Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Horus
Senior Member
Posts: 19871
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ኢዜማ ከ70 እስከ 100 የፓርላማ ወምበሮች ያሸንፋል

Post by Horus » 17 Jun 2021, 23:00

የኢትዮጵያ ፓርላማ ወምበሮች ቁጥር ክፍፍል
ጁን 17 2021

ተራ ቁጥር ክልል ወምበር ቁጥር ብልጽግና ኢዜማ ሌሎች
1 ኦሮሚያ 178
2 አማራ 138
3 ደቡብ 123
4 ትግሬ 38
5 ሱማሌ 23
6 አዲስ አበባ 23
7 ቤኒሻንጉል 9
8 አፋር 8
9 ጋምቤላ 3
10 ሃረሬ 2
11 ድሬ ደዋ 2

ድምር
አገር አቀፍ
547

አሸናፊ
50% +1 ማጆሪቲ
275

ሰኔ 14
ምርጫ ያደረጉ
445

ጳጉሜ 1
ምርጫ የሚያደርጉ
64

ወደ ፊት
ትግሬ
38

የሰኔ 14 ውጤት
275/445 አሸናፊ
62%

ሰኔ 14
አዲስ አበባ ምክር ቤት
138

ስለዚህ በነገው ምርጫ አሸናፊ የሚሆነው ፓርቲ ከ445 ወምበሮች 275 ወይም 62% ወምበር ማግኘት አለበት

በፓሬቶ ሕግ መሰረት የአንድ ነገር 80% ዉጤት የሚከወነው በ20% ሰራተኛ ነው ። ስለሆነም በሚመጣው መንስት ወስጥ ስኬታማ ለውጥ ለማምጣት ኢዜማ በግድ እንዲኖረው የሚያስፈልግ 100 ብቁ ወኮሎች ብቻ ነው ፣ ማለትም ረኳየርድ ሚኒማ ማለት ነው ።
Last edited by Horus on 18 Jun 2021, 01:17, edited 2 times in total.

Horus
Senior Member
Posts: 19871
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሴኔ 14 2013 ምርጫ ወምበር ቁጥር ቀመር፡ ኢዜማ በግድ ማሸነፍ ያለበት 100 መቀመጫ ብቻ ነው! ለምን?

Post by Horus » 18 Jun 2021, 00:36

ኢዜማ የኢትዮጵያ ፖለቲካና መንግስት ላይ በቂ በሆነ ተ ጽ ዕ ኖ ለማድረግ ማጂክ ቁጥሩ 100 ወንበር ነው ብያለሁ ። መሬት ባለው ሁኔታ መሰረት ስገምት ግን ማናልባት ከ72 መቀመጫዎች በላይ ላያገኝ ይችላል ። ስለሆነም የተፎካካሪ ቅንጅት ፓርላማ ውስጥ ከነ እናት እና ሌሎች ጋር ማድረግ ይኖርበት ይሆናል ። ተፎካካሪዎች ተደምረው ከ100 በላይ ቦታ ያገኛሉ!!

Horus
Senior Member
Posts: 19871
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሴኔ 14 2013 ምርጫ ወምበር ቁጥር ቀመር፡ ኢዜማ በግድ ማሸነፍ ያለበት 100 መቀመጫ ብቻ ነው! ለምን?

Post by Horus » 18 Jun 2021, 00:57

የኢዜማ 72 ማናልባት ወምበሮች ...
ከደቡብ 37
ከአማራ 20
ከአዲስ አበባ 10
ኦሮሚያ 5
ድምር 72

ስለዚህ ኢዜማ 100 መቀመጫ ወይም ከዚያ ካገኘ ታሪካዊ ክስተት ይሆናል !!

tolcha
Member
Posts: 3069
Joined: 27 Feb 2013, 16:51

Re: ኢዜማ ከ70 እስከ 100 የፓርላማ ወምበሮች ያሸንፋል

Post by tolcha » 18 Jun 2021, 03:55

Ayee ye Gurage potolika. Ante zim bileh qixihin amuqi!!!

Horus
Senior Member
Posts: 19871
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢዜማ ከ70 እስከ 100 የፓርላማ ወምበሮች ያሸንፋል

Post by Horus » 18 Jun 2021, 12:19

ብርቱካን አስደናቂ ማኔጀር፣ ታማኝ፣ ጽኑ ሴት!! ኢትዮጵያ ድምጽ መስጫ ካርዶች በአይሮፕላን እያከፋፈለች ነው ፣ ድንቅ አኩሪ ችሎታ !!

ብርቱካን መደቅሳ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እናት !!!


