Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 5526
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ነጋ፣ ነጋሳ፣ ንጉስ፣ ሰላም፣ ሻሎም

Post by Naga Tuma » 27 Sep 2022, 06:03

ሰሞኑን ስለኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የተጠቀሰዉ ሀሳብ ዉስጥ ምርምር የሚሻ ጥያቄ ኣለ።

ጥንት ጊዜ ኢትዮጵያ ዉስጥ ንግስና እንዴት ተጀመረ? የመጀመርያዉ ንጉስ ማን ነበረ? መቼ ነበረ?

ከኣሁን በፊት የገዳ ስርዓትን ምን እንዲወለድ ኣደረገዉ ብዬ ጠይቄ መልስ ኣላገኘሁም።

ኣሁን ደግሞ ንግስናን ምን ጥንት ጊዜ እንዲወለድ ኣደረገዉ እላለሁ።

ምናልባት ያን ጊዜ ፀብ ካየለበት ሰላም ወደኣየለበት መሸጋገር ጋር የተያያዘ ይሆን?

የተያያዙ ከሆነ የኢትዮጵያ የጥንት ጊዜ ስልጣኔ መጀመር ከንግስና መጀመር ጋር የተያያዘ ይሆን? ንግስና መጀመሩ ሰላም ወይም ነጋ መስፈን ማለት ሊሆን ይችላል? እስራኤላዊያን ሻሎምን ከንግስና ጋር ያያይዙት ይሆን?

እነዚህ ጥያቄዎች መላምቶች ናቸዉ። የኣሌክሳንድርያዉ የጥንት ጊዜ ላይብረሪ ባይቃጠል ኖሮ መልሶች ይኖሩት ይሆናል።

ለዚህ ጥያቄዎች መልሶች የሁለተኛዉ ህዳሴ ወይም ርኔይሳንስ መሠረት ሊሆኑ ይችላሉ? ከሆኑ ሁለተኛዉ ጥንታዊ ግብፅ ተኮር የሆነ የሰዉ ዘር ህዳሴ ከመጀመርያዉ የጥንት ግሪክ ስልጣኔ ተኮር ሀዳሴ በጣም ይበልጣል የምንለዉ ያለ ምክንያት አይዴለም። የዚህ ህዳሴ መነሻ ከጥንታዊ ግብፅ ኣድናቂዎች ጥንታዊያን ግሪኮች ተኮር ስይሆን እነሱ ካደነቋቸዉ ጥንታዊያን ግብፆች ተኮር ይሆናል ማለት ነዉ።

ለዚህም ነዉ ይህ ህዳሴ ለጥንታዊየን ግብፆች ታሪክ ተገቢ ወራሾች ግስጋሴ ሊሆን የሚችለዉ።