Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30844
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

THE ORTHODOX MOVEMENT & THE INCREDIBLE SPIRITUAL TRANSFORMATION OF ETHIOPIA!

Post by Horus » 09 Feb 2023, 00:30

A well known principle of systems thinking holds that 'Actors Produce Unintended Consequences' ! መንግስትና ግብረ አበሮቹ ያልጠበቁት ነገር እየወጠራቸው ነው ። እጅግ እጅግ ግዙፍ ነገር!

ኢህአዴግና ብልጽግና ወጣቱን የጫትና የሹሻ ሱሰኛ አድርገው ገድለውት ነበር ። አዲስ አበባ የሽርሙጥናና አደንዛዥ ዕጾች መሸቀጫ አድርገውት መላ ሕበረተሰቡ ሞራሉ የላሸቀ፣ መንፈሱ የወደቀ፣ አላማና ራዕይ አልባ ሕዝብ አድርገውት ነበር።

ያም በማድረጋቸው ወጣቱን እንደ መንጋ እየነዱ ያሻቸውን ቆሻሻ ስብከት ሲጭኑበት፣ ሲጫወቱበት ሃይ የሚላቸው ስለጠፋ ይባስ ብለው መንግስትና ኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን ሃይማኖትና ቤተ መቅደስ ለመንጠቅ፣ ለመቆጣጠር ተነሱ ። አዲስ ኦርቶዶክስ አዲስ ሲኖዶስም፣ ያባ ገዳ ቡልኮ የለበሱ ጳጳሳትን ፈጠሩ! ዋቄ ፌታ ኦርቶዶክስ ክርስትናን ሊተካ ማለት ነው።

ይህ የጎሳ ዲክታተሮች ድፍረት ግን ሌላ እጅግ ሌላ ማንም ያላሰበው በረከት ይዞ መጣ !! ያም የኢትዮጵያ ወጣት መንፈሳዊ ፍንዳታ! መንፈሳዊ ትንሳኤና መንፈሳዊ ትራንስፎርሜሽን ነው።

በእኔ እምነት ይህ አሁን እየተቀጣጠለ ያለው የወጣቱ መንፈሳዊ አብዮት ኢትዮጵያን ላንዴም ለሁሌም የሚለውጣት ይሆናል ። የኢትዮጵያ ወጣት ተለውጧል! አንድ የሚያደርገው እንደ ፋና የሚመራው ራዕይ ፣ አንድ የሚከተለው ትርጉም አግኝቷል ።

በጥጋብና እብሪት የተወጠሩት የጎሳ ተረኛ ዲክታተሮች የለኮሱት እሳት ኦርቶዶክስን እንደ ብረት ማጠንከሩ ብቻ ሳይሆን የዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊ ወጣት ይህችን አገር ለመረከብ በእሳት ያጠመቀ ትንኮሳ ሆነ !

የኦርቶዶክስ አሸናፊነት የማይጠረጠር ነበር ! ይህ የኢትዮጵያ ወጣት መንፈሳዊ ትንሳኤ ግን ማንም ያላለመው ተአምር ነው!



Horus
Senior Member+
Posts: 30844
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE ORTHODOX MOVEMENT & THE INCREDIBLE SPIRITUAL TRANSFORMATION OF ETHIOPIA!

Post by Horus » 09 Feb 2023, 01:23

እነዚህ ክቡር ጋሞዎች እንዴት እንዴት ያምራሉ !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30844
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE ORTHODOX MOVEMENT & THE INCREDIBLE SPIRITUAL TRANSFORMATION OF ETHIOPIA!

Post by Horus » 09 Feb 2023, 01:43

Hammer!


Horus
Senior Member+
Posts: 30844
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE ORTHODOX MOVEMENT & THE INCREDIBLE SPIRITUAL TRANSFORMATION OF ETHIOPIA!

Post by Horus » 09 Feb 2023, 02:05

ትክክል ነው!የኦርቶዶክስ ንቅናቄ የመላ ኢትዮአጵያዊያን ንቅናቄ ሆኖዋል!


Horus
Senior Member+
Posts: 30844
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE ORTHODOX MOVEMENT & THE INCREDIBLE SPIRITUAL TRANSFORMATION OF ETHIOPIA!

Post by Horus » 09 Feb 2023, 08:35

የ2015 የኢትዮጵያ ወጣት ልክ እንደ 1960ዎቹ ትውልድ በእሳት ተፈትኖ ማንነቱን ገናና ኢትዮጵያዊነቱን ሞት አይፈሬነቱን በሙሉ ሲቃ ሊያረጋግጥ ተነስቷል! ይህ ስር ነቀል አብዮት ካልሆነ ምን እንደ ሚሆን ወደ ፊት ታሪክ ይጽፈዋል!



