የወንድና ሴት ወጣቶች መተዋወቂያ ፣መፋቀሪያ ባህል ። ከመስቀል ቀን እስከ ጥቅምት አቦ ድረስ በየገበያውና ቤተክርስቲያ አካባቢ የሚድረግ ሰፊ የወጣቶች ዘፈን፣ ጭፈራ ሎሚ ፕሮግራም ። ቃሉ የአደይ አብና (የአደይ አበባ ስጦታ ) ማለት ሲሆን ጥንት ሎሚ ሳይሆን አበባ ለልጅቷ የሚሰጥበት ቀን ነበር ።
(2) የሚጆ ማይ
ወንዱ ልጅ ያፈቀራትን ለአባቱና እናቱ ነግሮ ከልጃቸው ፍላጎት ጋር ከተስማሙ ሶስት ገለልተኛ ሽማግልሎች ለጋብቻ ጥያቄ የሚልኩበት ስርዓት ነው ። የሴት ወላጆች ልጃችደውን ለመስጠት ከፈቀዱ የቸግ እለተ ቀጠሮ በሚጆ ቀን ይወሰናል
(3) የቸግ ማይ
ቸግ ፍጥምጥም ማለት ሲሆን በሴት ቤት የሚደረግ በጣም ትልቅ የድግስ ስርዓት ነው ። የስጦታ የጥሎሽ መስጫ ቀን ነው ።
(4) የጠፍር ማይ
ከሰርጉ ወርና 15 ቀን ሲቀረው ጀምሮ የሙሽሮቹ ዘመዶች ወንድም እህት፣ አጎት አክት ተራ በተራ ድግስ ደግሰው የምሽሮቹ ሚዜዎችና ጓደኞች ማታ የሚጨፈርበት ስርዓት ነው
(5) የእንሾሽላ ማይ
ሰርጉ እሁድ ሆኖ (ሰርግ ሁልግዜ እሁድ ነው የሚሆነው) አርብ ቀንና ሌሊት በወንዱም በሴቷም ቤት መላ ዘመድ አዝማዳቸው ተሰብስቦ ወጣቶቹን ለትዳር (ቢተን) መድረሳቸው እና መሰናበታቸው ተሚደረግበት በጣም ስሜት የሚነካ ስርዓት ። ዛሬ ላይ እንሾሽላ ከሰርግ እኩል እየደመቀ መጥቷል
(6) የእረ ማይ
እረ በእንሾሽላ ማግስት በሴቷ ቤት የሚደረግ የእናቶች የቅንጬ ገንፎና የሙሽራ እናተ ቅቤ ባናቷ ተደርጎላት የምትመሰገንበት የሴቶች ስርዓት ነው ። አሁን የቀረ ቢሆንም እረ ሙሽራዋ ኮስ የምትጠጣበት ቀን ነበር ።
(7) የሸባል ማይ
ሸባል ማለት ሰርግ ማለት ነው ። ጋብቻ ሙሉ ሂደቱ ሲሆን ሸባል የእሁድ ሰርግ ድግስና ወንዱ ሙሽራዋ ቤት ሄዶ የነገ ሚስቱን የሚያመጣበት ግዙፉ ድግስና ባህል ነው ።
(8) የምስራች
ሰኞ ሶስት የሙሽራው ሚዜዎች (የሙሽራርዋ ወንድሞች ሆነው ነው የሚታዩት) የልጅቷን ድንግልነት ለወላጆችዋ ለማብሰር የልጅቷ ወላጆች ቤት የሚሄዱበትና ለሴት ወላጆች እጅግ ትልቅ የክብር ቀን ነው ። በድሮ ግዜ ሙሽራዋ ድንግል ሆና ካልተገኘች በማግስቱ ሰኞ ሚዜዎቹ ሙሽራዋን ወደ ወላጆቿ የመልሷት ነበር ይባላል።
(9) አውታ
የሙሽራዋ ወገኖች ጓደኞች የልጅቷን ልብሶች፣ እቃዎች፣ ስጦታዎች፣ እንቁዎች ሁሉ ፣ ለትዳሯ የተሰጣት ነገር ሁሉ ወደ አዲሱ ቤቷ ወደ ወንዱ ቤት የሚያመጡበት በዓል ነው
(10) አንገት ኧግዳን
አንገት ኧግዳን መልስ ማለት ነው ። ዛሬ ተለውጦ ነው እንጂ መልስ ማለት ልጅቷ ወደ ቤተሰቧ ከባልና ሚዚዎቿ ጋር እመልሳ ከሶስት ቀን እስከ ሳምንት እየበሉ የሚጨፈርበት ድግስ ነው ።
ማይ ቀን ማለት ነው፤ በእብራይስጡ ዮም የሚለው