Blog Archives

የጎንደር ወጣቶች በከተማው ባለስልጣናት ላይ ተቃውሟቸውን አሰሙ።

ጎንደር ቀበሌ 18 አበራ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ግቢ የሚገኝ የዲያቆናት መኖርያዎች መቃጠላቸውን ምንጮች ገልፀዋል። ህዝብ የመንግስት አካል እንዲደርስ ጥረት ቢያደርግን የእሳት አደጋም ሆነ ሌሎች የመንግስት አካላት/ተቋማት ሊደርሱ አልቻሉም። የመንግስት አካል ሊደርስ ባለመቻሉ ሕዝብ እሳቱን ተረባርቦ አጥፍቷል። የከተማው ወጣቶች የመንግስት አካላት እሳቱን ለማጥፋት ጥረት አለማድረጋቸውን በመቃወም ጩኸት ሲያሰሙ እንደነበር ተገልፆአል። ወጣቶች “ለኃይማኖታችን ይፈሳል ደማችን” የሚል መፈክር እያሰሙ ወደ ፒያሳ ሲሄዱ ኮሌጅ አካባቢ ልዩ ኃይል እንዲመለሱ አድርጓል ተብሏል። በቃጠሎው ወቅት የመንግስት አካል እንዲደርስ ማንቂያ ይሆን ዘንድ ሕዝብ በርካታ ጥይት እንደተኮሰ ምንጮች ገልፀዋል።
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News