Blog Archives

የቀን ጅቦችና አክቲቭስት ነን ባይ ፈልፈላ ጅቦች የትግራይ ሕዝብ ጠላቶች ናቸው።

የቀን ጅቦችና አክቲቭስት ነን ባይ ፈልፈላ ጅቦች የትግራይ ሕዝብ ጠላቶች ናቸው። ( Hyena Government ) የቀን ጅብ የተባሉት የሕወሓትኢሕአዴግ አመራሮችና የዘረጉት የሌብነት ኔትወርክ ሰዎቻቸው እንጂ ሕዝብ አይደለም። ኢሕአዴግ ውስጥ በርካታ የቀን ጅቦች ሞልተዋል። የትግራይ አክቲቭስቶች አብዛኛዎቹ ሕወሓት ቀለብ የሚሰፍርላቸው ተጠቃሚዎች ናቸው በሌላ አባባል ትንንሽ ሌቦች ፈልፈላ ጅቦች ናቸው። ሃገርንና ሕዝብን ሙልጭ አድርገው የዘረፉ ቡድኖች ናቸው የቀን ጅቦች ስለዚህ ሕዝብን አይወክሉም። ትልልቆቹ ሌቦች ወይም የቀን ጅቦች ያሰማሯቸው ፈልፈላ ጅቦች ናቸው። በተደጋጋሚ አንድ ጉዳይ በተነሳ ሰዓት ሁሉ ወደ ዘረኝነት የሚወስዱትና ይህንን ይዘው በምስኪኑ የትግራይ ሕዝብ ጉያ ለመወሸቅ የሚፈልጉ የትግራይ አክቲቭስቶች ከማንም በላይ የትግራይ ሕዝብ ጠላቶች ናቸው። የትግራይ ሕዝብ በማንነቱ የማይደራደር ታላቅ ሕዝብ ነው። በጉያው እየሮጡ የሚወሸቁትን የቀን ጅቦችና አክቲቭስት ነን ባይ ፈልፈላ ጅቦች ሊዋጋቸው ይገባል። የቀን ጅብ ሲባል ሕወሃት ብቻ ሳይሆን አሽከሮቹንም ያመለክታል። ኢሕአዴግ ውስጥ በርካታ የቀን ጅቦች ሞልተዋል። ይህ እየታወቀ የቀን ጅብ የሚሏትን ነገር ጎትቶ ለዘር መቧደኛ መጠቀም አደጋው የከፋ ነው። ማንኛውንም ነገር ከመጠምዘዝና ከመሰንጠቅ በፊት ደጋግሞ ማሰብ ያስፈልጋል። የትግራይ አክቲቭስት ነን የሚሉ ሕዝብን አይወክሉም የሕወሃት ፈልፈላ ጅቦች ንቃተ ሕሊናቸው በዘረኝነት ተደፍኗል። ምንሊክ ሳልሳዊ #MinilikSalsawi
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News