Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የድርድር ድራማ!

Post by Horus » 06 Oct 2022, 23:30

እኔ ሆረስ ተከስተ ብርህን ቃላት መፍለጥ አልወድም ።
አንድ፣
የጦርነት ሁሉ አላማ ፖለቲካ ነው ።
ሁለት፣
ዉጊያ ማሸነፈ ጦርነት ማሸነፍ አይደለም።
ሶስት፣
ጦርነቱን ማሸነፍ ፖለቲካውን ማሸነፍ አይደለም።
አራት፣
ነገር ግን የፖለቲካ ግብ የሌለው ጦርነት የጂሎች ግዜ ማሳለፊያ ነው።
አምስት፣
ለድርድር መቀመጥ ጦርነት ማሸነፍ አይደለም ። የፖለቲካ ድልም አይደለም
ስድስት፣
ድርድር መቀመጥና የድርድሩን ፖለቲካ ማሸነፍ እንደ ቀንና ሌት የተለያዩ ናቸው!
ሰባት፣
ትህነግ የሚያሸንፈው ፖለቲካ የለውም ። የወያኔ ትግሬ ፖለቲካ ከሞተ ዘመናት አልፈዋል።
ስምንት ፣
ስለሆነም የትግሬዎች ጦርነት ፖለቲካ አልባ አላማቢስ የጂሎች መላላጥ ነው።

ትህነግ የሚያሸንፈው ፖለቲካ የለውም!!!

Happy አዳብና!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የድርድር ድራማ!

Post by Horus » 06 Oct 2022, 23:56

ለምሳሌ የፖለቲካ ሳይንስ የሚያውቀው ዴቪድ ሺን ለትግሬዎች ጦርነት የፖለቲካ አላማ ሊሰጣቸው እየጣረ ነው! ያም አላማ ትግሬ ሬፈረንደም አድርጎ ከኢትዮጵያ መገንጠል ነው። በኔ እምነት ብዙ አበሾች ሃሳቡን በልልታ የሚቀበሉት ይመስለኛል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳለችው የትግሬዎች አላማ ያ ከሆነ አንቀጽ 39 እንጂ ጦርነት አላስፈላጊ ነበር ። ዴቪድ ሺን አዳነችን አላዳመጣትም ማለት ነው!!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የድርድር ድራማ!

Post by Horus » 07 Oct 2022, 02:00

ይህን ጉድ ስሙ!
ማነው ትግሬን ወክሎ የሚደራደረው የሚለው የትግሬ ውሳጣዊ ትግል የመጀምሪያው ፖለቲካ ነው ! ገና ብዙ እንሰማለን!!


የአፍሪካ መግለጫ በአንድ ነገር አልተመቸኝም ። አንድም ቦታ የኢትዮጵያን መንግስት በስም አይጠቅስም ይህም ይሆነ ትህነግ ፣ የትግሬ ጦር፣ ወይም የትግሬ መንግስት ላለማለት ነው ። ይህ በፍጹም ትክክል አይደለም ። "the twp parties' ነው የሚላቸው ። እሺ አሁን የኢትዮፌዴራል መንግስት ከማን ጋር ነው ድርድር የሚያደርገው ።
(1) የኢትዮጵያ መንግስት ድርድር የሚያደረገው ከትግሬ መንግስት ጋር ከሆነ ዛሬ ላይ ህጋዊ የትግሬ መንግስት አለ ወይ? በሕገ ወጥ ምርጫ አይደለም ወይ ደብሬ ፕሪዚዳንት የሆነው?
(2) ከትህነግ ጋር ከሆነ ብልጽግ ና ከመጣ በኋላ ትህነግ የሚባል ህጋዊ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ የተመዘገበ ፓርቲ በኢትዮጵያ አለው ወይ?
(3) ድርድሩ ከትግሬ ጦር ጋር ከሆነ ይህ የጎሬላ ሪቤል ቡድን ስለሆነ እንዴት ከዚትዮጵያ መንግስት እኩል 'ዘ ቱ ፓርቴስ ' የሚል የተደራዳሪነት እስታተስ ይሰጣቸዋል?

