Blog Archives

የሀጅና ዑምራ ጉዞ ዘረፋ መጅሊስና የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የሀጅ ጉዞ ዘረፋ መጅሊስና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዌብሳይት ጎራ አልኩና ስለ ሀጅ ጉዞ ወጪ ዝርዝር አየሁ፡፡ ባጠቃላይ 97,910 ብር ክፍያ እንደሚያስፈልገው ያሳያል፡፡ መጀመሪያ ላይ የተቀመጠው የአየር ቲኬት ነው፡፡ ዋጋውም 25,510 ብር ነው ይላል፡፡ ከሀጅ ውጭዎች ውስጥ ወደ ጅዳ ያለውን የትኬት ዋጋ ለማጣራት ሞባይሌን ከፍቼ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ዌብ ሳይት ማየት ጀመርኩ፡፡ የትኬት ዋጋ ሌላ ቀናት ጊዜ መርጬ ትኬት ስሞክር የጅዳ የአየር ትኬት ዋጋ እስከ 12,786 ብር ወርዶ አየሁ፡፡ በርግጥ የበረራ ዋጋ በየወቅቱ የሚዋወጥ ቢሆንም ለኢኮኖሚ ተጓዥ ይሄንን ያህል ያለው ልዩነት ፈፅሞ አግባብ ያለው ጭማሪ አይደለም፡፡ የተጠየቀው ዋጋ 100 ፐርሰንት ጭማሪ ያለው ግልፅ የዘረፋ ድርጊት ነው፡፡ ይህ ዘረፋ እየተደረገ ያለው በመጅሊስና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ትብብር ይመስላል፡፡ (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን እስካላስተባበለ ድረስ) ለ5ሰአት30ደቂቃ በረራ 25,510 ብር! ልዩነቱን ለማጉላት ጅዳ እጅጉን ወደሚርቁ ወደተለያዩ ከተሞች በጁላይ መጨረሻ/ኦገስት መጀመሪያ ከአዲስ አበባ ተነስቼ ኦገስት መጨረሻ ወደ አዲስ አበባ ብመለስ ብዬ የምጠየቀውን የትኬት ዋጋ ለንፅፅር ላቅርብ፡፡ ለንደን (እንግሊዝ) 24,522ብር – ደርሶ መልስ የሚፈጀው የበረራ ሰአት 15፡35) አቢጃን (ኮት ዴቮዋር) 22,599 ብር ደርሶ መልስ የሚፈጀው የበረራ ሰአት 12፡30) ቦንቤይ/ሙምባይ (ህንድ) 18,536 ብር ደርሶ መልስ የሚፈጀው የበረራ ሰአት 10:20) ባንኮክ (ታይላንድ) 17,202 ብር (ደርሶ መልስ የሚፈጀው የበረራ ሰአት 17፡50) ጆሃንስበርግ (ደቡብ አፍሪካ) 10,430 ብር ደርሶ መልስ የሚፈጀው የበረራ ሰአት 10:50) እንደመጅሊስ አባባል ከሆነ ደርሶ መልስ
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News