Blog Archives

የቴሌኮም ጥቅል አገልግሎቶችን በህገ-ወጥ መንገድ ለደንበኞች በመሸጥ ላይ የተሳተፈ የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኛ በህግ ቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኛ በህግ ቁጥጥር ስር ዋለ የቴሌኮም ጥቅል አገልግሎቶችን በህገ-ወጥ መንገድ ለደንበኞች በመሸጥ ላይ የተሳተፈ የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኛ በህግ ቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ሰራተኛው ኩባንያው ያወጣውን የሲስተም አጠቃቀም ፍቃድ ፖሊሲ እና የቴሌኮም ማጭበርበርን ለመከላከል የወጣውን ፖሊሲ በመጣስ ከ3ሺ በላይ ጥቅል አገልግሎቶችን ለ2 ሺ 1 መቶ 35 ደንበኞች በህገ-ወጥ መንገድ በመሸጥ ሲሳተፍ እንደነበር ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡ በኩባንያው የደህንነት ቡድን ክትትል ሲደረግበት የነበረው ሰራተኛው ህገ-ወጡን ተግባር ሲፈፅም እጅ ከፍንጅ ተይዞ ለህግ አስከባሪ አካላት ተላልፎ መሰጠቱም ተገልጿል፡፡ ከህገ ወጥ ተግባሩ ጋር በተያያዘ ተገቢውን ክፍያ ሳይፈጽሙ ግልጋሎቱን ሲያገኙ የነበሩ የ2 ሺ 135 ደንበኞች አገልግሎት መቋረጡንም ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡ በመሰል ህገ-ወጥ ተግባራት በሚሳተፉ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ የሚያደርገውን ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታወቀው ኢትዮ ቴሌኮም ተግባሩን በማጣራት አግልግሎትን እስከማቋረጥና በህግ ተጠያቂ እስከማድረግ የደረሰ እርምጃን እንደሚወስድ ይፋ አድርጓል፡፡ ህዝቡ የቴሌኮም ማጭበርበር ተግባራት በሀገር ደህንነትና ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሱትን አደጋ በመገንዘብ ለጸጥታና ለህግ አስከባሪ ተቋማት ጥቆማውን በማቅረብ ህገወጦችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋጽዖ እንዲያበረክት ኢትዮ ቴሌኮም ጥሪ አቅርቧል።
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የስልክ ቀፎዎችን የማስመዝገብ አሰራሩም ደንበኞችን ከማጉላላት ያለፈ ጠቀሜታ አልነበረውም፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም

‹‹ከሁለት የስልክ ቀፎዎች በላይ ወደ ሀገር ማስገባት አይቻልም የሚለው ገደብ ተነስቷል፡፡›› ‹‹የስልክ ቀፎዎችን የማስመዝገብ አሰራሩም ደንበኞችን ከማጉላላት ያለፈ ጠቀሜታ አልነበረውም፡፡›› ኢትዮ ቴሌኮም ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡም ሆነ ከሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ የስልክ ቀፎዎችን ለማስከፈት ወደ ጉምሩክ እና ኢትዮ ቴሌኮም መስሪያ ቤቶች መሄድ እንደማያስፈልግ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡ የስልክ ቀፎዎች አገልግሎት ከመጀመራቸው በፊት በኢትዮ ቴሌኮም እና በጉምሩክ በኩል ህጋዊነታቸው እንዲረጋገጥ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ዓላማውም ህገ ወጥነትን ለመከላከል ተብሎ እንደ ነበር ይታወቃል፡፡ አሰራሩም ወጥነት የሌለው፣ክፍተቶች ያሉበት እና ደንበኞችን ከማጉላላት ባለፈ የጎላ ፋይዳ ያልታየበት መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱራሂም አህመድ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ተናግረዋል፡፡ ከሁለት የስልክ ቀፎዎች በላይ ወደ ሀገር ማስገባት እንደማይቻል የሚከለክለው እገዳም ተነስቷል ነው ያሉት አቶ አብዱራሂም፡፡ በመሆኑም IMI ቁጥር ያላቸውን ማለትም ደረጃውን የሚያሟሉ የስልክ ቀፎዎችን ኢትዮጵያ ውስጥ መገልገል እንደሚቻል አረጋግጠውልናል፡፡ በመሆኑም ወደየተቋማቱ መሄድ ሳያስፈልግ አዳዲስ የስልክ ቀፎዎችን መገልገል ይቻላል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም በዘርፉ የሚስተዋሉ የኮንትሮባንድ እና የቴሌኮም ማጭበርበርን ለመግታትም ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎች ተግባራዊ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡ እንደ አቶ አብዱራሂም መረጃ የታሪፍ ቅናሽ አና የስልክ ቀፎዎችን አለማስመዝገብ ከትናንት ነሀሴ 17/12/10 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሕወሓት የንግድ ድርጅቶች ካልታገዱ ለታቀደው ፕራይቬታይዜሽን ትልቅ አደጋ አለው ።

