Blog Archives

የኢትዮጵያ የመብት ድርጅቶች ህብረት ምስረታ በዓል በደሳለኝ ሆቴል እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ የመብት ድርጅቶች ህብረት ምስረታ በዓል በደሳለኝ ሆቴል እየተካሄደ ነው። መስራች ድርጅቶቹ ⏩ሂውማን ራይት ካውንስል (HRCo) ⏩ቪዥን ኢትዮጵያ ኮንግረስ ፎር ዲሞክራሲ (VECOD) ⏩አድቮኬትስ ኢትዮጵያ (AE) ⏩ዴቨሎፕመንታል ጀስቲስ ናሽናል አሶሴሽን (DJNA) እና ⏩ሳራ ጀስቲስ ፈሮም ኦል ውማን አሶሴሽን ናቸው። ህብረቱ የሚያተኩርባቸው እንቅስቃሴዎች 👉በስሩ ያሉ በሰብዓዊ እና ዲሞክራሲ መብቶች ላይ የሚሰሩ ማህበራትን ማስተባበር 👉ማህበራቱ የጋራ መድረክ እንዲኖራቸው ማስቻል 👉በሰብዓዊ መብት እና ዲሞክራሲ ስራዎች ላይ የተሻለ ስራ እንዲሰራ ማስተባበር 👉የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት . . . ማንኛውም የበጎ አድራጎት ፈቃድ ያላቸው፤ የሰብአዊ እና የዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲሁም መልካም አስተዳደር ላይ የሚሰሩ ማንኛውም ማህበራት አባል መሆን ይችላሉ።
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሰሜን ወሎ ወልዲያ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግፍ ( የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ )

በሰሜን ወሎ ወልዲያ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግፍ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል። የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በ145ኛ ልዩ መግለጫ የተመለከተው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የተፈጸሙትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ሲሆን የመብት ጥሰቱ የተፈጸመው ከሕዳር 24 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 04 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ነው። ሰመጉ ባለሙያዎቹን ወደ አካባቢው ልኮ የማጣራት ሥራውን የሰራው ከየካቲት 05 እስከ የካቲት 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በዚህም መሰረት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ወልደያ ከተማ፣ ወልደያ ዙሪያ ወረዳ፣ ቆቦ፣ ሮቢት፣ መርሳ፣ ውርጌሳ እንዲሆም በደቡብ ወሎ ደሴ የተፈጠሩት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መርምሮ በዚህ መግለጫ አካቷል። በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተሰነዘሩ17 ዜጎች እንደጠፋ እና የአካል ጉዳት እንደደረሰ ሪፖርቱ በምስል አስደግፎ አቅርቧል። 1. ሟች መምህር ታምሩ በሪሁን፡- ዕድሜ 42፣ በፌደራል ፖሊስ በጥይት የተገደለ። 2. ሟች ተማሪ ዮሴፍ እሸቱ፡- ዕድሜ 15፣ በታጠቁ የመንግስት ሀይሎች በጥይት የተገደለ። 3. ሟች ገብረመስቀል ጌታቸው፡- ዕድሜ 35፣ በታጠቁ የመንግስት ሀይሎች በጥይት የተገደለ። 4. ሟች ወ/ሮ ዝይን ንጋቴ፡- ዕድሜ 60፣ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ጭንቅላታቸውን በጥይት ተመተው የተገደሉ። 5. ሟች ንጉሴ አበበ፡- ዕድሜ 18፣ በታጠቁ የመንግስት ኃይሎች ግራ ጎኑ ላይ በጥይት ተመትቶ የተገደለ። 6. ሟች ህጻን ዳንኤል ካሳ፡- ዕድሜ 9፣ ታጠቁ የመንግስት ኃይሎች ጀርባው ላይ በጥይት ተመትቶ የተገደለ። 7. ሟች ሰይድ ፍሬው ፡- ዕድሜ 31፣ በታጠቁ የመንግስት
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የማነ አስፋው፣ የሸዋ ሮቢቱ የቀን ጅብ (ጌታቸው ሺፈራው)

