Blog Archives

ስለ ፓስተር ዳንኤል ዝም ማለት አልቻልኩም (ማሕሌት ፋንታሁን)

ስለ ፓስተር ዳንኤል ዝም ማለት አልቻልኩም (ማሕሌት ፋንታሁን) በ2006 ሃምሌ ወይም ነሃሴ ወር ላይ ቃሊቲ በእስር በነበርንበት ወቅት እኔና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬን መጥቶ አናግሮን ነበር። ማእከላዊ እያለን እኛን ለማግኘት በተደጋጋሚ ጠይቆ እንዳልፈቀዱለት በመጥቀስ ስለማእከላዊ እንዲሁም የቃሊቲ ሁኔታችን ጠየቀን። በማእከላዊ ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር እንድንገናኝ የተፈቀደልን ሶስት ወር ከቆየን እና ቃል ከሰጠን በኋላ መሆኑን፣ በምርመራ ወቅት መርማሪዎች እራቆታችንን እያስቆሙ እና ከባባድ እስፖርት እያሰሩ ያላደረግነውን ነገር እንድናምን እንደሚያስገድዱን፣ ዱላ፣ ዛቻ፣ ማስፈራራት እና ማመነጫጨቅ እንደነበረ በተጨማሪም ለ “ምርመራው” በአብዛኛው የምንጠራው ማታ እና ለሊት እንደነበረ ፤ ቃሊቲ ከገባን በኋላም ሌሎች በቀጠሮ ያሉ ሴት እስረኞች ሊጠይቃቸው የመጣ ቤተሰብ እና ጓደኛ ሁሉ ጠዋት እና ከሰአት በስራ ሰአት ባለ ጊዜ እንደሚጠየቁ እኛ ግን ልዩ አጃቢ ለየብቻችን ተመድቦልን ጥቂት ቤተሰቦቻችንን ብቻ በምሳ ሰዓት ባለ ጊዜ ለ15 እና 20 ደቂቃ ብቻ እንደምንገናኝ፤ ሌሎች እስረኞችም ከኛ በሽብር ከተከሰሱ ጋር እንዳያወሩ ጫና እንደሚደረግባቸው ነገርነው። ፓስተር ዳንኤል ከሰማን በኋላ ምንም አልመሰለውም። እንዲያውም “እናንተ በጣም ደህና ናችሁ። ጥሩ ሁኔታ ላይ ናችሁ። ” ብሎ ከኛ በፊት ታስራ የነበረች የፓለቲካ እስረኛን ጠቅሶ ሞራሏ በጣም ተጎድቶ እንደነበረ እና ለሷ ብዙ እገዛዎችን ማድረጉን ገለፀልን። እኛ ስለደረሰብን ነገር ሲጠይቀን ሳንደብቅ የነገርነው የሚፈይድልን ነገር አለ ብለን ተስፋ አድርገን ሳይሆን እውነቱን ይወቀው በሚል ነው። ምክንያቱም በኛ ላይ የደረሰው እና ይደርስ የነበረው የመብት ጥሰት ከኛ በፊት የታሰሩ እስረኞች ላይም ነበረ፤ ከኛ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News