Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12534
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

必读 ! ስለ ትግራይ መከላከያ አማሮች ምን ይላሉ ?

Post by Thomas H » 23 Oct 2021, 10:03

Abrar Mahmud
ለሽንፈቱ ሌላ ሚስጥር የለውም፤ ተጋሩ ሲበዛ ተዋጊዎች ናቸው። እነሱ እንደሚሉት "ውጊያ ባህላችን ነው" ይላሉ፤ ትክክል ነው። ከጥንት ጀምሮ ታሪክን ስንቃኝ ብቻቸውን ገጥመው የሚከተሉትን ወራሪዎችን በኋላ ቀር መሳሪያ አሸንፈዋል።
1. ከግብፆች ጋር :– ጉንደት (1875) ፣ጉራእ (1876)፣ አይለት (1887)፣ ሰንሂት (1880)
2. ከማህዲስቶች ጋር :– መተማ (1885)
3. ከጣሊያን ገር :– በሳሃቲት (1887) ፣ ዶግአሊ (1887)፣ አምባላጌ (1889)
4. ከኃ/ስላሴ ጋር :– ቀዳማይ ወያኔ
5. ከደርግ ጋር ለ17 ዓመት በርሃ ወጥተው ገጥመው አሸንፈዋል።
6. አሁን ደግሞ በብለፅግና ለአንድ ዓመት ገጥመው እያሸነፉ ይገኛሉ።
ስለዚህ አብረን እየኖርን የተጋሩ ጀግንነት ብዙም አንገነዘብም። ለሽንፈቱ ሌላ ምክንያት መጥራት ቂላቂልነት ነው። እነሱ (TDF) ከውጭ ጦር መሳሪያ እንዳያስገቡ 360° ተከበዋል፤ የሚላስ የሚቀመስ አያገኙም፣ በጀት የሚባል የለም። ትልቁ ሃይላቸው ህዝባቸው ነው፤ ትልቁ መሳሪያቸው ህዝባቸው ነው፤ ትልቁ ስንቃቸው ህዝባቸው ነው። ከዚህ ህዝብ የወጡ የጦር መሃንዲሶች በርካታ ናቸው። አዱሱ ትውልድም ከአባቶቹ ተምሮ የጦር ሊሂቅ ሆነዋል። የድላቸው ሚስጥር ከዚህ በላይ በመሆኑ በጥንቃቄ ማጥናት ያስፈልጋል።