እናም ይህ ከኢትዮጵያ ጋር ድርድር የሚያደርገው የትግሬ ቡድን ምን ስልጣን አለው? ስምምነት ቢደረገስ ለዚህ ስምምነት ተጠያቂ የሚያደርገው ምን ህጋዊነት አለው?

እንዴት ተብሎ ነው ኢትዮጵያ ስም የለሽ ተደራዳሪ ፓርቲ የሚለውን ስም የተቀበለውችው?

ከዚያ በተረፈ አንድ ነገር ልበል !!!

በጦርነት የተሸነፈ ቡድን በድርድር ትሪቲ አያሸንፍም ። ከጦርነት በኋላ የሚደረግ ድርድር ሁልግዜ የጦርነቱን ውጤት በወረቀት ላይ አስፍሮም ወደ ስምምነት መለወጥ ነው አላማው! ማለትም ኢትዮጵያ ትክክለኛ ተደራዳሪዎች ካሏት ማለት ነው ። አንድ ቡድን ወይም አገር በጦርነቱ ወስጥ ያላገኘውን ሚዛን በድህረ ጦርነት ድርድር ሊያገኝ አይችልም! የፖለቲካ ሎጂክ ይቃረናል!

እና ትህነግ ምንም አይነት የተለየ ድርሻ ሊያገኝ አይችልም! ወልቃይትና ራያን በጦር መያዝ አልቻለም፣ አሁን በድርድር ወልቃትና ራያ ሲሰጠው አይችልም።

እናሳ ምንድን ነው የዚህ ድርድር ፋይዳ ለትግሬ? መብራትና ዉሃ ማስገባት ነው በቃ!

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የድርድር ድራማ!

Post by Horus » 07 Oct 2022, 12:18

ኡሁሩ ኬኒያታ፣ ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም! እራሱ ወንጀለኛ ኡሁሩ ዘ ፓነል ኦፍ ዘ ዋይዝ እንዴት ይባላል?!!! እሱ እራሱ ለቀቀ!!

ቲ ፒ ኤል ኤፍ ፣ በጦር ሜዳ ጦርነቱን ማሸነፍ ያቃተው ጠረጴዛ ላይ ድርድር ሊያሸንፍ አይችልም!!! ሎጂክ አይፈቅድም!!!
Last edited by Horus on 07 Oct 2022, 12:57, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የድርድር ድራማ!

Post by Horus » 07 Oct 2022, 12:47

ስለሆነም ትግሬ የሚያሸንፈው ፖለቲካ የለውም ማለት ድርድሩን አይፈልግም ማለት ነው ። ትህነግ ድርድሩን ተቀብሎ ከሄደና ከተስማማ ከድርድሩ የጦር ሽንፈቱን ተቀብሎ ለትግሬ ሕዝብ ሰላም ማግኘት ብቻ ነው ። ያ ካልሆነ ዉጊያው በተለያየ መንገድ ይቀትላል ። ጦርነቱ አያበቃም ማለት ነው ።

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4063
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: የድርድር ድራማ!

Post by Za-Ilmaknun » 07 Oct 2022, 13:13

Horus wrote:
07 Oct 2022, 12:47
ስለሆነም ትግሬ የሚያሸንፈው ፖለቲካ የለውም ማለት ድርድሩን አይፈልግም ማለት ነው ። ትህነግ ድርድሩን ተቀብሎ ከሄደና ከተስማማ ከድርድሩ የጦር ሽንፈቱን ተቀብሎ ለትግሬ ሕዝብ ሰላም ማግኘት ብቻ ነው ። ያ ካልሆነ ዉጊያው በተለያየ መንገድ ይቀትላል ። ጦርነቱ አያበቃም ማለት ነው ።
The war will never end at least, in the short run. The war is borne of a failed political system that has been in the making for the past 50 plus years. Too many interests from too many actors are now converging to give the war far more dimensions than the linear TPLF-Bil'Tsigna conflict. :x

Abere
Senior Member
Posts: 10901
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የድርድር ድራማ!

