Blog Archives

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ የት ናቸው?

የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ የት ናቸው? የእስር ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል? የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ የእስር ማዘዣ እንደወጣባቸው እና ከአገር እንደሸሹ አንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን በስፋት ሲዘግቡት ሰንብተዋል። የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑትን ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚያብሔርን ስለጉዳዩ ጠይቀናቸዋል። ወ/ሮ ፈትለወርቅ ”እንደ ድርጅት በዚህ ደረጃ የምናውቀው ነገር የለም። ለድርጅት የክስ መጥሪያ አይመጣም” ይላሉ። በአንድ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ላይ ድርጅቱ ሳያውቀው ክስ ሊመሠረት ይችላል ወይ ተብለው የተጠየቁት የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፤ ”ውይይት የሚያስፈልገው ነገር ካለ ፖለቲካዊ ግምገማና ይደረጋል እንጂ ክስን በተመለከተ የመንግሥት ሥራ ነው የሚሆነው” ሲሉ መልሰዋል። ኾኖም የአቶ ጌታቸው ጉዳይ በግምገማም እንዳልተነሳ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ተናግረዋል። የኢህአዴግና የሕወሓት የሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው አሁን በተካሄደው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ እንዳልተገኙ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ጠቁመዋል። የአቶ ጌታቸው በስብሰባው ያለመገኘት ጉዳይ “የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸዋል ከሚለው ዜና ጋር የሚያያዝ ነው ወይ?” ተብለው የተጠየቁት ወይዘሮ ፈትለወርቅ ”አንድ ሰው ሰብሰባ ላይ በግል ጉዳይ ላይገኝ ይችላል። በስብሰባዎች ላይ ሁሉም ሰው ይገኛል ማለት አይደለም። የእሱ ከስብሰባ መቅረት ከዚህ ጋር ይገኛል ማለት ላይሆን ይችላል። በሥራ ጉዳይም ላይገኙ ይችላሉ” ይላሉ ወ/ሮ ፈትለወርቅ። ለመጨረሻ ጊዜ አቶ ጌታቸውን መቼ እንዳይዋቸው ከቢቢሲ የተጠየቁት ወይዘሮ ፈትለወርቅ በቅርቡ ከሁለት ሳምንት በፊት ገደማ መቀሌ እንዳገኟቸው አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል የፌዴራል አቃቢ ሕግ በአቶ
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News