Blog Archives

በጣና በለስ ፕሮጀክት በተቀሰቀሰ ግጭት ሶስት ሰዎች ሞተዋል ፣ የተባለው ወሬ ውሸት ነው ተባለ።

የስኳር ኮርፖሬሽን ፣ በጣና በለስ ፕሮጀክት በተቀሰቀሰ ግጭት ሶስት ሰዎች ሞተዋል ፣ የተባለው ወሬ ውሸት መሆኑን ዕወቁልኝ አለ፡፡ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ በነበሩት የአቶ ስመኘው በቀለ ፣ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በተፈፀመበት ቀን መብራት በመጥፋቱ በፈንደቃ ከተማ ግጭት ተቀስቅሶ ነበር፡፡ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ፣ ጃዊ ወረዳ ፣ ፈንደቃ ከተማ ፣ በቀብሩ እለት መብራት የጠፋው ሆን ተብሎ ነው በሚል መነሻ በተቀሰቀሰው ረብሻ 3 ሰዎች መሞታቸው የስኳር ኮርፖሬሽን ይናገራል፡፡ ይሁንና ፣ግጭቱ የተነሳውና የሞቱትም ሰዎች የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ናቸው ተብሎ መነገሩ ሀሰት ነው ብሏል፡፡ ግጭቱ የተነሳበት ፈንደቃ ከተማ ከፕሮጀክቱ በሶስት ኪሎ ሜትር ርቀት የምትገኝና የሞቱትም የፕሮጀክቱ ሰራተኞች አለመሆናቸውን የተናገረው ስኳር ኮርፖሬሽን ሰራተኞቼ ፣ ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የመጡና ተቻችለው ተዋደውና ተከባብረው የሚኖሩ ናቸው ብሏል፡፡ Sheger fm
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News