አጉል ጀብደኝነት ዋጋ ያስከፍላል። (ምንሊክ ሳልሳዊ )
ከፊታችን የተደቀነውን ከባድ አደጋ ለማክሸፍ መንግስት ጥብቅ እርምጃ በመላው ኢትዮጵያ ሊወስድ ይገባል። አካባቢያችንን በቅጡ ካላየንና በሚገባ ካልመረመርን፣ እያሰብን ሳይሆን እየተኛን ነው፦ ከተኛን ደግሞ የተመኘነው ለውጥ አይመጣም፡፡ በሀገራችን የምንናገረውን የሚያዳምጥ፣ ያዳመጠውንም የሚያውጠነጥን ዜጋ ከሌለ የለውጥና የተሀድሶ ተስፋ ይጨልማል፡፡ ፍቅርን አንድነትን መደመርን ሰላምን ለማግጨት የሚደረጉ ጥረቶች ሁሉ በጥሩ መንገድ ተጉዘው ስኬትን ቢያስመዘግቡም አንዳንድ አከባቢዎች ላይ ግን ቅጣትን የሚሹ ልክ መግባት ያለባቸው ስርዓት አልበኞች ተፈጥረዋል።
መንግስት ጉልበት እንዲጠቀም የሚጋብዙ ሰዎች እኩይ ተልእኳቸውም ማቆም አለመቻላቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ባለፈው የሕወሃት አገዛዝ አግዓዚ ሕዝብን ሲገድል እያዩ አጠገባቸው ወገናቸው እየተገደለ እያዩ ካለፈው አሰቃቂ ሂደት መማር ያልቻሉ ሰዎች ለውጥ ለማምጣት የሚካሄደውን መልካም ጅማሮ ለማደናቀፍ ይሁን በእኛነት ጀብድ ከፍ ብሎ ለመታየት በሆነ መንገድ ማሰቢያቸውን አረመኔያዊ አድርገው የአደባባይ ሽብር እየፈጸሙ ይገኛሉ።
ካሁን ቀደም ሲደረጉ የነበሩ ተቃውሞዎችንም ሆነ ክፋቶች አሁን ላይ እንዲደገሙ በፍጹም አንፈልግም። ካሁን ቀደም ያደረግናቸው ከባርነት ነጻ ለመውጣት የሔድንባቸው መንገዶች ለነጻነት መንገድ ያበኩን በመሆኑ ነጻነታችንን በእጃችን አጥብቀን ለመያዝ አገርና ሕዝብ ላይ አደጋ ከመፍጠርና አደጋ የሚፈጥሩትን ከማበረታታት ልንቆጠብ ይገባል። የተለያዩ የትግል ስልቶችን እየቀያየሩ ከመተቀም ይልቅ ሽብርና ጥላቻን መዝራት አደጋው የከፋ ነው።
አጉል ጀብደኝነት ዋጋ ያስከፍላል። (ምንሊክ ሳልሳዊ ) መግደል መሸነፍ ነው ፤ መዝረፍ መሸነፍ ነው ፤ መንገኝነት መሸነፍ ነው ፤ ማፈናቀል መሸነፍ ነው። አንድነት ከሌለ መቻቻል ከሌለ ፣ ፍቅር ከሌለ ሰላም አይኖርም ፤