Blog Archives

የኦነጎችና የኒዮ ኦነጎች አላማ ኦሮምያ የሚባል ሃገር ወይም ኦሮማይዝድ የሆነች ኢትዮጵያ መመስረት ነው (ሔኖክ አበበ)

ማነው እየቃዠ ያለው? ጀዋር መሃመድ ወይስ እኛ? (ሔኖክ አበበ) _____________ አንድ ቃለመጠይቅ ላይ ጀዋር ስላቅና እብሪት በተቀላቀለበት ሁኔታ እንዲህ አለ “…ይቃዣሉ እንዴ….ብፈልግ ኑሮ ኦሮምያን የዛሬ አራት ወር እገነጥላት ነበር…..አዲስ አበባን በቀለበት ውስጥ አስገብተን በ24 ሰዓት ውስጥ መቆጣጠር እንችል ነበር….” የኦነጎችና የኒዮ ኦነጎች አላማ ኦሮምያ የሚባል ሃገር መመስረት ነው:: ኒዮ ኦነጎች (እነጀዋር: ህዝቅኤል: ፀጋየ…) አላማቸው ኦሮምያ የሚባል ሃገር መመስረት ወይም ኦሮማይዝድ የሆነች (በሁሉም ነገር የኦሮሞ የበላይነት ያለባት) ኢትዮጵያ ከተቻለ የሃገሪቱ ስምም ኦሮምያ ተብሎ አዲስ ስም ያላት ሃገር መመስረት ነው:: ኦሮምያ ክልልን ወይም ኦነግ የሚያልመውን ታላቋን ኦሮምያ መመስረት እንደማይችሉ ሲገባቸው የኦሮሞ የበላይነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን እንገነባለን ብለው እንቅስቃሴ ውስጥ ናቸው:: ኢትዮጵያን መግዛት እየቻልን ለምን Secured ወደአልሆነ የሃገር ግንባታ እንሄዳለን በማለት:: ህወሃት ትግራይን ልገንጥል ብሎ እንደገና በትግሬ የበላይነት የተቃኘች ኢትዮጵያን መግዛት አዋጪ ነው ብሎ ሃሳቡን እንደቀየረው ማለት ነው:: እናም ኒዮ ኦነጎች ሃሳባቸውን የቀየሩ አሁን ያለውን ኦሮምያ ክልልም ሆነ በኦነግ የሚታሰበውን ታላቋን ኦሮምያ መገንጠል//መመስረት practical ስላልሆነ: ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ጦርነት ውስጥ የሚከት ስለሆነ: ሁሉም የኦሮሞ ህዝብ የራስን ሃገር መመስረትን አይደግፍም ብለው ስላሰቡ: ኦሮምያ ክልል ውስጥ ኦሮሞ ያልሆነ ሰፊ ህዝብ ስላለ: የአዲስ አበባ ሁኔታ ስላለ: አለም አቀፉ ማህበረሰብም (በተለይም አሜሪካና የአውሮፖ ህብረት) ሃሳባቸውን ስለማይደግፉት ያለፈችውንም: ያሁኗንም የወደፊቷንም ኢትዮጵያ በኦሮሞ ትርክት ቀንብበበን በኦሮሞ የበላይነት መግዛት ይሻለናል በሚል አሁን የያዙት መንገድ ላይ ይገኛሉ:: ስለዚህ ኦሮምያን መገንጠል ለሃገር
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News