↪የምሽት ሚስጢራዊ መረጃ
የዛሬ ዛቻ ነገ እስርን ይወልዳል!
______________________________
↪ዱዓቶቻችንና ወንድሞቻችን በጥበቃና ደህንነት ክፍሉ ጫናና ዛቻ እየደረሰባቸው
መሆኑ ተገለፀ።
ሙጂብ አሚኖ ዘ ኢስላም
______________________________
↪ከ1997 ምርጫ አንስቶ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በንቃት እየተከታተሉ የሚገኙት
የፖርቱጋል ሶሻሊስት ፓርቲና የአውሮፓ ሶሻሊስት ፓርቲ አባል፤ እንዲሁም
የአውሮፓ ፓርላማና የፓርላማው የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አባል አና ማሪያ ሮሳ
ጎምሽ የዶ/ር አብይ አሕመድ መሾም “ለኢትዮጵያም ሆነ ለኦሮሞ ሕዝብ በጎውን
ሊያመጣ፣ ጥቅማቸውን ሊያስጠብቅ የሚችል ነው” የሚል ሃሣብ በብዙዎች
ዘንድ እየተንፀባረቀ መሆኑን ጠቅሰው በመግለፅ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግልፅ
መልዕክቶችን ማስተላለፋቸው ጥሩ ምልክት ነው፤ ነገር ግን እስኪ ተግባሩን
እንጠብቅ” ብለው ነበር ከጠቅላያችን ጣፋጭ ንግግር በስተጓዳኝ ትግበራው
ላይ ጥርጣሪያቸውን አስምረው በማስቀመጥ ንግግራቸውን ያደረጉት።
↪እኛም በግላችን ለኢትዮጲያ ህዝብ እፁብ ድንቅ የዲሞክራሲ መርህ ይዞልን
አዲሱ ጠቅላያችን ከተፍ ቢል ምንኛ ጮቤ እንደምንረግጥ ይታወቃል።
ከዚህም በዘለለ ደግሞ ላለፉት ስድስት አመታት ህዝበ ሙስሊሙ ከአወሊያ
የተማረዎች ንቅናቄ ጋር ተያይዞ ያነሳቸው የፍትህና የነፃነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ
በርካታ መጓተቶች ዛሬ ድረስ ተጉዘው መተዋል። በርካቶች ታስ�ረዋል፣
ተገርፈዋል፣ ተሰውተዋል፣ ከአይን ብሌናችን በላይ የምንሳሳላቸው እህቶቻችን
አላህ በጀነት ይካሳቸውና ተደፍረዋል…ወዘ ተረፈ እኩይ ተግባራቶች
ተፈፅመውብናል።
↪የኢህአዴግ መንግስት እስረኞችን ለበርካታ አመታት ከሌሎች እስረኞች በተለየ
ሁኔታ /ባገለለ መልኩ/ አስሮ ካሰቃየ ቡሃላ ቀስ በቀስ ነጣጥሎ የኮሚቴውን
አባላት በዚህ በያዝነው አመት አጠናቆ ፈቷል። ሌሎች ከዚህ እንቅስቃሴ ጋር
ተያይዞ በእስር ላይ የነበሩ ወንድሞችና እህቶች ደግሞ እስራቸውን ጨርሰው
የተፈቱ አሉ። ጥቂት የማይባሉት ደግሞ