Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Horus
Senior Member+
Posts: 21370
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አዲሱ የኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካ ምንድን ነው? ያሜሪካና ሩሲያ አቋም?

Post by Horus » 22 Oct 2021, 12:43

አንድ፣
ኢትዮጵያ በአጭር ግዜ ወስጥ ሕዝቧን አንድ አድርጋ፣ አባይን ሞልታ፣ ምርጫ አድርጋ፣ አዲስ መንግስት መስርታ፣ ግዙፍ ጦርና ሰራዊት መልምላ በመውጣቷ ሳቢያ የሃያላኖች ስሌት ተለውጦ አዲስ የፖለቲካ አሰላለፍ እያመጣ ነው።

ሁለት፣
አሜሪካና አውሮፓ የትግሬ ባንዳን በመደገፍ ኢትዮጵያን አምበርክከው ቻይናን፣ ሩሲያን፣ እና ቱርክን ካፍሪካ ቀንድ ለማባረር ያደረጉት ጥረት ከሽፏል። ከዚያ ጋር ተያይዞም ግብጽ የኢትዮጵያን የዉሃ ልማት ለማስቆም የምታደርገው ጥረት ከሽፏል።

ሶስት፣፣
በአሜሪካና አውሮጳ የሚነዳው የተባበሩት መንግስታት አውቆም ሆነ ሳያውቅ፣ ፈቅዶም ሆነ ሳይፈቅድ በኢትዮጵያ ላይ ያቀናበረው ግፊትና ለትግሬ ባንዳ ያደረገው እርዳታ በራሱ ላይ ባርቆበት በታሪኩ ግዙፍ የሚባል ውስጣዊ ቀውስ አስከትሎበታል ። በተለይ አንቶኒዮ ጉቴሬስ ኢትዮጵያ የትግሬን ጦር አታሸንፍምና ተደረደሩ ያለ ነገር በታሪክ የማይረሳ ስህተት ሆኖ ይኖራል። ስለሆነም ተመድ ከትግሬ ባንዳ እየራቀ ይገኛል።

አራት፣
ስለሆነም አሜሪካ፣ አውሮጳ፣ እና ሩሲያ የትግሬ ባንዳ ጦር ኢትዮጵያን ሊያሸንፍ አይችልም፣ ተመልሶ ወደ ማዕከላዊ ስልጣን የመውጣት እድሉ ዜሮ ስለሆነ ሁሉም የሚስማሙበት ፖሊሲ የትግሬን ጉዳይ በሰላም መፍታት በሚለው ላይ ነው ። አሜሪካ ይህን አቋሟ ለትግሬ በመንገሯ ነው ጌታቸው ረዳ የትግሬ ጦር በአየር መቃወሚያ እየተከላከለ ነው፣ ሙሉ ሃይል አለን፣ ጠቅላላ፣ ግራንድ ኦፈንሲቭ እናደርጋለን እያለ አሜርካና አውሮጳን ለመሸወድ የሚለፋው።
በዚህ ለውጥ ሳቢያ ነው አሜሪካኖች አውሮፓዎች፣ ተመዶች ፣ የምራብ ሚዲያዎች ነጋ ጠባ በኢትዮጵያ ላይ የሚያዘንቡት ማስፈራሪያ የቆመው።

አምስት፣
በእኔ ግምት አሁን ያሜሪካም ሆነ የሩሲያ ፍርሃት የኢትዮጵያ ጦር ትግሬን ካማራና አፋር ካባረረ በኋላ ተመልሶ ትግሬ ውስጥ ይገባል ወይስ ትግሬ ድምበር ላይ ቆሞ ተኩስ ያቆማል? የሚለው ነው ። ይህ ለአቢይም ጄኒራሎች ትልቅ ጥያቄ ነው ።

ስድስት፣
በእኔ ግምት አሜሪካና ሩሲያ የተስማሙበት አንድ ነገር አለ፤ እሱም ኢትዮጵያን መደገፍ፣ የትግሬን ጦር ማፍረስ፣ ግን የኢትዮጵያ ሰራዊት እንደ ገና ትግሬ ገብቶ ሌላ የጦርነት አዙሪት እንዳይፈጥር መምከር፣ አለመደገፍ ወይም መከልከል ነው ። ይህም ስለሆነ ነው ዛሬ ሩሲያ ሁለቱም ወገኖች ባስቸኳይ ተኩስ አቁሙ የሚል መግለጫ ያወጣችው። ይህ የተመድም አቋም ነው ። ይህም ስለሆነ ነው የኢትዮጵያ ጄቶች የባዳንውን ጦር ተቋማት ሲደበድቡ አሜሪካኖች ጆሮ ዳባ ልበስ ያሉት ። ትግሬ ሁለተኛ መደበኛ ጦርነት የማድረግ አቅሙ መክሰም እንዳለበት ሃያላኖቹ ተስማምተዋል።

