Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4206
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

ማዲንጎ ምን አርጎ ነው ይህ ሁሉ ሽርጉድ? የንግሥት ኤልሳበትን እኮ መሰለ? ለሁሉ ነገር እኮ ልክ አለው ልክ አለው

Post by Abaymado » 29 Sep 2022, 11:26

ማዲንጎ ይህ ሁሉ ክብር የተሰጠው ምን አርጎ ነው?
በሙዚቃው?
ወይስ የሃጫሉን ለመድገም?
ወይስ ለሀገር ስለዘፈነ?
ወይስ ወያኔን እንዲመታ ስለዘፈነ?

ሁሉ ነገር ልክ አለው : ለስንቱ እንዲህ ይኮናል? ደሞስ ሰው በፍላጎቱ እንጂ ዜና ተስርቶለት ሰው እንዲወጣ ተደርጎ መሆን የለበትም::

Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: ማዲንጎ ምን አርጎ ነው ይህ ሁሉ ሽርጉድ? የንግሥት ኤልሳበትን እኮ መሰለ? ለሁሉ ነገር እኮ ልክ አለው ልክ አለው

Post by Assegid S. » 29 Sep 2022, 12:58

RIP

It is politics. They are not doing it for the deceased but for their own politics. They took it as an ad opportunity. I can understand why they did so and what politics they wanted to play. መድፍ አለመተኮሳቸውም ገርሞኛል ... ምናልባትም መድፉ ሁሉ ወደ ሰሜን ሳይወሰድ አልቀረም።

ግለሰቡን በጥልቀት ባላውቀውም የኣዲስ ኣበባ መስተዳድር በሰበብ አስባቡ ከሚዘርፈው ላይ ቆንጥሮ ... ትንሽም ቢሆን ለሀገሩና ለሞያው አስተዋፆ ላደረገ ሰው አይደለም መንገድ ላይ ወድቆ ለተገኘም አስክሬን ይህን መሳይም አሸኛኘት ቢደረግለት ተቃውሞ የለኝም። አስክሬን ... የወዳጅም ይሁን የጠላት ይከበራል።

የእኔ ቅሬታ ግን ... በዘር መርዝ ተለከፈው የኣዲስ አበባን ወጣት በገፍ ሲያስሩና ሲያሳስሩ የነበሩትን የኣዲስ-ኣበባን ከንቲባ "ጀግናችን" እያለ በሰው ሀዘን ላይ ለመዳር ሲያሽቃብጥ በነበረው የፕሮግራሙ መሪና በኣስተናባሪዎቹ ላይ ነው። ሌላ ሌላውን ሁሉ ትተን ... እንደ ሀዘናቸው ክብደት ከየትኛውም ባለስልጣን መጀመሪያ በተለያቸው የቤተሰብ ኣባል አስክሬን ላይ የኣበባ ጉንጉን ማስቀመጥ የሚገባቸው ወላጆቹ እና ልጁ ሆነው ሳለ ይህን ክብር በስተመጨረሻ ላይ መስጠታቸው የአዘጋጆቹን ማንነት በሚገባ ያስረዳል።

I think the deceased has done and left something valuable to be remembered in the coming generations; but ... አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ አቶ ዣንጥራር ... ወይ ዘንድሮ!
ግራ የገባው ነገር ... ሊሰሙት - ሊያወሩ
ሙታን ተሰብስበው ... ህያዉን ቀበሩ
Last edited by Assegid S. on 29 Sep 2022, 13:30, edited 2 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30847
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ማዲንጎ ምን አርጎ ነው ይህ ሁሉ ሽርጉድ? የንግሥት ኤልሳበትን እኮ መሰለ? ለሁሉ ነገር እኮ ልክ አለው ልክ አለው

Post by Horus » 29 Sep 2022, 13:25

የዋህ ወገኖቼ ነገሩ እንዲህ ነው። እርግጥ ማሙድ አህመድ እና ሙላቱ አስታጥቄ የምር ያለቀሱት ሁለቱም ሞት አፋፍ ላይ ያሉ እድሜ ጠገብ ሻምግሎች ናቸው ። እነሱ የውነት የራሳቸውን ሞት በአይናቸው ስለሚያዩ ነው ። ይህ በሳይኮሎጂ የተረጋገጠ ነው ።

አቢይ አህመድ ስንት እልፍ አዕላፍ ንጹሃን፣ እናቶች፣ ህጻናት፣ አዛውንት በግፍ በጥቁር ጭካኔ ሲገደሉ አንድም ቀን ነጠላ ዘቅዝቆ፣ ባንዲራ ዝቅ አድርጎ፣ አገርና ከተማ ለለቅሶ ጠርቶ አስለቅሶ የማያውቀው አቢይ አህመድ ከሁሉም ቀድሞ ነው ሃዘኑን የገለጸው ።

ይህ ሁሉ ስል የማዲንጎን ነብስ ፈጣሪ ከጻድቃኖች ያኑር በሚል ጸሎት ነው !!!

