Blog Archives

በአዲስ አበባ በክፍለ ከተማ ደረጃ ያሉ ዋና ዋና አመራሮች በአዲስ መልክ ሊዋቀሩ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በክፍለ ከተማ ደረጃ ያሉ ዋና ዋና አመራሮች እንደአዲስ ሊያደራጅ ነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በክፍለ ከተማ ደረጃ ያሉ ዋና ዋና አመራሮች እንደአዲስ ሊያደራጅ መሆኑን አስታወቀ። የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በዚህ ሳምንት በክፍለ ከተማ ደረጃ ያሉ ዋና ዋና አመራሮች በአዲስ መልክ ይዋቀራሉ ብለዋል። በከተማ ደረጃ የተጀመረው የማሻሻያ ስራ እስከ ወረዳ እንደሚዘልቅ በተገለጸው መሰረት ከአዲስ አመት በፊት በወረዳ ደረጃ ያለው አመራር በአዲስ አደረጃጀት ተዋቅሮ እንደሚጠናቀቅም ገልፀዋል። የተጀመረውን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ እና አሁን እየታየ ያለውን ሀገራዊ ተስፋ ለማደናቀፍ እንዲሁም የከተማዋን ሰላም ለማደፍረስ እየታዩ ያሉ ምልክቶችን ህብረተሰቡ ከአስተዳደሩ ጎን በመቆም ድርጊቱን እንዲከላከልም ምክትል ከንቲባዋ ጠይቀዋል። ሰሞኑን በርካታ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ሲዘዋወር በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን ያስታውሱት ወ/ሮ ዳግማዊት፣ በቀጣይም ነዋሪው የሚያያቸውን አጠራጣሪ ነገሮች ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጠይቀዋል። ቤታቸውን የሚያከራዩ ነዋሪዎች የተከራዮችን ማንነት ሊያጣሩ እና ተገቢውን መረጃ ሊይዙ ይገባል ብለዋል። ምንጭ፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News