Horus
Senior Member
Posts: 19871
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢዜማ ከ70 እስከ 100 የፓርላማ ወምበሮች ያሸንፋል

Post by Horus » 19 Jun 2021, 23:27

እኔ እንደ መረራ ጉዲና የሚያሳዝነኝ ሰው የለም። ድሮ ከነኢህ አፓ ጋር ሚኤሶን ሆኖ ጀመረ። ቀስ በቀስ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ወጣና የኦሮሞ ልዝብ ሆነ ። ኖሮ ኖሮ ለመጀመሪያ ግዜ ሻል ያለ ምርጫ ሲደረግ እንደ ህጻን አኩርፎ ወጥቶ ቁጭ አለ። ይህም የሚያሳየው እሱ ስለፖለቲካ ማውራት እንጂ የውነት መሪ ሆኖ አንድ ነገር መለወጥ የማይፈልግ ሰው መሆኑን ነው።

Horus
Senior Member
Posts: 19871
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢዜማ ከ70 እስከ 100 የፓርላማ ወምበሮች ያሸንፋል

Post by Horus » 21 Jun 2021, 04:07

ምርጫ ምናደርገው ለራሳችን እንጂ አሜሪካን ወይም አውሮፓን ለማስደሰት አይደለም ! ፕሮፍ ብርሃኑ ነጋ !Horus
Senior Member
Posts: 19871
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢዜማ ከ70 እስከ 100 የፓርላማ ወምበሮች ያሸንፋል

Post by Horus » 22 Jun 2021, 03:24

አሁን ረፖርት በሚደረጉት ቁጥሮች መሰረት ለኢዜማ የገመትኩት 70 እስከ 100 ወንበር በእጅጉን ዝቅ ማድረግ ይኖርብኛል ። የሩስኪው ሌኒን መጥፎ ቲኦሪ በጥሩ ተግባር ይታረማል ብሎ ነበር ። ድምጽ አሰጣጡ እጅግ ባብዛኛው በጎሳ ማንነት መለኪያ የተወሰነ ይመስለኛል ። ያው እንደ ተባለው የጎሳ ንቃተ ህሊና መቆየቱ ግልጽ ነው ።

Blueshift
Member
Posts: 653
Joined: 30 Mar 2021, 19:34

Re: ኢዜማ ከ70 እስከ 100 የፓርላማ ወምበሮች ያሸንፋል

Post by Blueshift » 22 Jun 2021, 03:39

Horus,

During the war, the man in charge is very popular. As a consequence, his party becomes very popular as well. It was given that Abbiy and the prosperity party were going to win big. I could have told you that. BTW, Abbiy is not democratic. He does not have to tell you that. All you have to do is read his lips. From now on, he will be more dictatorial. Just watch. :lol: :lol: :lol: Here is something to watch too. Agames will give him a lot of headache. He will withdraw his troops from Tigray. Tigray will be in limbo. :lol: Tigrayans and Amharas will fight it out for Western Tigray or Northern Amhara territories. I could be wrong. 90% of the time, I am always right. I am a good predictor. :lol:

DefendTheTruth
Member
Posts: 4866
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: ኢዜማ ከ70 እስከ 100 የፓርላማ ወምበሮች ያሸንፋል

Post by DefendTheTruth » 23 Jun 2021, 09:03

Horus,

please update us about your predictions fulfilment.I am not sure if this video is accurate but it is really bad for the development of democracy in our country. I liked the Prof.'s course politics ever since he returned back home to contribute to the effort of rebuilding our country.

Does your style of my way or the high-way contributed to the debacle of this party?

experts
Member
Posts: 199
Joined: 26 Apr 2019, 10:55

Re: ኢዜማ ከ70 እስከ 100 የፓርላማ ወምበሮች ያሸንፋል

Post by experts » 23 Jun 2021, 13:22

Horus. ለቅሶ ላይ ነው። እናዝናለን ብር አሁን ስልጣን ሚባል ነገር አያይም።

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 2821
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: ኢዜማ ከ70 እስከ 100 የፓርላማ ወምበሮች ያሸንፋል

Post by Za-Ilmaknun » 23 Jun 2021, 13:44

EZEMA promoted a politics that seemed focused on protecting the ruling party than forwarding an alternative politics that targeted the national sentiments of its supposed constituents. Opposition politics should also try to responsibly expose the weakness of one's opponents and create alliance with parties that share same vision.

The field was so crowded with so many parties with no meaningful differences. I am not sure what the difference between the party that calls itself "Enat" and EZEMA is. EZEMA could have worked with Balderas instead of trying to alienate the latter. Balderas came to the forefront in response to EZEMA's half-hearted opposition against the ruling party in matters that are so crucial to the City, its residents and the country at large.