የማነ አስፋው፣ የሸዋ ሮቢቱ የቀን ጅብ (ጌታቸው ሺፈራው) ኢቲቪ የቀን 7 ሰዓት ዜና ላይ ስለ ሸዋሮቢት እስረኞች ሰቆቃ አንድ ዘገባ ሰርቷል። ዘገባው እየታየ አንድ የሸዋሮቢት ኃላፊ እስረኞች ልብሳቸውን እያወለቁ ስላሳዩት ሰቆቃ መልስ መስጠት ጀመረ። የማነ አስፋው ነው። የማነ “አንድም እስረኛ ጉዳት ደርሶበት ተመትቶ አያውቅም” እያለ ስለመገረፋቸው ልብሳቸውን አውልቀው ያሳዩት የእስረኞቹን ሰቆቃ ለማስተባባል ሲሞክር ሸዋሮቢት እስር ቤት ጉልበቱን በሚስማር የተመታው አግባው ሰጠኝ ከጎኔ ነበር። ወዲያውኑ ደግሞ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤን ደውዬ ጠየኩት። መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ከደረሰበት ድብደባ በላይ የማነ “እገድልሃለሁ” ብሎ እንደዛተበት አጫወተኝ። “ማን እንደነገረው አላውቅም፣ ብቻ ገብቶ ማስረሻ የምትባለው በሕይወትህ ፍረድ፣ እገድልሃለሁ ብሎኛል!” ይላል ማስረሻ! ወደናትናኤል ያለምዘውድ ደውዬ የማነ ሸዋሮቢት እስረኛ አይደበደብም ማለቱን ስነግረው “የማነ ራሱ ደብድቦኛል” አለኝ። ናቲ ስለ ሸዋሮቢት የስቃይ እስር ቤት አንድ አሳዛኝ ፅሁፍ ፅፎ ነበር። በወቅቱ ነገረ ኢትዮጵያ ላይ አትመነዋል። ይህን ፅሁፍ የፃፈው ከሸዋሮቢት ወደ ቃሊቲ ከተመለሰ በኋላ ነው። እንደገና ቅጣት ብለው ወደ ሸዋሮቢት መለሱት። ሸዋሮቢት የቅጣት እስር ቤት ስለሆነ “ቅጣት” ተደርጎ ይላካል። ይህ ፅሁፍ ኢሳት ላይ ሲተረክ ያየው የማነ ናትናአል ከቃሊቲ ሲመለስ ጠብቆ ደብድቦታል። “ከእሱ በፊት የነበረው አቡ የሚያስደበድብህ በሌላ ሰው ነው። የማነ ግን ቆሞ ነው የሚያስደበድብህ፣ ራሱ የማነ ደብድቦኛል” አለኝ ናትናኤል። አንጋው ተገኘም የማነን ያውቀዋል። በድብደባ ተሰባብረው በወደቁበት ቤት ከፍቶ ገብቶ “ምን ችግር አለ?” ይላል የማነ። ቆሞ ነውኮ ያስደበደባቸው። አንጋውም “እንዴት ተሰባብረን ወድቀን
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት የነበሩ የህግ ታራሚዎች ኢ- ሰብዓዊ ድርጊት እንደተፈፀመባቸው ገለጹ፡፡ (ቪድዮ)

በሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት የነበሩ የህግ ታራሚዎች ኢ- ሰብዓዊ ድርጊት እንደተፈፀመባቸው ገለጹ፡፡ ሕክምና እና የቤተሰብ ጉብኝትን ከህግ ውጪ ተከልክለናል ብለዋል፡፡ የሸዋሮቢት ተሀድሶ ልማት ማዕከል ማረሚያ ቤት በበኩሉ ድርጊቱን አልፈጸምኩም ብሏል፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“አስከሬኑን” መንግስት አሽጎ አስቀብሮት፣ በእስር ቤት ተገኘ የተባለው ተስፋሁን ጉዳይ

የቀን ጅቦች ጉድ! ~”አስከሬኑን” መንግስት አሽጎ አስቀብሮት፣ በእስር ቤት ተገኘ የተባለው ተስፋሁን ጉዳይ (ጌታቸው ሺፈራው) ተስፋሁን የእኔአባት ይባላል። ወታደር ነበር። ከወታደር ቤት ለእረፍት ቤተሰቦቹ ወደሚኖርበት ቤተሰቦቹ ባህርዳር ሲመጣ እናቱ ጥሩአለም መንግስቴ “አትሂድብኝ” ይሉታል። የእናቱን ስጋትና ልመና ሰምቶ ወደወታደር ቤት ሳይመለስ ይቀራል። “ከስራው ቀረ” ያሉ አካላት ያፈላልጉት ስለነበር ቦታ ቀይሮ ተቀመጠ። እንደገና ወደባህርዳር ሲመለስ እንደሚፈለግ አወቀ። ተስፋሁን የእኔአባት ከጓደኛው ቴዎድሮስ መኮንም ጋር በ1994 ዓም ክረምት ወር ከባህርዳር ወደ ኢዲስ አበባ እየሄደ ነበር። “በሰላም ግቡ” ብሎ የሸኛቸው ቤተሰብ የሰማው አዲስ አበባ በሰላም መግባታቸውን አልነበረም። ቤተሰቦቻቸው በመንግስት ሚዲያ የሰሙት ማመን ያቃታቸውን ዜና ነበር። ወደ አዲስ አበባ የተሳፈሩበት አውሮፕላን ሊጠልፉ እንደነበር በዜና ተነገረ። ከቀናት በኋላ ደግሞ ማሕተም ተደርጎበት የተሻገ አስከሬን መጣላቸው። የተስፋሁን ቤተሰቦች ሰኔ 2/1997 ዓም አስከሬን ነው ተብሎ የታሸገ ሳጥን ብር ከፍለው ተረከቡ። “ከፍተን እንየው” ሲሉ እንደማይቻል ተነገራቸው። በወቅቱ ቀብሩ ሲፈፀም ደሕንነቶች ቆመው ነበር። እናቱ ጥሩአለም መንግስቴ “የልጄን አስከሬን ካላየሁ” ብለው የደሕንነቶችን ትዕዛዝ አልቀበልም አሉ። ደሕንነቶቹ ደግሞ “ከፍተን እናያለን ካላችሁ” መልሰን እንወስደዋለን አሉ። ለቀስተኛው “ሳይቀበር ከሚቀር” ብሎ እናቱ የደሕንነቶችን ትዕዛዝ እንዲቀበሉ አግባባ። የተስፋሁን የእኔአባት ቤሰተቦች ለወጣቱ ሀውልት የማቆም ፍላጎት ነበራቸው። አስከሬኑ በሳጥን ሰንብቶ ሀውልት የሚሰራበት አካባቢ እንዲቀበር ፍላጎታቸውን ገለፁ። አስከሬኑን ከፍተው ያዩታል ብለው የሰጉት ደሕንነቶች ግን ይህንም አልተቀበሉም። “ዛሬ እኛ ባለንበት ካልተቀበረ መልሰን እንወስደዋለን” ብለው አቋማቸውን አሳወቁ። በቀብር ስነ ስነ ስርዓት ጣልቃ ገቡ።
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ታሪክና ሕዝብ እንዲፈርድ በድብቅ ከማእከላዊ የወጣ ኢሰብአዊ ምስል

