Blog Archives

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችውን ሶፍያ የተባለችውን ሮቦት አነጋገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችውን ሶፍያ የተባለችውን ሮቦት አነጋገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሶፍያን እውን በማድረግ ሂደት ጉልህ ድርሻ በነበራቸው ኢትዮጵያዊያን ተመራማሪዎች ስራ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡ በዓለም ላይ ከተሰሩ ሰው መሰል ሮቦቶች ሶፍያ የሰው እሳቤ የበለጠ የተንፀባረቀባት የፈጠራ ሮቦት ነች፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሶፊያ ጋር በነበራቸው ቆይታ አሁን በአለም ላይ ቦታ እየያዘ በመጣው በሰው ሰራሽ ክህሎት (artificial intellegience) ዘርፍ ኢትዮጵያ የነቃ ተሳትፎ ልታደርግ ይገባል ብለዋል፡፡ በዚህም ወጣቶችን በማሳተፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ሊሰራ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ እንደከዚህ ቀደሙ የቴክኖሎጂው ተቀባይ ሳንሆን እኩል ባለድርሻ መሆንም ይገባልም ብለዋል፡፡ አይኮግላብ በተባለው ኢትዮጵያዊ ኩባንያ ስር የተሰባሰቡ ተመራማሪዎች ከግማሽ በላይ በሚሆነው የሮቦቷ የሶፍት ዌር ብልፀጋ ላይ ተሳትፎ ነበራቸው፡፡እነዚሁ ተመራማሪዎች በአዲስ አበባ ሚሊኒዮም አዳራሽ በተከፈተው 2ኛው አለም አቀፍ የአይሲቲ ኤክስፖ ላይም “በኢትዮጵያ የተነደፈ” በሚል ምርጥ ስራቸው በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እውቅና ተሰጥቶታል፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News