Horus
Senior Member
Posts: 19871
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢዜማ ከ70 እስከ 100 የፓርላማ ወምበሮች ያሸንፋል

Post by Horus » 23 Jun 2021, 13:51

ኢዜማ የረባ የፖለቲካ ተጽዕኖ ለመፍጠር ወደ 20% የሚጠጋ ወንበር እንደ ሚፈልግ አስልቼ ከ70 እስከ 100 ወንበር እንዲኖረው ማስፈለጉን ተስፋ አድርጌ ያለኝ አስፐሪሽን ከላይ ብያለሁ ። ይህ የኔ የግል አስፐሬሽን ነበር ። በመሬት ላይ አገር ቤት ያለው ሪያሊቲ ከኔ ምኞት የተለየ ሆነ ። በቃ ሌላ ነገር የለውም ። መሰረታዊ ትንተናዬ በዚያቅ ቀን ብዬዋለሁ ። ያስገረመኝ ነገር ቢኖር ሕዝቡ ድምጹን ይህን ያህል መንፈጉ እንጂ እኔ ኢዜማ አቢይን ያሸንፋል የሚል እምነትም ሃሳብም ኖሮኝ አላቅም ።

እኔ ሆረስ ነኝ፣ ቃል አልፈልጥም! የኢትዮጵያ 2013 ምርጫ ሙሉ ግምገማ ገና አልተደረገም። ነገር ግን በብዙ ብዙ መንገድ ይህ ምርጫ የኢትዮጵያን ፖለቲካ የሚለውጥ ስለሆነ በአንጎሌ ጫፍ ላይ ሳይሆን በልቤ ስር ጥልቅ ደስታ ተሰምቶኛል ። ለምን?

እኔ የማምንበት ነገር አለ፣ ቲኦሪ ሃሳብ ነው፣ ምናብ ነው። ያ ቲኦሪ የሚፈተነው በተግባር ነው ። ጥሩ ቲኦሪ ብቻውን ጥሩ ተግባር አይሆንም። ጥሩ ተግባር የራሱ ሕግ አለው ። እሱን የተግባር ፍልስፍና፣ ዘ ፊሎሶፊ ኦፍ አክሽን ወይም ሆነ ብለን የምናደገው ተግባር ፍልስፍና ይባላል።

ፖለቲካም እንዲሁ የተግባር ህግ አለው ። ላንድ ፖለቲካኛ የፖለቲካ ተግባሩ ቁልፍ ቁም ነገር ቁልጭ አግድርጎ በአንድ ቃል ለማስቀመጥ መቻል አለበት ።

የ2013 ምርጫ አላማ ምንድን ነው ለሚለው ቁጥር አንድ ጥያቄ እኔ ደግሜ ደግሜ እንዳልኩት የዚህ ምርጫ ግብ በሕዝቡ እይታና ፍላጎት አንድ ያለን መንግስት ለመለወጥ፣ አንድ ሪጂም ወይም አስተዳደር ካንዱ ቡድን ወደ ሌላ ቡድን ለመለወጥ አይደለም ብያለሁ ። የህዝቡ ፍላጎ በወያኔ ተሰባብሮ ተፍረክርኮ ያለውን መንግስት ማጠንከር፣ አገር አንድ አድርጎ ማጠንከር ነው የህዝቡ መሰረታዊ ጥያቄና ፍላጎት ።

ይህ ነው የዚህ ምርጫ ተግባር ፍልስፍና መቆሚያ ! ስለሆነም በምርጫው ከተካፈሉት ዋና ዋና ፓርቲዎች ስንቶቹ ይህን ፍልስፍና እንደሚገባቸው አላቅም ። ኢዜማ አንድም ግዜ በዚህ ምርጫ ሲወዳደር አላማው የአቢይን መንግስት አውርዶ ሌላ አዲስ የኢዜማ መንግስት ለማምጣት ነው ብሎ አያውቅም ። ስለዚህ ኢዜማ በዚህ ምርጫ የብልጽግና አጋር እንጂ ተቃራኒ አልነበረም ።

ይህ አቋም ትክክል ነበር ። ሕዝቡ ዛሬ የመሰከረው ያንን ነው ። ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ያላቸው ፍላጎት ጠንካራ፣ ሰላም የሚያስጠብቅ፣ አገር የሚያስቀጥል መንግስት ማደራጀት እንጂ የአቢይን መንግስት አውርዶ አዲስ መንግስት ለመሆን አይደለም። ይህን የማያውቅ ፖለቲከኛ ወደ ሌላ ስራ መሄድ አለበት ።

