Blog Archives

የሕወሓት ሰዎች የጠ/ሚ አብይ አህመድ አመራር ላይ ያላቸውን ተቃዉሞ በሰላማዊ ሰልፍ ገለጹ – በሌብነት እጅ ከፍንጅ የተያዘ ሰው እንዲፈታ ጠይቀዋል።

ወያኔዎች ዘውትር በትግራይ ክልል ድጋፍ ሲዳከምባቸው የሀውዜንን ጭፍጨፋ ካርታ መሳብ ስራቸው ነው ።ግን እስከ መቼ ይቀልዳሉ የሚገርመው ዛሬም የሰማእታትንና የሀውዜንን ካርድ ጆከራን ስበው ማየት ያማል እስኪ ተመልከቱ ዛሬ መቀሌ ላይ የተካሄደው ሰላማዊ የድጋፍ ሰልፍ ወይስ የቀብር ስነስረዓት ? ሰላማዊ ሰልፍ ሲከለክሉ የነበሩት የትህነግ አመራሮች እንደዚህ አይነት ሰላማዊ ሰልፎች እንዲደረጉ ያመቻቸው የጠሚ አብይ አህመድ አመራር ላይ ያላቸውን ተቃዉሞ በሰላማዊ ሰልፍ ገለጹ። Vicious!!! ባንድ በኩል የቀድሞ ሰልፍ ከልካዮች በተከፈተው ሰልፍ የመውጣት እድል ተጠቃሚ በመሆን ልብ ሳይሉ ለዶ/ር አብይ አመራር እዉቅና ሲሰጡና ከዚህ ቀደም የገነቡት ስርኣት አፋኝ እንደነበር ራሳቸውን ሲያጋልጡ ዋሉ። TPLF በሌብነት እጅ ከፍንጅ የተያዘ ሰው እንዲፈታ ጠይቀዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሰልፍ ከልካይ የሆነውን የመለስን ፎቶ እዚህ ላይ በመያዝና እንዲ ያለ ሰልፍ የሚፈቅድን አመራር በተመሳሳይ ሰላማዊ ሰልፍ የመቃወም አዙርት ዉስጥ ሲዳክሩ ነበር፡፡ ሰላማዊ ሰልፍን በሰላማዊ ሰልፍ መቃወም ምን የሚሉት ዝቅጠት ነው። በሌብነት እጅ ከፍንጅ የተያዘ ሰው እንዲፈታ ጠይቀዋል። የኢንሳ ባለስልጣን የነበረውና በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የተከሰሰው ቢኒያም ተወልደ የተባለው የሕወሃት ሰው እንዲፈታ ጠይቀዋል። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በርካታዎች የሰልፉ አላማ ያልገባቸውና የተሰጣቸውም መፈክል ያላገናዘቡ ከመሆን ተጨማሪ ለዶክተር አብይ አሕመድ ድጋፍ ሰልፍ አለ የሚል ፕሮፓጋንዳ ከተማ ውስጥ ተሰራጭቶ እንደነበር ተጠቁሟል። በተጨማሪም ስልጣን ላይ እያሉ ሰልፍ ከተካሄደ ሰልፈኞች ይገደሉ ይደበደቡና ይታሰሩ የነበረ ሲሆን በዛሬው የመቀሌ ሰልፍ ላይ ግን ዲሞክራሲያዊ መብታቸው ተጠብቆ ሀሳባቸውን ገልጸው ወደ ቤታቸው ገብተዋል። በመሆኑም
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የመቐለው ሰልፍና የደብረጺሆን ድንፋታ የቀን ጅቦች ጩኸት

የመቐለው ሰልፍና የደብረጺሆን ድንፋታ የቀን ጅቦች ጩኸት ምንሊክ ሳልሳዊ ፡ ዛሬ መቐለ ላይ በተደረገው ሰልፍ ላይ ደብረጺሆን የሚባል ጉቶ አፍ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያስፈራራልኛል ብሎ ያሰበውን ድንፋታ ሲናገር ነበር። ሃያ ሰባት አመት የኢትዮጵያ ሕዝብ በጨዋነት አክብሮ ዝም ብሏል። አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ትእግስቱ አልቋል። መገደል እና መዘረፍ ፤ መሰደድና መታሰር ሰልችቶታል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ያገኘው የነጻነት ተስፋ እንዳይቀለበስ ከሕወሃት ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቆ ለድል እንደሚበቃ ደብረጺሆን ሊያውቀው ይገባል።ተከባብሮ መኖርን የመሰለ ታላቅ ነገር የለም ። ገዳይ ተከብሮ ዘራፊ ተከብሮ ተገዳይና ተዘራፊ ተንቆ ዝም ብሎ ማለፍና መኖር እንዴት ይቻላል ይህ መመለስ ያለበት ጥያቄ ነው። መበታተን የሕወሓት ከመነሻዋ ጀምሮ ያለ አላማዋ ስለሆነ ምንም አይደንቅም። አዲስም ነገር የለውም። መጀመሪያ ስለመከባበር ሊያወራ የሚችለው ሰው መከባበርን የሚያውቅና ሕዝብን የሚያከብር እንጂ በሴሰኝነት ሃገር ሲዘርፍና ሲገድል የነበረ ሰው ስለመከባበር መናገር አይችልም። ስለመበታተን ደግሞ ለተባለው ሃያ ሰባት አመት በዘረጋቹት መዋቅራቹ የሕዝብን ሰላም ለጊዜው ልታደፈርሱ ትችላላቹህ እንጂ አገርን መበታተን አትችሉም። የሕወሓት ጅቦች በትግራይ ተደብቀው መግቢያ ቀዳዳ ስታጡ ዛቻና ማስፈራራት ብታደርጉም ማንም የማይፈራ መሆኑን አስረግጠን ለመናገር እንወዳለን። ሕወሓት አንድነትና ፍቅር አይዋጥለትም። ዲሞክራሲና ነጻነት ያመዋል። ይህ የታወቀ ሐቅ ነው። ሕገ መንግስት ይከበር የሚለው መፈክር የጻፈው ሕወሓት ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት የትኛውን ሕግ አክብሮ ያውቃል ፤ ሕገመንግስቱ እኮ ጥፍር ንቀሉ ፣ ብልት አኮላሹ ፣ ግደሉ ፣ ዝረፉ ወዘተ አይልም። መጀመሪያ ሕገመንግስቱን የራሳቸው የፓርቲ መርሃ ግብር ግልባጭ
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News