ ኣይዴለም። ባህል ዉስጥ ያለ ነዉ። እስከ አድዋ ድረስ ያዘመተዉ ባህል ዉስጥ የነበረ ነዉ።

ጀግንነት ብርመዱ ላይ መቆም ሳይሆን ለብርመዱ መቆም ነዉ። ብርመዱ ላይ መቆም የፈሪነት መገለጫ ነዉ።

ስለዚህ የባህል ሽብር ማንን ለመጥቀም ነዉ? እንዴት ተመልሶ እንዲስተካከል ነዉ?

ባህል ቃላትን መርጦ መናገርን ስያስተምር የቃላት ሽብር ማንን ይጠቅማል? እንዴት ተመልሶ እንዲስተካከል ነዉ?

ቃላትን መርጦ መናገር መጀመር ያለምክንያት ኣይዴለም። ኣንድም የስልጣኔ መጀመርያ ነዉ። ብኔንስ ነመ ጫሉ ህን ጅሩ ተብሎ፣ ተስተዉሎ። ከሰዉ የበለጠ አዉሬ ዬለም ማለት ነዉ። ብኔንሰ በእንግሊዘኛ ቢስት የሚባለዉ ነዉ። ቃሉም ሆነ ማስተዋሉ ያን ያህል ጥንታዊ ነዉ። ሰዉ ስብእናዉን ከማጣት ሌላዉን መቅጣትን የሚመርጥ ነዉ።

ሃገሩ ሰፊ። ሀሳብ እና አስተሳሰብ ኣእላፍ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ኣዲስ ነገር መፍጠር ገና የሚስፋፋ።

እነዚህን ኣስተዉለን ነዉ በሰፊዉ በማናዉቀዉ ጥልቅ እና ጥንታዊ የኢትዮጵያዊየን የሰዉ ጎሳዎች ማንነት ትግል ዉስጥ የምንዋዥቀዉ? ከን ቃጆፍኑ? ሺዞፎርንክ የምንሆነዉ?

Naga Tuma
Member+
Posts: 5740
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ኢትዮጵያ ዉስጥ ስንት የሰዉ ጎሳዎች ኣሉ?

Post by Naga Tuma » 25 Mar 2024, 19:29

ስለዚህ ርዕስ ዝም ብዬ ሳሰላስል ከጥንት ግዜ ጀምሮ ባህል የኢትዮጵያ የሰዉ ጎሳዎችን ኣንድ ለአረት ወይም ከዛ በላይ ያስተሳሰረዉን ነዉ በዚህ ዘመን በኣንድ ጎሳ ስም በሚመስል ክልል ማለት የተጀመረዉ እላለሁ።

ለመሆኑ የሰዉ ጎሳዎች ክልል መስራች መሪዎች መለስ ዜናዊ እና ነጋሶ ግዳዳ እያንዳንዱ አረት ወይም ከዛ በላይ ጎሳዎች እነ ማን ናቸዉ?

Naga Tuma
Member+
Posts: 5740
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ኢትዮጵያ ዉስጥ ስንት የሰዉ ጎሳዎች ኣሉ?

Post by Naga Tuma » 14 Aug 2024, 15:39

ሰደቸ መጫ የኦሮሞ ቃል መሠረት እልመ ኦርማ ነዉ ይላል፥

We've been calling ourselves ilma Orma loooong before the German j krapf came to Ethiopia dude. You are showing how ignorant you are when you post such nonsensical things dude. It's okay to NOT know. But it's not okay to pretend that you know something.

እልመ ወንድ ልጅ ማለት ነዉ።
ኦርመ ባዕድ ማለት ነዉ።

ስለዚህ የትኛዉ የኢትዮጵያ ጎሳ ነዉ ኦርመ ወይም ባዕድ ያለዉ?

የትኛዉ የኢትዮጵያ ጎሳ ወይም ጎሳዎች ናቸዉ ባዕድ የተባሉት?

Post Reply