ከሁሉም አስቀድሞ ህዝቡ ፖለቲከኞችን ያስተማረው ትምህርት ይህ ነው። እያንዳንዱ ምርጫ የዚያን ወቅት ግብና አጀንዳ አለው ፣ የዛሬ ምርጫ አጀንዳ ሰላም ማስፈን እንጂ መንግስት መለወጥ አይደለም ፤ የሆነውም ያ ነው ።

እነኢዜማ ፣ አብን ፣ ባልደራስ ፣ ምናምን ለምን የሕዝብ ድምጽ ተከለከሉ? ከላይ ብዬዋለሁ! የተሳሳተ የመሪዎች ቲኦሪ በትክክለኛ የህዝብ ተግባር ይታረማል ይባላል።
እኔ ላለፈው 30 አመት በኢትዮጵያ ከ4 ወይ 5 ፓርቲዎች በላይ መኖር የለባቸውውም ብያለሁ፤ አሁንም እላለሁ ። ዛሬ ህዝቡ የላከው ትምህርት ያ ነው። ወይ አንድ ሁኑ ወይ ወግዱ ነው ያለው ሕዝቡ ።

በኢትዮጵያ አንድ በጎሳ ቀመር የቆመ ፓርቲ አለ፣ እሱም ብልጽግና ነው ። በዜጋ ፖለቲካ ቀመር የሚቆሙ አንድ ሊብራል ፣አንድ ሶሺያል ዴሞክራሲ ፣አንድ ወግ አጥባቂ ፓርቲዎች ሊኖሩ ይችላሉ ። ሌላ አንድ አረንጓዴ ፓርቲ ሊኖር ይችላል። በቃ ከዚህ አልፈው በግለሰቦች ምኞትና ድንቁርና ላይ የቆሙ 50፣ 100 ፓርቲዎች በህዝብ እንደ ሚወገዱ ይህው አየን፣ አበቃ ! የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግስት አደራጅ እንጂ መንግስት እና አገር ማፍረሻ መሳሪያዎች አይደሉም ። ፓርቲ ድርጅት ነው፣ ድርጅት መሳሪያ ነው ።

ሶስተኛው፣ ኢዜማ ለምን ድምጽ ተነፈገ የሚለው ቀላል ጥያቄ ነው! ፈረንጆች ፖለቲካ የሰፈር ጨዋታ፣ የሰፈር ትግል ነው ይላሉ ። ይህም ማለት በዴሞክራሲ ውስጥ አንድ ግለሰብ ምረጡኝ ለማለት እሱ ወይም እሷ በዝርዝር ለዚያ ሰፈር፣ ለዚያ መራጭ ህዝብ ሊያደርግ፣ ምን ሊያሻሽል እንዳቀደ እና ያም ዝርዝር የሰፈር ግብ ከሌላው ፓርቲ ፕላን እንዴት እንደ ሚሻል በፋክት፣ በግልጽ ህዝቡን ማሳመን አለበት ።

ኢዜማ አንድም ቦታ ይህን ሲያደርግ አልታየም፣ ኢዜማ በፍልስፍና በዜጋ ፖለቲካ ንድፈ ነገር ከብልጽግና መለየቱ ቢታወቅም ሪቴይል ፖለቲካ ወይም የፖለቲካ ችርቻሮ የሚባለው ጭብጥ፣ የሚዳሰስ፣ የሚቀመስ ጥቅም ለህዝብ ስላላቀረበ ህዝቡ ድምጹን የሚስጥለት ምክንያት አልነበረም። ይህው ነው ሌላ ምስጢር የለውም ።

ስለሆነም ይህ ምርጫ የብዙሃኖች ጥበብ ወይም ዊዝደም ኦፍ ዘ ማስስ የተረጋገጠበት ልምድ ነው ። ይህ ማለት በተለይ ብልጽግናና ኢዜማ ግልጽ የሆነ የአጭር ግዜ ልዩነት ስለሌላቸው ፣ ፈረንጅ እንደ ሚለው ለአንድ ስራ ሁለት ሰው ከቀጠርክ አንዱን አባርር ፣ ሰዉ ብልህ፣ ብልጥ ስለሆነ ሰላምና ጸጥታ ላይ ያለውን ቡድን አጠናክሮ ጠንካራ አገር እና መንግስት እንዲኖር ድምጹን ለዚያ ሰጠ ። ይህ ነው ምስጢሩ !!

