Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 33200
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

(((JOKE OF Z CENTURY))):Terrorist Sibhat Nega Sues Z Ethiopian Police(((HAHAHA)))!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 02 Dec 2022, 08:48

Natnael Mekonnen

**አቶ ስብሐት ነጋ የፌደራል ፖሊስን በፍርድ ቤት ከሰሱ።**

አቶ ስብሐት ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር ልሄድ ስል በፌደራል ፖሊስ ከኤርፖርት ታግጃለው ሲሉ ለፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል።

ክሱን ያቀረቡት በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የመሰረታዊ መብቶች ጉዳዮች ችሎት ነው።

አቶ ስብሐት ነጋ በከፍተኛ ህመም ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ህክምና አድርገው ለመመለስ ወደውጭ ሀገር ሊሄዱ ሲሉ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከኤርፖርት እንዲመለሱ መደረጋቸውን ለችሎቱ በቀረበው ክስ ላይ ተጠቅሷል።

በዚህ በቀረበ ክስ ኢትዮጲያ በአለም አቀፍ ደረጃ የፈረመቻቸውን ህጎችን እና በህገመንግስቱ የተቀመጡ የዜጎችን የመቀሳቀስ መብት በሚጣረዝ መልኩ ፍርድ ቤት ባላዘዘበት ሁኔታ ፖሊስ ከስልጣኑ ውጪ የጉዞ እግድ መጣሉና አቶ ስብሐትን ከኤርፖርት እንዲመለሱ ማድረጉ የህግ አግባብ የሌለው ነው ሲል ጠበቃቸው ታደለ ገ/መድህን ለችሎቱ አቅርቧል።

የአቶ ስብሐት ነጋ ክስ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ዙሪያ ፖሊስ መልስ ባለማቅረቡ ምክንያት መልስ የመስጠት መብቱ እንዲታለፍ ብይን ሰቷል።

በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለፊታችን ሮቡ ህዳር 28 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

በትግራይ ክልል ከነበረው ጦርነት ጋር ተያይዞ በፌደራል መንግሥቱ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ የነበሩት የህወሓት አመራሮች ማለትም የድርጅቱ መስራች የነበሩት አቶ ስብሐት ነጋ እና እህታቸው ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ፣ አቶ ዓባይ ወልዱ፣ አቶ አባዲ ዘሙ፣ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር እና አቶ ኪሮስ ሐጎስ በምህረት እንዲፈቱ መወሰኑን ተከትሎ ከስር መፈታታቸው ይታወሳል።
:lol: :mrgreen: