Blog Archives

የልጅ እያሱ እና የዶክተር አብይ እጣ (ጌታቸው ሺፈራው)

የልጅ እያሱ እና የዶክተር አብይ እጣ (ጌታቸው ሺፈራው) በኢትዮጵያ ታሪክ ያልተፃፈላቸው ብዙ መፈንቅለ መንግስቶች ተደርገዋል። የሁለት፣ ወይንም የሶስቱን ብቻ በታሪክ እናገኘዋለን። ~በቀዳሚነት ተፅፎ የምናገኘው የ1953 ዓም መፈንቅለ መንግስትን ነው። ይህ መፈንቅለ መንግስት ስርዓቱ ኮትኩቶ ባሳደጋቸው፣ ለንጉሱ ሰግደው፣ የንጉሱን ትዕዛዝ የቅዱስ መፅሐፍ ቃል ያህል ሲያከብሩ የኖሩ የሞከሩት ነው። በዚህ ስርዓት ውስጥ ያደጉት መኮንኖች የሕዝብ ብሶት፣ የስርዓቱ ድክመቶችና ሌሎች ለውጦችን ሲገነዘቡ ያደርጉታል ተብለው የማይታሰበውን አድርገውታል። ~ሌላኛው በታሪክ ውስጥ የተሻለ ሰነዶች ያሉት የ1981 ዓም መፈንቅለ መንግስት ነው። በ1953 ዓም ቃላቸው የመፅሐፍ ቃል አድርገው የሚወስዱት፣ “ጃንሆን” እያሉ መንበራቸው ላይ እንደተነሱት ሁሉ፣ በአንድ ወቅት ኮ/ል መንግስቱን በማርክሲስም ሽፋን ንጉስ አድርገው ይቆጥሩ የነበሩ፣ ከጓድ መንግስቱ አመራር ሲሉ የነበሩ መኮንኖች የፈፀሙት ነው። ልዩነቱ በአጤው ዘመን መለኮታዊ፣ በደርግ ወቅት ርዮትዓለማዊ መሆኑ እንጅ ሁለቱን መሪዎች መኮንኖቹ ለማምለክ ደርሰዋል። ~ሶስተኛና በክስ ደረጃ ተፅፎ የሚገኘው በ2000 ዓም ተደረገ የተባለው ሲሆን ይህን ሙከራ አደረጉ የተባሉትም ከሁለቱ ስርዓቶች የሚለዩበት አውዶች ቢኖሩም፣ በስርዓቱ ያደጉ “ታጋዮች” አደረጉት የተባለው ነው። የዚህኛው ልዩነት ማንነት ላይ ያነጣጠረ፣ መገፋቱን በዚሁ ማንነት ላይ የመጣ መሆኑ ነው። ~ብዙውን ጊዜ የማይወራለት ልጅ እያሱ ላይ የሆነው ነው። ልጅ እያሱ በወቅቱ በነበረው ፖለቲካ ሕጋዊ ማዕቀፍ የነበረው ቢሆንም አቅም የነበራቸው አካላት ግን ከጎኑ አልነበሩም። ከልጅ እያሱ ይልቅ ለተፈሪ መኮንን ቅርበት የነበራቸው አካላት የልጅ እያሱን በአጤ ምኒልክ የተሰጠ ንግስና (በወቅቱ ሕጋዊ፣ ወይንም ምክንያታዊ) በሀይላቸው ወደ ተፈሪ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“አባቴን ንጉሥ ሳላሰኝ ፈረሴን ከቀይ ባህር ዉሃ ሳላጠጣ ንጉሠ ነገሥት ተብዬ ዘዉድ አልጭንም”

(ምስጋናዉ ታደሰ) የዛሬዉ ጽሁፌ ከመቶ ዓመት በፊት በግንቦት ወር 1906 ዓ.ም የተፈጸመ አንድ ታሪካዊ ክስተት ያስቃኘናል፡፡ በ1901 ዓ.ም አፄ ምኒልክ በጠና በመታመማቸው ምክንያት የመንግሥቱን ሥራ በሚገባ ለመከወን ባለመቻላቸው ሥልጣናቸውን ለወራሻቸው ለማስተላለፍ ወሰኑ፡፡ ወንድ ልጅ ስላልነበራቸው ከልጃቸው ከሸዋረጋ ምኒልክና ከወሎዉ ራስ ሚካኤል የተወለደው የ13 ዓመቱ የልጅ ልጃቸውን ልጅ ኢያሱን አልጋ ወራሽ ማድረጋቸውን ግንቦት 10 ቀን 1901 ዓ.ም በአዋጅ ለሕዝብ አስታወቁ፡፡ በዚያው ቀን የኢትዩጵያ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ የዳግማዊ ምኒልክን ቃል የማይቀበሉትን ሰዎች ሁሉ አወገዙ፤ ረገሙ፡፡ የሚቀበሉትን ግን ባረኩ፣ መረቁ፡፡ በ1906 ዓ.ም አፄ ምኒልክ ማረፋቸዉን ተከትሎ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት መሣፍንትና መኳንንቱ ወደ ልጅ ኢያሱ ቀርበው ንጉሠ ነገሥት ተብለው በአያታቸው ዙፋን እንዲቀመጡ ጠየቋቸው፡፡ ልጅ ኢያሱም “አባቴን ንጉሥ ሳላሰኝ ፈረሴን ከቀይ ባሕር ውሃ ሳላጠጣ ዘውድ ጭኜ ንጉሠ ነገሥት አልባልም” በማለት መለሱላቸዉ፡፡ (ፈረሴን ከቀይ ባህር ዉሃ ሳላጠጣ የሚለዉ አነጋገር የኢትዮጵያ ተፈጥሮአዊ ድንበር የሆነዉን ቀይ ባህርን ሳላስመልስ፣ ለሀገሬ ወደብ ሳላመጣ የሚል አንድምታ ያለዉ ነዉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ልጅ ኢያሱ ኤርትራን ከጣልያን ለማስመለስና ቀይ ባህርን የኢትዮጵያ አካል ለማድረግ ያደረጉትን ጥረት በሌላ ጽሁፍ የምንመለከተዉ ይሆናል፡፡) በዚህ መሰረት ልጅ ኢያሱ ንጉሠ ነገሥት ከመሆናቸው በፊት አባታቸውን ንጉሥ ለማሠኘት ወሠኑ፡፡ እንደዜና መዋዕል ፀሐፊያቸው እንደ ኤልያስ ገብረ እግዚአብሔር ገለፃ ልጅ ኢያሱ ይህን ያሰቡበት ምክንያት የስልጣን መሰረታቸውን ለማጠናከር ነው፡፡ በእናታቸው የንጉሠ ነገሥት ልጅ የሆኑት ልጅ ኢያሱ አባታቸውን ንጉሥ በማሰኘት የሁለት ነገሥታት ልጅ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News
Follow us on Facebook
Follow us on Facebook