ካራ ቆሬ



Horus
Senior Member+
Posts: 30844
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE ORTHODOX MOVEMENT & THE INCREDIBLE SPIRITUAL TRANSFORMATION OF ETHIOPIA!

Post by Horus » 10 Feb 2023, 00:42

የተበላ ዕቁብ ሕግ እና የዲክታተሩ ስሌት ግዙፍ ስህተት
ዲክታተር አቢይ አህመድ አሊ በምን ምክንያት ይህን የሰማይ ስባሪ የሚያክል ስህተት ሊፈጽም የቻለው?
እኔ ሆረስ ቃላት በመፍለጥ ግዜያችሁን አላባክንም! በቀጥያ የዲክታተሩን ችግር በስሙ እጠራዋለሁ፣ በዳቦ ስሞቹ ሳይሆን።
ነጥብ 1፣
ዲክታተሩ የተበላ ዕቁብ ሕግን መግደፉ ነው ። የተበላ ዕቁብ ሕግ ማለት አንድ ዲክታተር ወይም ተንኮለኛ ከዚህ ቀደም የተጠቀመበትን ዘዴ መላልሶ ለመጠቀም መሞከር ጂልነት ነው፤ ስልቱ ወይም ብልጠቱ ሁሉም ስላወቀው ማለት ነው። አቢይ ሊያደርግ የሞከረው መለስ ዜናዌ ያደረገውን ብቻ ሳይሆን እራሱ አቢይ በሙስሊም መጅሊስ ላይ ያደረገውን ደባ ነው በኦርቶዶክስ ላይ ሊደግም ሲምክር እጅ ከፍንጅ የተያዘው!
ነጥብ 2፣
አቢይ አህመድ ናርሲሲስት ራስ አምላኪ ዲክታተር ስለሆነ ነው ። የዲክታተሩ እጅግ መሰረታዊ እና መውደቂያ በሽታው እራሱን ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን አዋቂ፣ ስለሁሉን ሰውና ሕዝብ አውቅላችኋለሁ ባይ የራሱን ምናብና ቅዠት እንደ ነባራዊ ሪያሊቲ የሚያምን ግብዝ ራስ አምላኪ ስለሆነ ነው። ይህ ደሞ የሳይኮሎጂ በሽታ ነው ።
ነጥብ 3፣
በነጥብ 2 መሰረት ራሱን ያገነነው ራስ አምላኪ የኦርቶዶክስን ጥልቀት፣ ግዝፈት፣ ኃይል፣ የሰው የውቀት፣ ክህሎትና የቁስ ሃብት፣ የኦርቶዶክስን ዝናና ክብር ልክ ፈጽሞ ያልተገነዘበ የሚመኘውን የሚያምን በራሱ ምናብ ውስጥ የሚመላለስ ግብዝ ራስ አምላኪ ስለሆነ ነው። ኦርቶዶክስ እጅግ እጅግ ግዙፍና እንደ አለት የጸና ሓያል እምነትና ተቋም ነው ።
ዲክታተር አቢይ አህመድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ላይ ያሳየው የእብሪት፣ የንቀት፣ የድፍረትና እዩኝ እዩኝ ባይነት የዚህ የራሱ ልብ ወለድ ራስ አምላኪነት በሽታ ውጤት ነው ። በሳይኮሎጂ አነጋገር ከሪያሊቲ ጋር የተፋታ ሳኮቲክ ማለት ነው ።
ነጥብ 4፣
ዲክታተር አቢይ አህመድ አሊ በእውነተኛ ውስጠ ልቡ የኦሮሞ ብሄረተኛ እንጂ ኢትዮጵያዊ አይደለም፤ የስልጣን እና ዝና ነጋዴ እንጂ ክርስቲያንም አይደለም ። ይህ ሌላው ትልቁ የአቢይ አህመድ መውደቂያ ነው ። በዚህም ምክንያት የዲክታተሩ ቃላት ኢትዮጵያ የሚል ድምጽ ሲያስተጋቡ፣ የዲክታተሩ ተግባር ግን ኦሮሙማ የሚል ሃቅ ያበራሉ ። ይህ መጣረስ ደሞ የዲክታተሩ ውድቀት ሰበብ ነው ።
ሌሎችም ብዙ ምክኛቶች ስላሉ ጨንሩበት!
ሆረስ ዐይነ ብርህን ዘዚትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ላዕለ ኩሉ ኢትዮጵያ ዘላለማዊ!!!

Post Reply