Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በብርሃን እጦት መንገድ የጠፋቸው የኢትዮጵያ "ፖለቲከኞች"?

Post by Horus » 27 May 2022, 14:37

የስነ ምግባር ፍልስፍና እና የስነ ምግባር ንድፈ ሃሳብ የሌለው ሕዝብ ነጻነቱን፣ ፍትህን፣ ሕግና ማህበራዊ እድገት የሚተገብርበት የፖሊቲካም ሆነ ሶሺያ ስርዓት ሊፈጥር አይችልም። አንድ ማህበራዊ ስርዓት ከሌላው እንዴት እንደ ሚሻል፣ አንዱ ከሌላው ለምን እንደ ሚመረጥ መንገድ የሚያሳዩትና መምረጫ ዘዴ የሚሰጡት የሞራል ፍልስፍናዎችና የሞራል ንድፈ ሃሳቦች ናቸው። አንድ ተግባር ወይም ተቋም ጥሩ መሆኑን፣ ትክክል መሆኑን የሚነግረን ፍልስፍና ከሌለን መጥፎን ከጥሩ፣ ለከትን ከስህተት የማንለይ ያይምሮ ኣይነ ስውራን ነን። የኢትዮጵያ ብቸኛ ችግር የብርሃን እጦት ነው! በጭለማ ውስጥ መተራመስ ብዙ ሁካታ ይፈጥራል እንጂ ማንም ምን እንደ ሚያደረግ፣ ማንም ወዴት እንደ ሚሄድ አያይም። በጭለማ ውስጥ የሚመላለሱ ሕዝብ መከራ ያ ነው፤ መንገድ የላቸውም! መድረሻቸውን አያውቁም! ያሳዝናል!!

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: በብርሃን እጦት መንገድ የጠፋቸው የኢትዮጵያ "ፖለቲከኞች"?

Post by sarcasm » 27 May 2022, 15:01

ስፍር ቁጥር የሌለው ዲግሬ ማስተርስ PhD ያላቸው ልሂቃን አገሪቱ ያፈራችውን ሁሉ በጦርነት ኣውድመው፤ ኣሁን ሕዝቡን "የስነ ምግባር ፍልስፍና እና የስነ ምግባር ንድፈ ሃሳብ የሌለው ሕዝብ" እያሉ ይሰድባሉ።

union
Member+
Posts: 6046
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: በብርሃን እጦት መንገድ የጠፋቸው የኢትዮጵያ "ፖለቲከኞች"?

Post by union » 27 May 2022, 15:12

አይ አያስማማም። የኢትዮጵያ ችግር ገንዘብ እና ስልጣንን የሚያስቀድሙ ሆዳም ከሀዲዎች ለስልጣን መብቃታቸው ነው። ብርአምጡንም ጨምሮ ማለት ነው። አገር ይታመሳል ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ትምህርት ምንስቴር ቢሮ ቁጭ ብሎ ቡና ይጠጣልኛል ያለው :lol:

አሁን የትምህርት ሚንስትር መሆን እንደ ማእረግ መቆጠሩ ነው። ሰውዬው ደሀ ነው ነው ማለት ነው። ገንዘብ ነው ችግሩ እንጂ እንዴት የትምህርት ሚንስትር ስልጣን ይቀበላል። ትምህርት ለማሻሻል ምናምን የሚለው ፍገራ ተጋለጠ በአማራ ህዝብ። የወር ክፍያዋን ነው የፈለገው ይሄ መናጢ ደሀ።

የእምነት ድህነት አለ የአይምሮ ድህነት አለ የዝቅተኝነት ስሜት ጣጣ አለ። በነኚ ነገሮች ውስጥ የኖረ ሰው ደግሞ በምንም ነገር ሙሉ ሊሆን አይችልም። የግዴታ ደና ገንዘብ ያስፈልገዋል ለመኖር። ገንዘብ ደግሞ ነጭ ካልሆነ በዚህ በሽታ ውስጥ እየኖረ አይገኝም አያድግም። ቢማርም በችግር የተማረ ደሀ ነው። መጨረሻ ላይ በራሱ ፍላጎት ያቺን ገንዘብ ፍለጋ ባሪያ ነው የሚሆነው። ይክዳል ይዋሻል ይሸምጣል ያጭበረብራል ያፈናቅላል ይገላል። ከፀሀይ በታች ያሉ ክፍቶችን በሙሉ ከማድረግ ወደዃላ አይልም። ብርሀኑ ጥሩ ምሳሌ ነው። ህዝቡም ነቄ ነው ድምፁን ነፈገው :lol:

union
Member+
Posts: 6046
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: በብርሃን እጦት መንገድ የጠፋቸው የኢትዮጵያ "ፖለቲከኞች"?

Post by union » 27 May 2022, 15:37

የብዙ ኢሊት ተብዬዎች ችግራቸው ይሄ ነው። እውነቱን እያወቁ በገንዘብ እና ዝና ወዳድነታቸው ህዝባቸውን ያዋራዳሉ። ብርሀኑ አንድ ነው። እን ዳውድ እና በቀለ ገርባ ለምሳሌ አዲስ አበባ የኦሮሞ ብቻ ነው ብለው ወጥተው በሚዲያ ሲያውጅ ታሪካዊ ማስረጃ እንደሌላቸው ያውቃሉ። አማራ ጉራጌ እና ጋፍት ታሪካዊ ማስረጃ እስከ አፍጢማቸው እንደታጠቁ ያውቃሉ ግን እነሱ የዛሬዋን ጥቅማቸውን ነው የሚያስቡት። በግርግር ሊገኝ የሚችለውን ብር እና ዝና ነው የፈለጉት እንጂ መጨረሻቸው የህውሀት አይነት እንደሆነ አጥተውት አይደለም። ስለዚህ በልቼ ልሙት ነው ነገሩ። እንደ እንስሳ ማለት ነው።

የሰውን ንብረት የኔ ይላሉ። በሰው ይቀናሉ። በአቋራጭ ለመክበር ይሯሯጣሉ። አጉል ፍክክር ውስጥ ይገባሉ። በዛው ይገደላሉ።

DefendTheTruth
Member+
Posts: 9765
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: በብርሃን እጦት መንገድ የጠፋቸው የኢትዮጵያ "ፖለቲከኞች"?

Post by DefendTheTruth » 27 May 2022, 15:50

sarcasm wrote:
27 May 2022, 15:01
ስፍር ቁጥር የሌለው ዲግሬ ማስተርስ PhD ያላቸው ልሂቃን አገሪቱ ያፈራችውን ሁሉ በጦርነት ኣውድመው፤ ኣሁን ሕዝቡን "የስነ ምግባር ፍልስፍና እና የስነ ምግባር ንድፈ ሃሳብ የሌለው ሕዝብ" እያሉ ይሰድባሉ።
There is a saying which goes like: don't look at where you fell, look at where you slipped.

The problem started when a community that could deserve the name would opt to pick a 20 years old from school chair and send him to the battle front with a big fanfare, alluding to him "Our Hero".

That was the epic failure, if you want to know something.

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በብርሃን እጦት መንገድ የጠፋቸው የኢትዮጵያ "ፖለቲከኞች"?

Post by Horus » 27 May 2022, 15:50

sarcasm wrote:
27 May 2022, 15:01
ስፍር ቁጥር የሌለው ዲግሬ ማስተርስ PhD ያላቸው ልሂቃን አገሪቱ ያፈራችውን ሁሉ በጦርነት ኣውድመው፤ ኣሁን ሕዝቡን "የስነ ምግባር ፍልስፍና እና የስነ ምግባር ንድፈ ሃሳብ የሌለው ሕዝብ" እያሉ ይሰድባሉ።
sarcasm
በጦርነት የወደሙት ስፍር ቁጥር የሌላቸው የፍልስፍናና ንድፈ ሃሳብ ሊቃውንት እነማን ናቸው? አንባቢ እንዲያውቃቸው እስቲ አንድ ሁለት ብለህ በስም ዘርዝራቸው?

justo
Member
Posts: 3178
Joined: 05 May 2013, 17:54

Re: በብርሃን እጦት መንገድ የጠፋቸው የኢትዮጵያ "ፖለቲከኞች"?

Post by justo » 27 May 2022, 16:08

Horus wrote:
27 May 2022, 15:50
sarcasm wrote:
27 May 2022, 15:01
ስፍር ቁጥር የሌለው ዲግሬ ማስተርስ PhD ያላቸው ልሂቃን አገሪቱ ያፈራችውን ሁሉ በጦርነት ኣውድመው፤ ኣሁን ሕዝቡን "የስነ ምግባር ፍልስፍና እና የስነ ምግባር ንድፈ ሃሳብ የሌለው ሕዝብ" እያሉ ይሰድባሉ።
sarcasm
በጦርነት የወደሙት ስፍር ቁጥር የሌላቸው የፍልስፍናና ንድፈ ሃሳብ ሊቃውንት እነማን ናቸው? አንባቢ እንዲያውቃቸው እስቲ አንድ ሁለት ብለህ በስም ዘርዝራቸው?
Let me help you with some names
ረዳት ፕሮፈሶር መረሳ ብሩለ
ረዳት ፕሮፈሶር ወዲ ሹሚየ
ረዳት ፕሮፈሶር ወዲ ኣይኑ
ረዳት ብሮፈሶር መሃሪ
እና some more

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: በብርሃን እጦት መንገድ የጠፋቸው የኢትዮጵያ "ፖለቲከኞች"?

Post by sarcasm » 27 May 2022, 17:15

Horus wrote:
27 May 2022, 15:50
sarcasm wrote:
27 May 2022, 15:01
ስፍር ቁጥር የሌለው ዲግሬ ማስተርስ PhD ያላቸው ልሂቃን አገሪቱ ያፈራችውን ሁሉ በጦርነት ኣውድመው፤ ኣሁን ሕዝቡን "የስነ ምግባር ፍልስፍና እና የስነ ምግባር ንድፈ ሃሳብ የሌለው ሕዝብ" እያሉ ይሰድባሉ።
sarcasm
በጦርነት የወደሙት ስፍር ቁጥር የሌላቸው የፍልስፍናና ንድፈ ሃሳብ ሊቃውንት እነማን ናቸው? አንባቢ እንዲያውቃቸው እስቲ አንድ ሁለት ብለህ በስም ዘርዝራቸው?
አገሪቱ ያፈራችውን ቁሳዊ ነገሮች ማለቴ ነው

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: በብርሃን እጦት መንገድ የጠፋቸው የኢትዮጵያ "ፖለቲከኞች"?

Post by Sam Ebalalehu » 27 May 2022, 18:36

Eden ቁሳዊ ነገሮች ግዜ ይውሰዱ እንጂ ይመጠሉ ። እኔ ያ አያሳስበኝም። አንተማ ምንችግር አለብህ ትይ ይሆናል ። አንቺም እንደምገምተው የራስሽ ቁሳዊ ችግር አይመስለኝም ያሳሰበሽ። ሀያ አራት ሰአት ER ላይ የሚያነጃብብ ፍጡር ቁሳዊ ችግር ይኖርበታል ብሎ መገመት ይቸግራል። የሰፊው ህዝብ ችግር ነው እነደምገምተው እንቅልፍ የነሳሽ። እኔን እንቅልፍ የሚነሳ በተቃራኒዉ የበሰሉ ፣ አርቆ ማሰብ የሚችሉ ፣ ከራሳቸው ጥቅም ይልቅ የአገር የሚያስቀድሙ ፣ ከስህተታቸው መማር የሚችሉ፣ የፖለቲካ መሪዎች አለመኖራቸው ነው። እነሱ ካሉ ቁሳዊ እርካታ መከተሉ የግድ ነው።

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በብርሃን እጦት መንገድ የጠፋቸው የኢትዮጵያ "ፖለቲከኞች"?

Post by Horus » 27 May 2022, 20:00

sarcasm
ስማቸውን ጥቀስ ያልኩህኮ አለ ምክንያት አልነበረም! በስም ልትጠራቸው እንደ ማትችል ስለማውቅ ነው! ለምን ካልክ መልሱ የሉም ነው ። ቢኖሩማ ከ50 አመት ጦርነት በኋላ የትግሬ ሕዝብ የተባበሩት መንግስታት ስንዴ ተመጽዋች አይሆንም ነበር ። ዛሬ በዚህ ሰዓት ለትግሬ ሕዝብ የሚጠቅም ሃሳብና ስርዓት ምንድን ነው ብሎ የሚጠይቅ አንድ የትግሬ ልሂቅ የለም! ለምን ካልከኝ ትግሬ ያን የሚያደርግበት የስነ ምግባር ፍልስፍናና ንድፈ ሃሳብ የለውም ። አማራን መጥላትና አቢይን መስደብ ፍልስፍናም ንደፈ ሃሳብም አይደለም ።

እንኳንስ ከጦርነትና ከንዴት ብዛት ማሰብ ያቆመው የትግሬ ፖለቲከኛ ተውና በዳኛቸው አሰፋ ፍልስፍና አስተማሪነት ፊሎሶፊ የተማረው ሺመልስ አብዲሳ የፍልስፍና ጨዋ መሆኑን የምታውቀው መላ ኦሮሞ በክልልና አውራጃ ቀውስ ሲናጋበት የሄደው እውነተኛ መፍትሄ ፍለጋ ሳይሆን በኦሮሞ የማይሰራው የገዳ ሲስተም በኢትዮጵያ አሰፍናለሁ ወደ ማለት ነው! ያ ለኦሮሞ ሕዝብ ሽያጭ የቀረበ መደለያ ማለት ነው።

አማራም ውስጥ ያለው ችግር ይህ ነው። ማንም ምን አይነት ሰርዓት እንደ ሚጠቅመው፣ እንደ ሚፈልግ በውል የሚያውቅ የለም ።

በአንድ ቃል 'እልፍ አእላፍ' ያልካቸው የፍልስፍናና ቲኦሪ ሊቃውንት የሉም! እነዚያን ቃላት አትጠቀም፣ ባዶ ሰልሆኑ!

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: በብርሃን እጦት መንገድ የጠፋቸው የኢትዮጵያ "ፖለቲከኞች"?

Post by Sam Ebalalehu » 27 May 2022, 20:23

Eden, የመጨረሻውን የ Horus አረፍተነገር አብላሊው። ትርጉም — ያልተፃፈ አታንብቢ። ሰዎቹ በዛሪይቱ ኢትዮጵያ የሉም። I happen to agree with him.

Post Reply