Post by Abere » 07 Oct 2022, 13:15

ሆረስ፤

በምን ላይ ነው የሚደራደሩት? እነ ማን ናቸው የሚደራደሩ? አንተ የምትለው ይገባኛል። ለስልጣን፥ለንዋይ፥ለዝና የመሳሰሉት ክፍፍል ወይም ድርሻ። ግን አንድት ሙሽራ ወይም ምሽሪት ብቻው(ዋ)ን ሰርግ ቦታ ቢሄድ ሌላው ጥንድ ከሌለ ጋብቻ የሚሆን አይመስለኝም። በፊት እንዳልኩት ይህ ጦርነት የትግሬ እና የአማራ ጦርነት ነው። ለምን ጦርነት ገቡ? ሌላ ጥያቄ ነው። አሁን ለድርድር ሲባል ተደራዳሪዎች አማራ እና ትግሬ እንጅ ብልጽግና-ኦነግ እና ወያኔ ሊሆኑ አይችሉም። ተደራደረ አልተደራደረ ልዩነት የለውም።ፍየል ወዲያ ቅምዝምዝ ወዲህ የሆነ ጉዳይ ነው።

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የድርድር ድራማ!

Post by Horus » 07 Oct 2022, 13:29

Abere wrote:
07 Oct 2022, 13:15
ሆረስ፤

በምን ላይ ነው የሚደራደሩት? እነ ማን ናቸው የሚደራደሩ? አንተ የምትለው ይገባኛል። ለስልጣን፥ለንዋይ፥ለዝና የመሳሰሉት ክፍፍል ወይም ድርሻ። ግን አንድት ሙሽራ ወይም ምሽሪት ብቻው(ዋ)ን ሰርግ ቦታ ቢሄድ ሌላው ጥንድ ከሌለ ጋብቻ የሚሆን አይመስለኝም። በፊት እንዳልኩት ይህ ጦርነት የትግሬ እና የአማራ ጦርነት ነው። ለምን ጦርነት ገቡ? ሌላ ጥያቄ ነው። አሁን ለድርድር ሲባል ተደራዳሪዎች አማራ እና ትግሬ እንጅ ብልጽግና-ኦነግ እና ወያኔ ሊሆኑ አይችሉም። ተደራደረ አልተደራደረ ልዩነት የለውም።ፍየል ወዲያ ቅምዝምዝ ወዲህ የሆነ ጉዳይ ነው።
እኔ ከዚህ ቀደም በረጅሙ በምትለው ነጥብ ላይ ፖስት አድርጌያለሁ። ካሁን እስከ ዘመን ፍጻሜ በድምበርተኘትና በሌሎችም ሶሺያልና መሬት ትስስሮች ሳቢያ ዘላለማዊ ወዳጅም ዘላለማዊ ጠላትም የሚሆኑት አማራ፣ ትግሬ፣ አፋርና ኤርትራ ናቸው ። ማንኛውም የሰላም ድርድር ሆነ የጦርነት መሸናነፍ እነዚህ አራት ሰዎች ከሌሉበት በትክልል ፍየል ወዲህ ቅምዝምዝ ወዲያ ነው ። የጦርነቱም ሆነ የድርድሩ ፖለቲካ ይዘት ምንድን ነው ስንል የነዚህ አራት ህዝቦች ጉዳይ ዋናው ጥያቄ ነው ።

ከዚያም የኢትዮጵያ አገራዊ ጉዳይና ያካባቢው/አለም ሃይሎች ጂኦፖለቲካ ይመጣል ። አሁን ግን ከኤርትራ በስተቀር አማራም፣ አፋርም፣ ትግሬም ይህ ነው የሚባል ለጥቅማቸው የሚደራደር ሃይል ደቡብ አፍሪካ የላቸውም ። ልብ በል ትህነግም ቢሆን ለትግሬ ህዝብ ዘላቂ ጥቅም አይደለም ድርድር የሚለው፣ ለራሱ ስልጣናን ደህነንት ነው። ስለዚህ ነው ጦርነቱ በሆነ መልኩ የሚቀጥለው!

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የድርድር ድራማ!

Post by Horus » 07 Oct 2022, 13:47

ይህን ስሙ! ትህነግ ከአማጺነት ወደ መንግስትነት ልቆ ሲያበቃ ተመልሶ ከመንግስትነት ወደ አማጽነት የወረደ የመጀምሪያ ክስተት ባለም ላይ :lol: :lol: :lol:

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የድርድር ድራማ!

Post by Horus » 07 Oct 2022, 14:46

"To go through life armed only with audacity would be tiring and also fatal." Robert Greene, The 48 Laws of Power. P. 235

union
Member+
Posts: 6046
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: የድርድር ድራማ!