ታሪክና ሕዝብ ይፍረድ! ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ይህ ምስሉን የምትመለከቱት ወጣት ማንደፍሮ አካልነው ይባላል። ከአጠገቡ የሚታየው ደግሞ ከሰባት ዓመታት በፊት በማዕከላዊ በደረሰበት ከፍተኛ ድብደባ ወደቃሊቲ እስር ቤት ከተላከ በሁዋላ ቀለሙን የቀየረው አካሉ እየተቀረፈ ይንጠባጠብ ስለነበር በወቅቱ “ታሪክና ሕዝብ ይፍረድ” ብለን በድብቅ ያስወጣነው የትግል አሻራው ነው። ወጣት ማንደፍሮ በላስታ ላሊበላ የመኢአድ አባልና በ2002 ዓ.ም የክልል ም/ቤት ተወዳዳሪ የነበረ ሲሆን በአከባቢው የሥርዓቱ ካድሬዎች ብዙ እንግልቶች ካደረሱበት በሁዋላ እርሱን ጨምሮ ወጣት መሰለ ድንቁ ከአይና ቡግና፣ ወጣት ቴዎድሮስ አያሌው ከወልዲያ፣ አቶ ሲሳይ ብርሌ ከኡርጌሳ እና ሌሎችም ለዴሞክራሲ የሞገቱ የእናት ኢትዮጵያ ልጆች ግንቦት 20 ቀን 2003 ዓ.ም ወደማዕከላዊ ምርመራ መጥተዋል። በሰው ልጅ ላይ ሊፈጸም ይችላል ተብሎ የማይገመት የግፍ መአትም ወርዶባቸዋል። በወቅቱ እኔ በሌሊት ወደ ግፈኛው ምርመራ ክፍል ስወሰድ እነዚህ ወጣቶች ፊታቸው በደም ተሸፍኖና ሰውነታቸው ቆሳስሎ በሸክም ሲመለሱ አይ ነበር። ሲናገሩት ይቀላል፤ ሲኖሩት ይከብዳል! ከማንደፍሮ ጋር ዛሬ የተገናኘነው በወቅቱ በደረሰበት ድብደባ በተደጋጋሚ ራሱን እየሳተ፣ አንዳንድ የሰውነት ክፍሎቹን መቆጣጠር ባለመቻሉና በመሳሰሉት የህክምና እርዳታ ፈልጎ ወደመዲናችን በመምጣቱ ነበር። ይሁንና ለህክምናው የሚያስፈልገው ወጪ ከጠበቀው በላይ ሆኖ በመገኘቱ ከነህመሙ ወደትውልድ አከባቢው እያዘነ ለመመለስ ተገዷል። እሱና ሌሎች ወንድም እህቶቻችን የከፈሉት ዋጋ ለነፃነትና ለዴሞክራሲ ቢሆንም በእንደዚህ አይነት ሁኔታ አጋርነታችንን ማሳየቱም የህሊና እርካታ ይሰጣልና ከዚህ ወንድሜ ጎን እንድትቆሙ በአክብሮት እጠይቃለሁ። የስልክ ቁጥሩ:- (0922- 629000) ነው። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ያስብ፤ ሕዝቧን ይባርክ!
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News