Blog Archives

የሮማው ሊቃነጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ የኢትዮጵያንና የኤርትራን የሰላም ውይይት አደነቁ።

Pope Francis singles out ‘good news’ about Ethiopia Eritrea conflict የሮማው ሊቃነጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ የኢትዮጵያንና የኤርትራን የሰላም ውይይት አደነቁ። በዛሬው እለት በቫቲካን ከተማ አደባባይ ለተሰበሰበው ሕዝብ ባደረጉት ንግግር በተለይ ትኩረት ሰትተው ኢትዮጵያና ኤርትራ የጀመሩትን የሰላም ውይይት እንዳስደሰታቸው አጥብቀው ተናግረዋል። ጳጳሱ ለካቶሊክ አማኞች ባደረጉት ንግግር ከአፍሪካ ረዥም ጊዜ የቆየው ግጭት በሰላም መፈታቱ ታላቅ ድል መሆኑን አስምረውበታል። (ምንሊክ ሳልሳዊ)   የሁለቱ ሃገራት ከሃያ አመት በኋላ ለሰላም ውይይት መብቃታቸው ለምስራቅ አፍሪካ እንዲሁም ለአፍሪካ አሕጉር የተስፋ ብርሃን ያመጣ ነው ሲሉ አወድሰውታል። ኤርትራ ከቅኝገዢዬ ብላ ከሰየመቻት ኢትዮጵያ ነጻነቴ አገጨሁ ብላ ባወጀች አምስት አመት በኋላ የተጀመረው ግጭት እስከ ዛሬው ውይይት ድረስ መዝለቁን ያስታወሰው ዘገባው የኢትዮጵያን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርን ጠቅሶ እንዳለው የኢትዮጵያና የ ኤርትራ መሪዎች በቅርቡ እንደሚገናኙ ጠቅሷል ። (ምንሊክ ሳልሳዊ)   https://www.tampabay.com/pope-singles-out-good-news-about-ethiopia-eritrea-conflict-ap_world5ccffc3482ed44059f7b2fcc1eda4618
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News