Post by union » 07 Oct 2022, 15:33

ሆረስ
ትህነግ ፓለቲካው ሂወት ኖሮት አያውቅም። በማጭበርበር እና በማፈን ነው እስካሁን የኖረው። አሁን ልዩነቱ ሰው ሁሉ ሌባ እንደሆኑ አወቀ እና ተፋቸው። አሁን አዲሱ እብድ ብልፅግና የሚባለው ነው። ከትህነግ ያልተማረው የሞተ ፓለቲካ የተሸከመው ብልፅግና ነው።

የኢትዮጵያን ህዝብ ማንነት በደንብ ያልተገነዘበው ብልፅግና አዲስ አበባን ለመውረር ዝግጅት ላይ ነው። አሁን ድርድር እያለ ትህነግ በደጋፊዎቿ እንዳትተፋ ግዜ እየገዛላት ነው። በህዝብ ከተሸነፈው ከትህነግጋ ወደ ድርድር የሚሮጠው ዋናው ትህነግ እራሱ ብልፅግና ነው! አበቃ!
Horus wrote:
06 Oct 2022, 23:30
እኔ ሆረስ ተከስተ ብርህን ቃላት መፍለጥ አልወድም ።
አንድ፣
የጦርነት ሁሉ አላማ ፖለቲካ ነው ።
ሁለት፣
ዉጊያ ማሸነፈ ጦርነት ማሸነፍ አይደለም።
ሶስት፣
ጦርነቱን ማሸነፍ ፖለቲካውን ማሸነፍ አይደለም።
አራት፣
ነገር ግን የፖለቲካ ግብ የሌለው ጦርነት የጂሎች ግዜ ማሳለፊያ ነው።
አምስት፣
ለድርድር መቀመጥ ጦርነት ማሸነፍ አይደለም ። የፖለቲካ ድልም አይደለም
ስድስት፣
ድርድር መቀመጥና የድርድሩን ፖለቲካ ማሸነፍ እንደ ቀንና ሌት የተለያዩ ናቸው!
ሰባት፣
ትህነግ የሚያሸንፈው ፖለቲካ የለውም ። የወያኔ ትግሬ ፖለቲካ ከሞተ ዘመናት አልፈዋል።
ስምንት ፣
ስለሆነም የትግሬዎች ጦርነት ፖለቲካ አልባ አላማቢስ የጂሎች መላላጥ ነው።

ትህነግ የሚያሸንፈው ፖለቲካ የለውም!!!

Happy አዳብና!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የድርድር ድራማ!

Post by Horus » 08 Oct 2022, 00:10

ድርድር ማንም የማይፈልገው አር የነካው ቃል ነው። ድርድር አቢይም ኣይፈልገውም፣ ትህነግም አይፈልገውም።

ድርድር ማለት ማንም የማያሸንፍበት እና በትክክል ከተካሄደ መሸነፍን 50/50 ክፍፍል የሚደረግበት የሁለት ተሸናፊዎች ጨዋታ ነው ። አንድ ሰው ተደራደረ ማለት ጨዋታውን ማሸነፍ ስላቃተው ትግል አቆመ ማለት ነው።
ዛሬ ላይ እነደብሬ 1 ሚሊዮን ድረስ ሰው አስድለው በድርድር ባዶ ሰላም ይዘው መቀሌ ከመግባት የላቀ ቅሌትና ውርደት የለም ።

ላቢይ አህመድም የ120 ሚሊዮን ሕዝብ ግብር እየሰበሰበ መላ አማራ፣አፋርና ኤርትራ ከጎኑ ይዞ በድርድር በወያኔ ተሸንፎ 4 ኪሎ ከመግባት የላቀ ውርደት የለም ። ስለዚህ ድርድር የጀርባ አጥንታቸው ይደቀቀ ተሸናፊዎች ፍላጎት ነው ።

ታዲያ ለምንድን ነው ደቡብ አፍሪካ የሚሄዱት? የፖለቲካ ድራማ ! የዲፕሎምሲ ድራማ ስለሆነ ያ ድራማ ደሞ ላለም ሁሉ መተወን ስላለበት ነው !!!

Post Reply