Blog Archives

የጃዊ ፈንደቃ ነዋሪዎችና የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ፍጥጫ ላይ ናቸው።

የአማራ ክልል መንግስት ምን እየሰራ ነዉ? ጃዊ ላይ ተከስቶ በነበረዉ ግርግር የሰዉ ሂወት ማለፉ ይታወቃል፡፡ በዚህ ሁኔታም እጅግ ብዙ ግለሰቦች በጥርጣሬ ለእስር ተዳርገዋል፡፡ አሁን ደግሞ በቀኑ የነበሩ የፖሊስ አመራርና ተረኛ ፖሊሶችን የፌደራል መንግስት ትዕዛዝ ነዉ፤ ፌደራል መንግስቱ ይፈልጋቸዋል በማለት የአማራ ክልል መንግስት ዛሬ ፖሊሶቹን አሳልፎ ለመስጠት ጥረት እያደረገ ነዉ፡፡ የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድሩ ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል ቦታዉ ድረስ አጣሪ ልከን ሁኔታዉን እናጣራለን ማለቱን እናስታዉሳለን፡፡ በዚህ የአማራ ክልል መንግስት ዉሳኔ የተበሳጨዉ አጠቃላይ የወረዳዉ ፀጥታ አካልና ህዝቡ አሁን ላይ ግልብጥ ብሎ በመዉጣት እነዚህን ግለሰቦች አሳልፈን አንሰጥም በማለት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ የትግራይ ክልል ህዝብን ያስገደሉ ወንጀለኞችና ሀገርን የዘረፉ ሌቦችን አሳልፎ አልሰጥም ይላል፤ የአማራ ክልል መንግስት ደግሞ የፌደራል መንግስት ትዕዛዝ ነዉ በማለት በግርግር የጠፋ የሶስት ሰዉ ሂወት አለና ፌደራል መንግስቱ ይፈልጋችኋል በማለት ልጆቹን አሳልፎ ለመስጠት ይሽለጠለጣል፡፡ ነገ ደግሞ በጥርጣሬ የተያዙትን ግለሰቦች አሳልፌ ልስጥ ይላል፡፡ ተጠርጣሪዎች ማስረጃ ተሰብስቦባቸዉ ጥፋተኛ ሆነዉ ከተገኙ በያሉበት ህጉን ተከትሎ ቅጣት መስጠትና ፍትህ ማስፈን አይቻልም። እነዚህ ግለሰቦች በህግ ማስከበር ስም እዉነት ተላልፈዉ ቢሰጡ የትና እንዴት ነዉ የሚሄዱት? ፌደራል መንግስትስ ሁኔታዉ ተጣርቶ በያሉበት ፍትህ መስጠት አይቻልም ብሎ ለምን ያምናል? በፌደራል መንግስት ስም ወንጀል ሰርተዉ ትግራይ የተደበቁት ዝም እየተባሉ ተጠርጣሪን የወረዳ ሰዉ አሳልፌ ልዉሰድ ማለት ምን ማለት ነዉ? ብአዴን ግን ምን ይሻለዋል? መቸ ነዉ ጀገን ማለት የሚጀምረዉ?
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጃዊ ወረዳ -ፈንድቃ ከተማ በዜጎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

በጃዊ ወረዳ -ፈንድቃ ከተማ በዜጎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ ሀምሌ 24/2010 በአማራ ክልል በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳ -ፈንድቃ ከተማ በዜጎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን አስታወቁ። ኃላፊው እንደገለፁት በጣና በለስ የስኳር ፕሮጀክት ይሰሩ በነበሩ ዜጎች ህይወት ላይ ትላንት ጉዳት አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው ተጀምሯል።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News