Blog Archives

በአማራ ክልል በሰቆጣና በላሊበላ ሻደይ፣አሸንድየ ፣ በትግራይ ክልል አሸንዳ በዓል በድምቀት በመከበር ላይ ነው

በየአመቱ ከነሀሴ 14 ጀምሮ ለሶስት ቀናት  በአማራ ክልል በሰቆጣና በላሊበላ ሻደይ፣አሸንድየ በትግራይ ክልል አሸንዳ፣ በዓል በድምቀት በመከበር ላይ ነው።በዓሉ ልጃገረዶች/ ሴቶች በተለያዩ ባህላዊ አልባሳትና ጌጣ ጌጦች ተውበው ሹሩባ ተሰርተው በነጻነት የሚጨፍሩበት፣ የመሰላቸውን ሀሳብ በዜማቸው የሚገልጹበት ታላቅ ዕለት ነው። የበዓሉ ባለቤቶች ሴቶች በተለይም ወጣት ሴቶች ናቸው። የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በዓሉን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት በአሉ የሴት ልጆች በተለይም ወጣት ሴቶች አንገታቸውን አቀርቅረው በሚሄዱበትና በአደባባይ ወጥተው ፍላጎታቸውን በማይገልጹበት ወቅት ሁሉ በሙሉ ነጻነት ይልቁንም በጋራና በአደባባይ የወደዱትን የሚያሞጉሱበት፣ የጠሉትን ሃሳብና ተግባር በነጻነት የሚያወግዙበት ድንቅ በአል ነው ብለዋል። አሸንዳ/ ሻደይ የሴቶች ውበት፣ ክብር እና ነጻነት ማሳያ ብቻ ሳይሆን ነጻነት ራሷ ነጻ የምትወጣበትና በአደባበይም ስጋ ለብሳ የምትታይበት ታላቅ ቀን ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ። ጠቅላይ ሚንስትሩ በመልእክታቸው የሰሜኑ ክፍል የሀገራችን ህዝቦች ከሚያለያዩዋቸው ይልቅ አንድ የሚያደረጉዋቸው እንደሚበዙ ብዙ ከማስረዳት ይልቅ የአሸንዳን አንድ ሰበዝ በፍቅር ማሳየት ሁሉን ነገር ይገልጸዋል ብለዋል። ይህን አስደሳችና አስዳናቂ ባህል፣ የሰሜን የሀገራችን ህዝቦች ብቻ ሳይሆን የመላ ኢትዮጵያ ህዝቦች፤ የኢትየዮጵያውያንም ብቻ ሳይሆን የአለም ሀብትና ቅርስ መሆን እንዲችል በአለም በማይዳሰስ ሀብትነት እንዲመዘገብ አጥብቀን መስራት ይኖርብናልም ብለዋል። ልጃገረዶች/ሴቶች ከዋዜማው እስከ ማግሥት ልጃገረዶች የአሸንዳ ቅጠልን አሸርጠው አደባባይ በመውጣትና በየቤቱ በመዞር እየጨፈሩና እያዜሙ  የሚያከብሩት በዓል  ስያሜው  በክረምት ወቅት ከሚበቅለው የአሸንዳ ተክል እንደተወሰደም ይነገራል። በዓሉን ለመዘገብ በርካታ የአገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙሀን ወደ የአከባቢዎቹ ተሰማርተዋል።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶክተር አቢይ አሕመድ አሸንዳ/ ሻደይ/ አሸንድየ በዓልን በማስመልከት የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አሕመድ አሸንዳ/ ሻደይ/ አሸንድየ በዓልን በማስመልከት የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል። የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት የላከው የመልካም ምኞት መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል። አሸንዳ/ ሻደይ/ አሸንድየ የሰሜን ኢትዮጵያ ህዝቦች የአንድነትና የወንድማማችነት ህያው ማስረጃ! በሁሉም አቅጣጫ ያሉትን የሀገራችንን ህዝቦች እንዳይበታተኑ ያስተሳሰሩ፤ እንዳይለያዩ ያጣመሩ፣ እንዳይፈርሱ ያማገሩ በርካታና ጠንካራ ማጎች በሀገራችን ሁሉም ጫፎች በክብር እና በፍቅር እዚም እዚያም አሉ። ህዝቦቻችን በጋብቻ ተዛምደው፣ በማንነት ተዋህደው የኖሩ፣ ያሉና የሚኖሩ ህዝቦች ናቸው። ልክ እንደ ምስራቁ፣ ደቡቡና ምእራቡ ህዝባችን ሁሉ የሰሜን የሃገራቸን ህዝቦችም በባህል፣ በቋንቋ፣ በዘር፣ በሃይማኖት ወዘተ ተሰናስልው፤ ተዋደውና ተዋህደው የኖሩ፣ ያሉና የሚኖሩ ስለመሆናቸው በርካታ የታሪክ፣ የባህል፤ የእምነት እና የቋንቋ ማስረጃዎች ማቅረብ የሚያስፈልገው ሁነት ሳይሆን በህይወታቸው ውስጥ ከተረበረቡ እልፍመገለጫዎቻቸው የሚስተዋል ግሩም እውነት ነው። የዚህ አንድነትና የጋራ ማንነት- የዚህ ዘመንን እንኳ የሚያስገብር ከነፍስ የተሸመነ እውነት ማሳያ ከሆኑ የማህበረሰባችን እሴት ባህሎች ውስጥ ደግሞ በትግራይ እና በአማራ ክልሎች የሚኖሩ የትግራይ፣ የአማራ፣ የአገው፣ የኩናማ እና የኢሮብ ህዝቦች መመሳሰልና መተሳሳርን የሚያሳየው የአሸንዳ/ ሻደይ ክብረ በአል አንዱና ምናልባትም ዋነኛው ነው። የዚህን በአል አከባበር ለሚመለከት የውጭ ታዛቢ የሰሜን ህዝቦቻችን በሁሉም መለክያ አንድ ህዝብ እንጂ ሁለት ወይም ሶስት ሆነው ሊታዩት እንደማይችሉ እሙን ነው። የሰሜኑ ክፍል የሀገራችን ህዝቦች ልክ እንደ ደቡብ፣ ምስራቅ፣ ምእራቦቹ ህዝቦቻችን ከሚያለያዩዋቸው ይልቅ አንድ የሚያደረጉዋቸው እንደሚበዙ ብዙ ከማስረዳት ይልቅ የአሸንዳን አንድ ሰበዝ በፍቅር ማሳየት ሁሉን ነገር ይገልጸዋል። ስለ
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News