Blog Archives

ቅዳሜ፣ ሰኔ 16/2010 በአዲስ አበባ አብዮት አደባባይ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን የለውጥ እርምጃዎች ለመደገፍ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች የተሰጠ መግለጫ

ቅዳሜ፣ ሰኔ 16/2010 በአዲስ አበባ አብዮት አደባባይ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን የለውጥ እርምጃዎች ለመደገፍ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች የተሰጠ መግለጫ ሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት 27 አመታት በጥቂቶች የጭቆና አገዛዝ ስር ወድቃ ዜጎቿ ለሞት፣ ለእስር፣ ለአካል ጉዳት፣ ለቶርቸር፣ ለስደት፣ የሀገራችን ሀብት እና ማዕድናት ተዘርፎ ለጥቂቶች የተንደላቀቀ ኑሮ እና ምቾት እየዋለ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነዉ። በአጠቃላይ የሀገራችን ህዝቦች በገዛ ሀገራቸዉ ተንቀዉ እና ተዋርደዉ ለመከራ ኑሮ የተዳረጉበት፣ የሀገራችን ወጣቶች በሀገራቸዉ ተስፋ አጥተዉ ለስደት የተዳረጉበትና በየበረሃዉ በዉሃ ጥም እና በረሀብ እየረገፉ፣ በባህር የዓሳ እራት እየሆኑ እንደሆነ ይታወቃል። የሀገራችን ህዝቦች በተለይም ወጣቱ አንድም ቀን ለዚህ ለዉርደት ለዳረጋቸዉ የጥቂቶች የጭቆና አገዛዝ ተንበርክከዉ አያዉቁም። በኦሮሚያ የቄሮ፣ በአማራ የፋኖ፣በጉራጌ ዘርማ በሌሎች የሀገራችን አከባቢዎችም ወጣቶች በተደራጀ እና በተበታተነ መልኩ ገዢዎችን እየተፋለሙ ዉድ ህይወታችዉን እና አካላቸዉን ገብረዋል። ትኩስ የወጣትነት ዕድሜያችዉንም በማዕከላዊ፣ በቃሊቲ፣ በቂሊንጦ፣ በከርቸሌ እና ሌሎች ማጎሪያ ካምፖች ዉስጥ ለማሳለፍ ተገደዋል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ወጣቶች መስዋዕትነት እና የደም ፅዋ ሞልቶ መፍሰስ ጀምራል። በሀገራችን ወጣቶች ትግል የህዝብ ልጆች የሆኑ፣ ህዝብ ህዝብ የሚሸቱ፣ የህዝቡ ስቃይ የሚያማቸዉ አመራሮች ወደ ፊት በመዉጣት ትላልቅ እርምጃዎችን መዉሰድ ጅምረዋል። በዶ/ር አቢይ አህመድ የሚመራዉ አዲሱ መንግስት በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞችን ነፃ አዉጥቷል። በተለያዩ ሀገራት ተሰድዉ በእስር የሚሰቃዩ ኢትዮጵያዉያንን አስፈትተትዋል። ሲደረጉ የነብሩ ዝርፊያዎችን በማስቆም ላይ ይገኛል። አይነኬ የማይመስሉ የገዢዉ መደብ ደም መጣጭ ፈርኦኖች ከስልጣን በማሰናበት ተስፋ የሚሰጥ የለዉጥ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News