ምንሊክ ሳልሳዊ የሕወሓት የንግድ ድርጅቶች ካልታገዱ ለታቀደው ፕራይቬታይዜሽን ትልቅ አደጋ አለው ። የፖለቲካ ድርጅቶች በንግድ ስራ ላይ እንዳይሰማሩ ጥብቅ ህግ መውጣት አለበት። ፕራይቬታይዜሽን ጠቃሚ ነው፣ ግን ጎን ለጎን መንግስት ሙስና ላይ ዘመቻ መክፈት አለበት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች ከንግድ ስር መውጣት አለባቸው፣ የተዘረፉ ሃብቶች እንዲመለሱ ያስፈልጋል ። ሕወሓት የኢኮኖሚ የበላይነቱንና የስለላ መስመሩን ለማጠናከር በግል ኢንቨስትመት ስም አየር መንገድንና ቴሌን በመቆጣጠር ለዘረፋ ተዘጋጅቷል ።አሁን በተያዘው የሕዝብ የለውጥ መስመር ለመዝረፍ ለሕወሓት የማይቻል ሲሆን ምእራባውያን ደጓሚዎችም በሚፈጥሩት ጫና ተቋማቱ በከፊል ወደ ግል ዞረዋል በሚል ሽፋን ራሱ ሕወሓት በንግድ ድርጅቶቹና ወኪሎቹ ከእጁ እንዳይወጣ ያደርጋል ። አየር መንገድንና ቴሌን በመዝረፍ አክስሮ ከገበያ ውጪ ማድረግ እና ንብረቶችን በመውረስ ማሸሽ ሌላኛው የሕወሓት ግብ ነው። ብስለት ይጠበቅብናል ፤ በተገኘው በተነበበ መግለጫ ሁሉ ሀገር ለዘራፊዎች ሀገር ለአደጋ ተላልፋ ስትሰጥ እንደማየት አስከፊነት የለም ። ፕራይቬታይዜሽን ጠቃሚ ነው፣ ግን ጎን ለጎን መንግስት ሙስና ላይ ዘመቻ መክፈት አለበት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች ከንግድ ስር መውጣት አለባቸው፣ የተዘረፉ ሃብቶች እንዲመለሱ ያስፈልጋል። አየር መንገድንና ቴሌን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት አክስዮን ለመሸጥ መታሰቡ ሕወሓት በሌላ የዝርፊያ መንገድ መምጣቱ በቂ ማሳያ ነው ። እነዚህ ድርጅቶችን ለመቀራመት ከማቀድ በፊት የግል ባለሐብቶች በቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፍ እንዲሠማሩ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊፈቀድ ይገባል ። ሕወሓት የኢኮኖሚ የበላይነቱንና የስለላ መስመሩን ለማጠናከር አየር መንገድና ቴሌን መሰል ተቋሞቹን ተቆጣጥሮ የፖለቲካ የበላይነቱን ኦሕዴድ እንዲይዝ በስፋት እየሰራ ነው ። አየር መንገድንና
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የቴሌኮም ዘርፉ ነጻ ይውጣ ! ( Black Lion )

  የቴሌኮም ዘርፉ ነጻ ይውጣ! *** Black Lion *** የኢትዮጵያ መንግሥት ኢኮኖሚያዊ ዓላማ ያለው በሚመስል ሰበብ የቴሌኮም ዘርፉን ለነጻ ገበያ ውድድር ክፍት አላደረገውም። በመንግሥት ይዞታ ሥር ያለው ብቸኛው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት – ኢትዮ ቴሌኮም – አገሪቱን በተቋቋመለት የሕግ አግባብ መሠረት “…ዓለም ዐቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎትን መስጠትና ማዳረስ” አልተቻለውም። በዚህ ምክንያት አገራችን ከ95 በመቶ በላይ ለሚሆኑት ዜጎቿ ኢንተርኔትን ማዳረስ አልቻለችም። በተንቀሳቃሽ ስልክ ተዳራሽነት፣ በቴሌቪዥን ስርጭት እና ሌሎችም አገልግሎቶች ከጎረቤት አገሮች አንጻር እንኳን ዕኩል መጓዝ አልቻለችም። ይህ ለምን ሆነ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ከዚሁ እጅግ ውስን ከሆነችው የኢንተርኔት ተዳራሽነት ላይም አፈናው ከፍ ያለ ሆኗል። የኢትዮጵያ መንግሥት የተቺዎቹን የዜና ድረገጽ በማገድ በአፍሪካ ፈር ቀዳጁ ነው። ኢትዮጵያ ይህንን ማድረግ የሚያስችላት ቁሳቁስ በውድ ዋጋ መሸመቷም እንደ ‹ፍሪደም ሐውስ› ባሉ ድርጅቶች ተጋልጧል። በተለያዩ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ላይ የሚመሠረቱ ክሶች የተንቀሳቃሽ ስልክ ንግግራቸው ለዓመታት እንደተጠለፈ የሚያስረዳ ነው። ይህ የሚያሳየው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የቴሌኮም መረቡን ተጠቅሞ ዜጎቹን ለመሰለል ወይም ከመረጃ ለመገደብ ያለውን ቁርጠኝነት ያክል፣ ዜጎቹ የቴክኖሎጂው ትሩፋት ተቋዳሽ እንዲሆኑ ፈቃደኝነቱ እንደሌለው ነው። የቴሌኮም ተዳራሽነት የዓለምን፣ በተለይ ደግሞ የድሃ አፍሪካውያንን ሕይወት በተለያየ መንገድ እየቀየረ ነው። በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት እና በመዝናኛ መስኮች ሁሉ የቴሌኮም ተወዳዳሪነትን በፈቀዱ አገራት በተለይም በኬንያ፣ በናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ እንዲሁም ጋና በመሳሰሉት አገራት እየተመዘገበ ያለው እመርታ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊታይ ያልቻለው ዘርፉ የመወዳደር ብቃታቸው አነስተኛ በሆኑ ሰዎች
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News