ሰባት፣
የትግሬ ጦረኝነት ካልቸርና ረሃብተኝነት እውነታ ለምራብም ለምስራቅም ሃያላን የማይዋጥ፣ እነሱንም የማይጠቅም፣ አካባቢውን የሚያምስ እና ለአለም አሸባሪዎች ሁሉ ሜዳ የሚጠርግ ስለሆነ ትግሬ ከዚህ በኋላ ከጎሬላ ጦርነት ያለፈ አመጽ ሊፈይድ አይችልም ። አሜሪካ ይህን የተገነዘበችው የትግሬ ባንዳ የተመድ ትራኮች ሰርቆ ተዋጊ ያመላለሰ ቀን ነው ። ትግሬ መደበኛ ጦር የለውም።

ስምንት ፣
የኢትዮጵያ መንግስትም ቢሆን አሁን አንድ ትልቅ እስትራተጂክ ጥያቄ መፍታት አለበት፣ ይፈታል ማለት ነው። ያም ጥያቄ የባንዳው ጦር ካማራና አፋር ከተወገደ በኋልና ቁልፍ ጦር የመዋጋት አቅሙ ከከሰመ በኋል ያገር ሰራዊት ትግሬ ገብቶ ወያኔን ለመልቀም ይሞክር ወይስ በትግሬ ዙሪያ አጥሮ በመስፈር ትግሬዎች ጉዳያቸውን እንዲጨርሱ መተው የሚለው ነው ።

የእኔ እምነት ሁለተኛው ነው ። የሚቀጥለው የትግሬ ችግር የረሃብና የራሱ የጦርነት ካልቸር ችግር ነው። ካልቸር ባህሪ ነው፣ ባንዴ አይለወጥም፣ ትግሬ ብዙ ብዙ ትራማ የተካሄደበት፣ ሳይኮሎጂው የታመመ ማህበረሰብ ነው ። ስለሆነ እነሱ ችግራቸውን የሚያሳብቡበት የውጭ ሃይል እስካገኙ ድረስ ወደ ራሳቸው መመልከት አይፈልጉም ። በመሆኑም ትግሬዎችን ለብቻቸው ትቶ ለ50 አመት ያከማቹትን የቀውስ ክምር ራሳቸው እንዲፈቱት መተው ነው ።

ሆረስ ዘ ፋልከን
Last edited by Horus on 22 Oct 2021, 16:51, edited 2 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 21370
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ የኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካ ምንድን ነው? ያሜሪካና ሩሲያ አቋም?

Post by Horus » 22 Oct 2021, 13:15


Last edited by Horus on 22 Oct 2021, 13:37, edited 2 times in total.Horus
Senior Member+
Posts: 21370
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ የኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካ ምንድን ነው? ያሜሪካና ሩሲያ አቋም?

Post by Horus » 22 Oct 2021, 15:23

ያው ሰሞኑን ስንለው እንደ ነበረው አሜሪካ እያፈገች ይቺ ተረስታ የነበች ህንዳዊት አሁን ብቅ ብቅ ማለት ጀመረች ። እነብሊንከን ና ሳማንታ ዝም በሉ ተብለዋል ።

https://et.usembassy.gov/u-s-ambassador ... bahir-dar/

Horus
Senior Member+
Posts: 21370
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ የኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካ ምንድን ነው? ያሜሪካና ሩሲያ አቋም?

Post by Horus » 22 Oct 2021, 16:39

ይህ ጉድ ስሙ!
22 ትራክ ሙሉ የባንዳ መንጋ ጦር እስከነ ትራኩ ሲጋይ ....
ተመድ የሰጣቸው 400 ትራኮች ተራ በትራ በጄት እየነደዱ ነው
ሌላውን ስሙ ከወሎ ገበሬ ፍየል ዘርፎ አርዶ ሲጠብስ በጄት የተቆላውን የባንዳ መንጋ ጉድ ስሙ
ገና መቀሌ ሕዝባዊ አመጽ በባንዳው ላይ ይነሳል
ለመሆኑ ባንዳው የተመድ አይሮፕላን እንዳያርፍ ማድረጋቸው ለምን? ተመድ የኢትዮጵያ አየር ሃይል እንዲቃወምላቸው ተብሎ ከሆነ እጅግ ያስቃል !

Last edited by Horus on 22 Oct 2021, 16:46, edited 1 time in total.

Jaegol
Member
Posts: 751
Joined: 31 Oct 2019, 20:06

Re: አዲሱ የኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካ ምንድን ነው? ያሜሪካና ሩሲያ አቋም?

Post by Jaegol » 22 Oct 2021, 16:44

Chigaram kilil is the new Gaza… the job ahead is to make tplf a toothless terrorist org like hamas and keep them in their cage, if they try to attack their neighbors and retaliation 10 x their aggression
The above should be the new policy unit Biden/ Susan rice leave office in 3 years… then evaluate

Post Reply