ኢዜማ አልተሸነፈም ፣ ያልጠየቀውን ሊሰጠው አይችልም ። የጎሳው ሲስተም፣ የጎሳው መዋቅር ላይ ኢዜማ ቦታ እንደሌለው ፣ኢዜማ ሊመራው ሊቆጣጠረው የሚችል እስትራክቸር እንዳልሆነ ከኢዜማ በላይ ህዝቡ አውቆ የተሳሳተውን ቲኦሪ አርሞላቸዋል ። ኢዜማ በኤትኖክራሲ ላይ ዴሞክራሲ ለተገብር አይችልም ። ኢጎሳዊ ሲስተም እስከሌለ ድረስ ኢዜማ መንግሳትዊ ስልጣን ልይዝ አይችልም ። ይህ የፖልቲካ ሕግ ነው።

የኢዜማ አላማና ስራ ኢጎሳዊ የሆነ የዜጎች ሲስተም መፍጠር ስለሆነ ወደዚያ ተግባሩ ይሄዳል ማለት ነው።

ይህ ምርጫ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ህይወት ላንዴም ለሁሌም ይለውጣል የሚል እምነት አለኝ ። በሌላ ፖስት ላይ እንዳልኩት የዜጋ ፓርቲዎች ቢያንስ 20% ወንበር ካላገኙ የብልጽግና ማጣፈጫ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ ስለማይኖራቸው ፓርላማ ከመቀመጥ አለመግባታቸው የተሻለው ነው። የዛሬ አምስት አመት 2 ወይም 3 አገር አቀፍ ፓርቲ ሆነው ይምጡ። እስከዚያ ኢትዮጵያ አባይን ትሙላ !! በቃ
Last edited by Horus on 24 Jun 2021, 01:53, edited 3 times in total.

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 2821
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: ኢዜማ ከ70 እስከ 100 የፓርላማ ወምበሮች ያሸንፋል

Post by Za-Ilmaknun » 23 Jun 2021, 14:31

Blueshift wrote:
22 Jun 2021, 03:39
Horus,

During the war, the man in charge is very popular. As a consequence, his party becomes very popular as well. It was given that Abbiy and the prosperity party were going to win big. I could have told you that. BTW, Abbiy is not democratic. He does not have to tell you that. All you have to do is read his lips. From now on, he will be more dictatorial. Just watch. :lol: :lol: :lol: Here is something to watch too. Agames will give him a lot of headache. He will withdraw his troops from Tigray. Tigray will be in limbo. :lol: Tigrayans and Amharas will fight it out for Western Tigray or Northern Amhara territories. I could be wrong. 90% of the time, I am always right. I am a good predictor. :lol: :
So you are confirming the war on TPLF is a very popular war.. :| Better to have a dictator who is able to peacefully rule the country than ethnic entrepreneurs who would loot the country bone dry and perpetually promote communal strife. There never was a Wester Tigrai a few years ago and please also get a grip that there won't be any until judgement day. The occupation has ended. Deal with it loser !! :mrgreen:I forgot, how about Badime and half of Irob?? :lol: :lol

DefendTheTruth
Member
Posts: 4866
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: ኢዜማ ከ70 እስከ 100 የፓርላማ ወምበሮች ያሸንፋል

Post by DefendTheTruth » 23 Jun 2021, 15:02

Horus,

I think you are saying people have got real interests and they make their decisions based on their own interests, when you write ፖለቲካ የሰፈር ጨዋታ ነው. This is what I was saying when Jawahr Mohammed and Prof. Merera were touring the country and rallying people in their hundreds of thousands, if not in millions behind them. That was misleading, in my view. At the end of the day we all don't live from pure rhetoric, we have interest that practically affect our lives, like food, shelter, clothing, security, justice and etc are our priorities.

You may not be able to deliver all these as a single party or a small group, but you can do some of it. For example you can invest in a community's basic needs as a group of few people. I will be glad to know what EZEMA did in this respect. If it didn't do, why did it fail?

There was a short clip recently that I came across and there was an BaldiRas party cadre complaining about election rules. He said an elderly woman came in the election station and started to ask where Abiy is, the election officers replied saying it is not Abiy that you will see here, it is the electic bulb that represents him. I was loughing at the party cadre and his complains. It should be devastating for him, in my view.


I have been raising on this forum on multiple cases that why many people who are claiming to care about their country don't show their caring by investing in the community of their choice? Here it is the consequences of that failure that you said here.

Look at how someone, an elderly woman, who probably don't understand about politics much, make her choice, a lesson needs to be drawn here.

Either you earn it or you will be thrown away by the people on whose shoulder you are seeking to get to power. People are wise and make decisions rationally.

Look at what the PM is doing and guess why the elderly woman asked to show her where he is.This election is also a big stride for the whole of Ethiopian politics. You either earn it or there will be nothing that will be given to you as a gift.

Post Reply