Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7993
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

"አብይ አህመድ እና ኦህዴድ ኢትዮጵያን እየገዛበት ያለው በወረራ/በምርኮ እንደያዛት ሀገር ነው" ተባለ!!

Post by Wedi » 08 Feb 2023, 12:29

"አብይ አህመድ እና ኦህዴድ ኢትዮጵያን እየገዛበት ያለው በወረራ/በምርኮ እንደያዛት ሀገር ነው" ተባለ!!

ካሳ አንበሳው
·
ኦህዴድ ኢትዮጵያን እየገዛበት ያለው በወረራ/በምርኮ እንደያዛት ሀገር ነው፣

በወረራ/ምርኮ የያዝከውን ሀገር ስታስተዳድር ህዝቡ የኔ አይደለም፣ እኔም የዚህ ህዝብ መሪ የመሆን ታሪካዊ፣ ህጋዊና ሞራላዊ መብት የለኝም ብለህ ነው የምታምነው፣

አንድን ሀገር በወረራ/ምርኮ ስትቆጣጠር የሚዘረፍውን ትዘርፋለህ፣ የሚገደለውን ትገድላለህ፣ መሰበር ያለበትን ትሰብራለህ፣

አንተ "ባለሙሉ መብት" የምትለው መሪ/ህዝብ መቼ እንደሚነሳ ስለማታውቅ ሩጫህ ከጊዜ ጋር ይሆናል፣ የምትፈልገው በጥድፊያ ትከውናለህ

እኛ ነበርን እኮ እንደ መሪ የቆጠርናቸው፣ እነሱማ ኢትዮጵያ የምትባል ትልቅ ሀገር ባላሰቡት መንገድና ጊዜ እጃቸው ላይ ወድቃ ተደናግጠዋል፣ ኢትዮጵያን የመምራት መብትና አቅምና አለን ብለው አያምኑን፣ ችግራችን የሚቀዳው እንዲህ ካለ የበታችነት ስሜት ነው፣