Blog Archives

በሶማሌ ክልል ጥቅማቸው የቀርባቸው የአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች በተለይም ካቢኔው በህዝቡ ላይ ሽብር እየነዙ ነው።

ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አሳሳቢ መረጃ (ዮናታን ተስፋዬ) በአሁኑ ሰዓት መከላከያ አንፃራዊ ሰላም እንዲሰፍን ከሀገር ሽማግሌዎች እና ተቆርቋሪ ዜጓች ጋር እየሰራ ቢሆንም – ጥቅማቸው የቀርባቸው የአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች በተለይም ካቢኔው በህዝቡ ላይ (መጤ ወይም ደገኛ በተባለው ህዝብ ላይ) ሽብር እየነዙ ነው። በሶማሊኛ ቋንቋ የሚተላለፈው ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ እስካሁን በአብዲ ኢሌ ካቢኔ እና ዘመዶች ቁጥጥር ውስጥ በመሆኑ በህዝብ ላይ ከፍተኛ የሽብር ፕሮፖጋንዳ ከፍተው እያወኩ ነው። ከዚሀም የተነሳ ከ10 ሺህ በላይ ‘ደገኞች’ ክልሉን ለቀው በመውጣት ላይ ሲሆኑ – በአንዳንድ ቦታ በቴሌቪዥን ጣቢያው በሚተላለፈው ፕሮፖጋንዳ የተነሳ የተደራጀ ማፈናቀል እየተካሄደ ነው። የሀገር ሽማግሌዎች የፌደራል መንግስት ሚዲያውን በቁጥጥሩ ስር አውሎ ኃላፊነት በሚሰማው ሰው እንዲሰራ ጥሪ እያቀረቡ ነው።
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News