የአቢይ አህመድ ፖለቲካ ግን ባለፈው ግዜ ለቴዲ አፍሮ 'እያመመው መጣ' ለሚለው ከባድ የናዕት ቅኔና መንግስት ወቀሳ መልስ ሲሰጥ እኔ በዩ ቲዩብና በዘፈን ከስልጣን አልወርድም ብሎ ነበር ። በትግሬ ጦርነት ውስጥ ገብተው በለው ግደለው እያሉ ወታደር አዋጊ ያልሆኑ ሙዚቀኞች አሉ። ለምሳሌ ቴዲ ለጦርነት አልዘፍንም ያለ ሰው ነው ምክኛቱም ዛሬ ሳይሆን ድሮ ጀምሮ የቴዲ አፍሮን የፍቅር አይዲዮሎጂ መንግስት እንደ ተቃወመው ነው ። በሌላ በኩል ማዲንጎ ሄዶ ለጦር ማበረታቻ ዘፍኗል። ትላንት ይህን በተመለከተ አቢይ አድንቆ ተናግሯል ። ስለዚህ ለማዲንጎ የተደረገልት ክብር እያደነቅን ፖለቲካው ምንድን ነው ላላችሁ የኔ ግላዊ መልሰ ይህ ነው ።

ዛሬ ቀዝቅዞ ቀዝቅዞ በረዶ ሊሆን የደረሰው የብልጽኛ ፕሮሞሽን ድራማ አንዳች አጋጣሚ ሲያገኝ መቆናጠጥ አመሉ እየሆነ ነው !! ችግሩ ሕዝብ ሁሉን ነገር ይታዘባል፣ ልክ እንደዚህ ውይይት ማለት ነው ። ላሊበላ በሰው ተዝካር ይጋባል እንዲሉ ነው!

Abaymado
Member
Posts: 4206
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Re: ማዲንጎ ምን አርጎ ነው ይህ ሁሉ ሽርጉድ? የንግሥት ኤልሳበትን እኮ መሰለ? ለሁሉ ነገር እኮ ልክ አለው ልክ አለው

Post by Abaymado » 29 Sep 2022, 13:34

የዚህ አገር ለቅሶ አካሄድ አቅለሽልሾኛል

አሁን ይህ የጤና ነው ወይ? በቃ ሊባል ይገባዋል :: በተለይ በእድሜ የገፉ እናቶች እየተዝናኑበት ነው ልበል?


Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ማዲንጎ ምን አርጎ ነው ይህ ሁሉ ሽርጉድ? የንግሥት ኤልሳበትን እኮ መሰለ? ለሁሉ ነገር እኮ ልክ አለው ልክ አለው

Post by Meleket » 30 Sep 2022, 03:32

"ኣንበሳው ኣገሳ!" በሚለው ዜማ ውስጥ ማዲንጎ ኣፈወርቅ በኣዛዚያሙና ውብ ቅላጼው ለሃገሩ ለኢትዮጵያ ያበረከተውን ላቅ ያለ ኣስተዋጽኦ የምናደንቅለት፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞችየኣዘዞዋ ሎዛ ማርያም ከእርሱ ጋር ትሁን እያልን፡ ወደ ሰላማዊትና ሰማያዊት ሃገሩ ለተሸጋገረው ለድምጻዊ ማዲንጎ (ተገኔ) ኣፈወርቅ መላ ቤተሰቦቹና ኣድናቂዎቹ ሁሉ መጽናናቱን እንመኛለን።

Abaymado
Member
Posts: 4206
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Re: ማዲንጎ ምን አርጎ ነው ይህ ሁሉ ሽርጉድ? የንግሥት ኤልሳበትን እኮ መሰለ? ለሁሉ ነገር እኮ ልክ አለው ልክ አለው

Post by Abaymado » 30 Sep 2022, 06:56

What about this one?



ማዲንጎ የሚመቸኝ ዘፋኝ ነው መሞቱን ስሠማ ደንግጫለሁ ኢሱን ማጣት ይከብዳል፡፡
ግን ይህ ለዛውን አጣ


Abaymado
Member
Posts: 4206
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Re: ማዲንጎ ምን አርጎ ነው ይህ ሁሉ ሽርጉድ? የንግሥት ኤልሳበትን እኮ መሰለ? ለሁሉ ነገር እኮ ልክ አለው ልክ አለው

Post by Abaymado » 02 Oct 2022, 16:30

እንደ ፋሽን እየሆነ ያለው የለቅሶ ስርእዐትና ደንብ




Selam/
Senior Member
Posts: 11800
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ማዲንጎ ምን አርጎ ነው ይህ ሁሉ ሽርጉድ? የንግሥት ኤልሳበትን እኮ መሰለ? ለሁሉ ነገር እኮ ልክ አለው ልክ አለው

Post by Selam/ » 02 Oct 2022, 17:25

ወዳጆቹና ዘመዶቹ ለምን ወይም እንዴት አዘኑ አይባልም። ፖለቲከኞቹን ተዋቸው። መጀመሪያ የሚታረዘውንና የሚረግፈውን የሚያስተዳድሩት ህዝብ ይታደጉት።

Abaymado wrote:
29 Sep 2022, 11:26
ማዲንጎ ይህ ሁሉ ክብር የተሰጠው ምን አርጎ ነው?
በሙዚቃው?
ወይስ የሃጫሉን ለመድገም?
ወይስ ለሀገር ስለዘፈነ?
ወይስ ወያኔን እንዲመታ ስለዘፈነ?

ሁሉ ነገር ልክ አለው : ለስንቱ እንዲህ ይኮናል? ደሞስ ሰው በፍላጎቱ እንጂ ዜና ተስርቶለት ሰው እንዲወጣ ተደርጎ መሆን የለበትም::

Post Reply